Get Mystery Box with random crypto!

hotie preparatory

የቴሌግራም ቻናል አርማ hotiepreparatory — hotie preparatory H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hotiepreparatory — hotie preparatory
የሰርጥ አድራሻ: @hotiepreparatory
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.66K

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2022-09-22 09:46:50 ቀን 12/01/2015
ማስታወቂያ
የሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2013 እና የ2014ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
የሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2013 እና የ2014ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ2015 ዓ.ም መስከረም 28 ጀምሮ ለሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ምዝገባ ያከናወናችሁ ተማሪዎች በጤና ችግር ፣በወሊድ ምከንያትና በሌሎች አስቸጋሪ ምክንያቶች በተመደባችሁበት ዩኒቨርስቲ ገብታችሁ መፈተን የማትችሉ ተማሪዎች እስከ ነገ መስከረም 13/2015ዓ.ም ከቀኑ 6:00 ድረስ ብቻ ት/ቤት በመገኘት እንድታሳውቁ ት/ቤቱ በጥብቅ ያሳውቃል ።
የት/ቤቱን መረጃ በፍጥነት እንዲደርሳችሁ የት/ቤቱን የቴሌግራም ቻናላችንን @hotiepreparatory ይቀላቀላሉ
752 views06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-19 18:03:45 ቀን 09/01/2015
ማስታወቂያ
የሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2013 እና የ2014ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
የሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2013 እና የ2014ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ2015 ዓ.ም መስከረም 28 ጀምሮ ለሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ምዝገባ ያከናወናችሁ ተማሪዎች የመፈተኛ ወረቀት(Admition Card) ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከምትኖሩበት ቀበሌ የኗሪነት የታደሰ መታወቂያ እንድታወጡና በፈተና ወቅት ይዛችሁ እንድትገኙ ት/ቤቱ ያሳውቃል፡፡
የት/ቤቱን መረጃ በፍጥነት እንዲደርሳችሁ የት/ቤቱን የቴሌግራም ቻናላችንን @hotiepreparatory ይቀላቀላሉ
1.2K viewsedited  15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 11:34:59 ቀን 06/01/2015
ማስታወቂያ
የሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደትን በተመለከተ ከትምህረት ቤቱ ቀትስቦ፣ ወመህ፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ጋር ከ መስከረም 4-5/2015ዓ.ም ድረስ ውይይት አደረገ፡፡ በውይይቱም የ2014ዓ.ም የትምህርት ዘመን የስራ አፈጻጸም ጠንካራና ደካማ ጎኖች በበመለከተ፣ የ2015ዓ.ም የትምህርት ዘመን የስራ እቅድ እና የመምህራንና የትምህርት አመራር የዲሲፕሊን መመሪያ ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግና አቅጣጫ በማስቀመጥ አጠናቋል፡፡
የት/ቤቱን መረጃ በፍጥነት እንዲደርሳችሁ የት/ቤቱን የቴሌግራም ቻናላችንን @hotiepreparatory ይቀላቀላሉ
1.5K views08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-16 10:53:05 ቀን 06/01/2015
ማስታወቂያ
የሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2013 እና የ2014ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
የሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2013 እና የ2014ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ2015 ዓ.ም መስከረም 28 ጀምሮ ለሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ምዝገባ ያከናወናችሁ ተማሪዎች ስለፈተናው አጠቃላይ ገለጻ መስከረም 10/2015 ዓ.ም ስለሚሰጥ ሁሉም ተማሪ ከጧቱ 2፡30 ትምህርት ቤት በመገኘት ገለጻውን እንድትከታተሉ ት/ቤቱ ያሳውቃል፡፡
የት/ቤቱን መረጃ በፍጥነት እንዲደርሳችሁ የት/ቤቱን የቴሌግራም ቻናላችንን @hotiepreparatory ይቀላቀላሉ
1.4K views07:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 14:36:53 3. ለተፈታኞች የተፈቀዱ ነገሮች
ተፈታኞች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጡ ይዘው እንዲመጡ እና ግቢ ውስጥ እንዲጠቀሙ የተፈቀዱ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡
 አዲስ ወይም ቀድሞ ለመማርና ለማጥናት ሲጠቀሙበት የነበረ ማስተወሻ ደብተር፣ የትምህርት መጽሐፍ፣ መንፈሳዊ/ኃይማኖታዊ መጽሐፍት፣ ባዶ ወረቀት
 ደረቅ ምግቦች ወይም ሰንባች ምግቦች (ጩኮ፣ በሶ፣ ዳቦ ቆሎ፣ ቆሎ….)
