Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውሃ እየተሟጠጠ መሆኑን ጥናት አመለከተ የአዲስ አበባ የከርሰ ምድር | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የአዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውሃ እየተሟጠጠ መሆኑን ጥናት አመለከተ

የአዲስ አበባ የከርሰ ምድር ውሃ እየተሟጠጠና በመዲናይቱ የውሃ አቅርቦት አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደደረሰ በዚህ ሳምንት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጉባኤ ላይ የምህንድስና ባለሙያዎች ያቀረቡት ጥናት ማመልከቱን ሪፖርተር ዘግቧል።

መዲናይቱ በአሁኑ ወቅት በቀን 1.2 ሚሊዮን ኪውቢክ ሜትር የውሃ ፍላጎት እንዳላት ሲገለፅ ነገር ግን የውሃ አቅርቦቱ 40 በመቶ የሚሆነውን ፍላጎት ብቻ እየሸፈነ ስለመሆኑ ተመላክቷል። የከተማዋ የውሃ ፍላጎት ከአቅርቦት በላይ መሆኑ የውሃ ጥራት እንዲኖር አድርጓልም ተብሏል።

ቁጥጥር ያልተደረገበት የከርሰ ምድር ውሃ አጠቃቀም እንደሚስተዋል ጥናቱ ሲጠቁም የውሃ ማጠራቀሚያ ታንኮች ላይ ጥገኛ መሆን ችግሩን እያባባሰው እንደሆነ ተጠቁሟል። ይህንን ለመቅረፍ የዝናብ ውሃን ለማከማቸት የሚረዱ ማጠራቀሚያዎችን መገንባት እንደሚገባና መንግስትም የውሃ ቁፋሮ እና የከርሰ ምድር ውሃ አጠቃቀምን የተመለከቱ ጠንካራ ህጎች ማውጣት እንዳለበት ባለሙያዎቹ አሳስበዋል።

@TikvahethMagazine