Get Mystery Box with random crypto!

ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች 5 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሊገነባ ነው **** በ450 ሚሊዮ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች 5 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ሊገነባ ነው
****

በ450 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ለሚገነባው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ሰራተኞች ሁለተኛ ምዕራፍ የ5 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ዛሬ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።

የግንባታ ፕሮጀክት ማስጀመሪያ የመሰረት ድንጋዩን የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስቀምጠዋል።

በግንባታ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ የሰንሻይን ኮንስትራክሽን ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ሥራ አስፈጻሚ ሳሙኤል ታፈሰ፣ የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ታረቀኝ ገመቹና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

በ17 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የቤቶቹ ግንባታ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሲኤምሲ ልዩ ሥሙ ሃያት-49 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ እንደሚከናወን ተገልጿል።

ግንባታው በሰንሻይን ኮንስትራክሽንና በቻይናው ኮንስትራክሽን ኮሙኒኬሽን ኩባንያ (ሲሲሲሲ) የሚከናወን ሲሆን በአራት ዓመት ውስጥ ይጠናቀቃል መባሉን ኢዜአ ዘግቧል።

በፕሮጀክቱ ከ5 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎችን የሚይዝ የመኪና ማቆሚያ ሥፍራ፣ የልጆች መጫወቻ፣ አረንጓዴ ሥፍራ፣ ትምህርት ቤት፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሥፍራና የገበያ ማዕከላት እንደሚይዝ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ቤቶቹ የራሱ ጥልቅ ጉድጓድ ውኃና የፀሐይ ኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት እንደሚኖረውም ተመላክቷል።