Get Mystery Box with random crypto!

#NewsAlert በአዲስ አበባ ከተማ እየተስፋፋ የመጣው የእገታ ወንጀል ከሰሞኑ በስፋት እየደረ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

#NewsAlert በአዲስ አበባ ከተማ እየተስፋፋ የመጣው የእገታ ወንጀል

ከሰሞኑ በስፋት እየደረሱኝ ያሉ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በፊት በፊት በክፍለ ሀገራት፣ ከዛም በአንዳንድ የአዲስ አበባ አቅራቢያ ስፍራዎች ሲከናወኑ የነበሩ የእገታ ወንጀሎች አሁን ላይ በአዲስ አበባ ከተማ መታየት ጀምረዋል።

ከ10,000 ብር ጀምሮ እስከ 1 ሚልዮን ዶላር የተጠየቀባቸው ሰዎች እንዳሉ፣ እገታዎቹ በቀንም ይሁን በጭለማ እንደሚከናወኑ፣ አብዛኞቹ የፀጥታ አካላትን በመምሰል (ወይም ሆነው... ይህ ሲጣራ ይታወቃል) ድርጊቱን እንደሚፈፅሙ እና ከመኖርያ ቤታቸው ጭምር የተወሰዱ ሰዎች እንዳሉ አረጋግጫለሁ።

እንደ ነጋዴዎች፣ ዲያስፖራዎች እና የውጭ ዜግነት ያላቸው ሰዎች እና ብር አላቸው ተብለው የሚገመቱ ማንኛውም ሰዎች በተለይ ኢላማ እንደሆኑ ታውቋል።

አጋቾቹ ድርጊቶቹን ከፈፀሙ በኋላ ታጋቾች ድርጊቱን ለፖሊስ እንዳያሳውቁ ስለሚያስፈራሩ ትክክለኛ የድርጊቱን መጠን ለማወቅ አስቸጋሪ ነው።

ማስተባበል መቼም መፍትሄ ስለማይሆን አሁንም ሳይረፍድ የሚመለከተው አካል በይፋ ወደፊት በመምጣት ድርጊቱን ቢያንስ በይፋ ለህዝብ ማሳወቅ አለበት።

ከእንዲህ አይነት እገታ 'ተጠንቀቁ' ቢባል እንዴት መጠንቀቅ እንደሚቻል ባላውቅም... ብቻ ጥንቃቄ አይለየን።

@EliasMeseret