Get Mystery Box with random crypto!

አጎት ባልቻ እስቲ ዛሬ ትንሽ ስለ አጎት ባልቻ እንጨዋወት። ጽሁፉን ከዚሁ ሰፈር ማግኘቴን ከወ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

አጎት ባልቻ

እስቲ ዛሬ ትንሽ ስለ አጎት ባልቻ እንጨዋወት። ጽሁፉን ከዚሁ ሰፈር ማግኘቴን ከወዲሁ ልንገራችሁ። ነገር ግን ወሬ ጨማምሬበት ኢትዮጵያዊ ቃና እንዲኖረው አድርጌያለሁ።

ለመሆኑ አጎት ባልቻ ማን ናቸው?! አትቸኩል፣ ልነግርህ ነው። አጎት ባልቻም እንዲሁ እንዳንተ ችኩል ነበሩ።

አጎት ባልቻ ለ40 ዓመታት ያህል አሜሪካን አገር ከኖሩ በኋላ፣ በ70 ዓመታቸው ወደ አገራቸው ተመለሱ። በያዝነው ዓመት ነው ባለ 5 መኝታ ቤት የተንጣለለ ቤታቸው ውስጥ መኖር የጀመሩት። የቤት መስሪያ ገንዘብ ለመቆጠብ ድፍን 30 ዓመታትን ፈግተዋል። ቤቱን ለመገንባት ደግሞ 10 ዓመታትን።

የአጎት ባልቻ ቤት የተንጣለለ ባለ ሶስት ወለል ቪላ ነው። አምስት ቅንጡ መኝታ ቤቶች ያሉት ሲሆን፣ ሁሉም መኝታ ቤቶች የሚገኙት ከሁለተኛ ወለል ጀምሮ ነው። በተለይ ግዙፉ እና ቅንጡ ዋና መኝታ ቤት የሚገኘው ሶስተኛ ወለል ላይ ነው። ከታች ያሉ ከፍሎች ሳሎን፣ ወጥ ቤቶች እና የእንግዳ መጸዳጃ ቤት ናቸው።

አጎት ባልቻ አሁን የሚኖሩት ከታች ባለው የቤቱ ሳሎን ውስጥ ነው። ምክንያቱም የ70 ዓመቱ አዛውንት ያለ ሌላ ሰው እርዳታ ደረጃውን መውጣት አይችሉም። በሰው እርዳታም ቢሆን ቢያንስ 10 ደቂቃ ይፈጅባቸዋል። ለዚህ ነው ሳሎን ውስጥ ለመኖር የወሰኑት። ቅንጡ እና ዋና መኝታ ቤታቸው ውስጥ የቤት ሰራተኛቸው እንድትተኛ ፈቀዱ።

አጎት ባልቻ የጡረታ ኑሮአቸው እንደዚህ ይሆናል ብለው የገመቱ አይመስልም። ተጨባጭ እውነታ ግን ይሄው ነው። አጎት ባልቻ አስደሳች የሚባል ህይወት የላቸውም። የፈለጉትን ምግብ መመገብ ብቻ ሳይሆን የፈቀዱት መኝታ ቤት ውስጥ እንኳን መተኛት አይችሉም።

እና በውጭ አገር እየኖርህ ቤት የምትገነባ ወዳጄ፣ ቤቱ ግፋቢል ከ50 ዓመትህ በፊት ተሰርቶ የማያልቅ ከሆነ እርሳው። እንደ አጎት ባልቻ 40 ዓመታትን አታባክን። በፍጹም ከጡረታ በኋላ እኖራለሁ ብለህም አታስብ፤ ከጡረታ በኋላ ህይወት የለም። አሁኑኑ በመሃል በመሃል ጡረታ እየወጣ ተዝናና።

በአጎት ባልቻ ስም ጧ ያለ እንቅልፍ ተመኘሁልህ።
Lami S