Get Mystery Box with random crypto!

ኮርፖሬሽኑ ከአራት ኪሎ ቀበና የመንገድ ኮሪደር ለተነሱ 21 የልማት ተነሺዎች የእጣ ማውጣት ስነ ስ | Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች

ኮርፖሬሽኑ ከአራት ኪሎ ቀበና የመንገድ ኮሪደር ለተነሱ 21 የልማት ተነሺዎች የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት አካሄደ

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከየካ ክፍል ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ከአራት ኪሎ ቀበና የመንገድ ኮሪደር ለተነሱ 21 የልማት ተነሺዎች ምትክ ቤት ለመስጠት እጣ የማውጣት ስነ ስርዓት አካሄደ።

ዕጣ የማውጣት መርሀግብሩ ላይ የተሳተፉት አዲስ አበባን የሚመጥን የኮሪደር ልማት ስራ የሚሰራባቸው አካባቢዎች ላይ የሚገኙ ተነሺዎች ሲሆኑ  የልማት ተነሺዎቹ  ተገቢው ምትክ እንደሚሰጣቸው በተገባው ቃል እና በመመሪያው መሰረት የጋራ መኖሪያ ቤት እጣ አውጥተዋል ።