Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ኮርፖሬሽን ጨረታ ባወጣባቸው | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

የኢትዮጵያ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ኮርፖሬሽን ጨረታ ባወጣባቸው የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ መደብሮች ዙሪያ ከጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ላቀረቡበት ቅሬታ ባንድ ሳምንት ውስጥ ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቋል። ኮርፖሬሽኑ ከኹለት ሳምንት በፊት ጨረታ ያወጣው፣ በ3 ሺህ 146 የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በ306 ለንግድ መደብርነት በተሠሩ ቤቶች ላይ ነበር። ኾኖም ከ950 በላይ የ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝጋቢዎች የጨረታውን መውጣት በመቃወም ለእንባ ጠባቂ ተቋም አቤቱታ አቅርበዋል። እንባ ጠባቂ ተቋም፣ ለዓመታት ገንዘብ በባንክ እየቆጠቡ የጋራ መኖሪያ ቤት ያልደረሳቸው በርካታ ተመዝጋቢዎች እያሉ ኮርፖሬሽኑ ለምን በጋራ መኖሪያ ቤቶቹ ላይ ጨረታ እንዳወጣ ማብራሪያ እንዲሰጥ ነው። ኮርፖሬሽኑ ቀደም ሲል የቆረጠውን የጨረታ ማውጫ ቀን ወደ መጋቢት 3 አራዝሞታል።

ዋዜማ