 ገንዘብ (ብር)፣
 የልብስ ወይም የእጅ ቦርሳ፣ የግል ልብስ፣ ጫማ
 የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ (ሳሙና፣ ሞዴስ፣ የጥርስ ብሩሽ፣ የጥርስ ሳሙና፣ የገላ ማድረቂያ ፎጣ፣ ሶፍት፣ ሻምፖ፣ ኮንዲሽነር፣ ሎሽን፣ ቻፕስቲክ፣ የጸጉር ቅባት፣ የፊት ቅባት)
4. ለተፈታኞች የተከለከሉ ነገሮች
 በፈተና ማዕከል (ዩኒቨርሲቲ) እና መፈተኛ ክፍሎች ውስጥ የተከለከሉ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ማንኛውንም ዓይነት የጦር መሣሪያ ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውንም ዓይነት ስለት እና ሹልነት ያላቸውን ብረታ ብረቶችና ጠንካራ ፕላስትኮች ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም ድምጽ የሚቀዳ፣ ፎቶ የሚያነሳ፣ ቪዲዮ የሚቀርጽ፣ ከቴሌ መስመርም ሆነ ከቴሌ መስመር ውጭ መልዕክት በዲጂታል መንገድ የሚሰጥ ወይም የሚቀበል የግል ዕቃ/መሳሪያ /ቴክኖሎጂ ውጤት፣ ስልክ፣ አይ-ፓድ፣ ታብሌት፣ ኮምፕዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስማርት ሰዓት፣ ማጂክ ብዕር/እስክሪብቶ፣ ማጂክ ኮት/ጃኬት እና ሌሎች ማንኛቸውም ፎቶ፣ ምስል እና ድምጽ የሚቀርጹ የኤሌክትሮኖክስ መሣሪያዎችን በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥም ሆነ ግቢ ዙሪያ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ማንኛውንም ዓይነት የግል ፍላሽ ዲስክ፣ ሃርድ ዲስክ፣ ሲዲ፣ ሚሞሪ፣ ሚሞሪ ሪደር፣ ኦ-ቲጂ ኮንቨርተርና መሰል ዕቃዎችን ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም አደንዛዥ እጾች (ጫት፣ ሲጋራ፣ በሓኪም ማዘዣ የሌለው መድኃኒት (በሽሮፕም ይሁን በታብሌት፣ ህክምና መስጫ መርፌ)) መያዝ ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም ዓይነት የአልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት ወይም መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 ማንኛውም ዓይነት የአንገት ሐብል፣ የጸጉር ጌጥ፣ የጆሮ ጌጥ፣ የጣት ቀለበት፣ የእጅ አንባር፣ አድርጎ ወይም ይዞ መገኘት የተከለከለ ነው፡፡ (ከልሙጥ የጋብቻ ቀለበት በስተቀረ)
 ፈተና ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ ወደ ፈተና ክፍል መግባት እና ፈተናው ተጀምሮ 45 ደቂቃ ሳይሞላ ከፈተና ክፍል መውጣት የተከለከለ ነው፡፡
 ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ይዞ መውጣት ተከለከለ ነው፡፡
 በፈተና ሰዓት በመፈተኛ ክፍል ውስጥ ማስቲካ መያዝም ሆነ መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡
 በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ በግልም ሆነ በቡድን መጮህ ወይም በጣም ከፍተኛ ድምጽ ማሰማት የተከለከለ ነው፡፡
1.8K views11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-15 14:35:56 የ 2014/15 አገር አቀፍ የ 12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኞች በመፈተኛ ዩኒቨረስቲዎች ሊኖራቸዉ የሚችሉ መብቶች፡ ግደታዎች፡የተፈቀዱና ያልተፈቀዱ ጉዳዮች
1.የተፈታኞች መብቶች
የተፈታኞች መብት የተፈታኞች መብቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡
• ከፈተና ጥያቄ ውጪ ማንኛውንም ያልተረዳውን ነገር ጠይቆ የመረዳት መብት አለው፡፡
• በየኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ምግብ፣ የህክምና አገልግሎት፣ የማደሪያ ክፍል፣ ፍራሽና ትራስ የማግኘት መብት አለው፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለውን የቤተ መጽሐፍት፣ የመጸዳጃ ቤቶች፣ የሻወር፣ የካፍቴሪያዎች፣ የሚኒ ሱፐር ማርኬቶች፣ የተለያዩ ሱቆች፣ የመናፈሻና መዝናኛ አገልግሎቶችን የመጠቀም መብት አለው፡፡
• የኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ የጋራ የደህንነት ጥበቃ የማግኘት መብት አለው፡፡
• በፈተና ሰዓት መፈተኛ ክፍል ገብቶ ብርሃናማ የመፈተኛ ቦታ፣ ወንበር፣ መጻፊያ ጠረጴዛ የማግኘት መብት አለው፡፡
• ፈተና ከመጀመሩ አንድ ቀን ቀድሞ ስለፈተናው ገለጻ (ኦሬንቴሽን) የማግኘት መብት አለው፡፡
2. የተፈታኞች ግዴታ
ተፈታኞች የሚከተሉት ግዴታዎች አለባቸው፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከልም ይሁን መፈተኛ ክፍል አድሚሽን ካርድ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ የትምህርት ቤት ወይም የነዋሪነት መታወቂያ ይዞ መገኘት አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ግቢ ከመግባቱ በፊትና ወደ መፈተኛ ክፍል ከመግባቱ በፊት ሙሉ አካላዊ ፍተሻ የመፈተሽ ግዴታ አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ በዩኒቨርሲቲ ግቢና በመፈተኛ ክፍል የተከለከሉ ቁሳቁሶችን/ዕቃዎችን መያዝ የለበትም፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ እርሳስ፣ ላጲስና የእርሳስ መቅረጫ ይዞ መገኘት አለበት፤
• ማንኛውም ተፈታኝ የፈተና ደንብን የማክበር ግዴታ አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ በፈተና ማዕከል ውስጥና በመፈተኛ ክፍል ውስጥ የፈተና አስፈጻሚዎች የፈተና አስተዳደር ሥራን ውጤታማ ለማድረግና ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የሚያደርጉትን ጥረት የመተባበር ግዴታ አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ ፈተና ከመጀመሩ በፊት መፈተኛ ክፍል የመገኘት ግዴታ አለበት፡፡
• ተፈታኙ ፈተናው ሳይጠናቀቅ ከፈተና ክፍል የሚወጣ ከሆነ የፈተና ጥያቄ የያዘውን ቡኩሌት ለፈታኙ የማሰረከብ ግዴታ አለበት፡፡
• ማንኛውም ተፈታኝ ወደ ተመደበበት ዩኒቨርሲቲ ሲመጣ አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ጨርቅ ይዞ የመምጣት ግዴታ አለበት።
1.6K views11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 19:05:19
1.2K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-14 19:05:19 Share 'ለ 12ኛ ተፈታኞች.docx'
1.5K views16:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-12 15:47:51 ቀን 02/01/2015
ማስታወቂያ
የሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2013 እና የ2014ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
የሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2013 እና የ2014ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በ2015 ዓ.ም መስከረም 28 ጀምሮ ለሀገር አቀፍ ፈተና ለመፈተን ምዝገባ ያከናወናችሁ ተማሪዎች የመፈተኛ ወረቀት(Admition Card)ስለመጣ ቀጥሎ በወጣው ፕሮግራም መሰረት ት/ቤት በአካል በመገኘት እንድትወስዱ ያሳውቃል፡፡
• ዓርብ ጧት፡- የ2014ዓ.ም መደበኛ ተማሪዎች
• ዓርብ ከሰዓት፡- የ2014ዓ.ም የማታ ተማሪዎች
• ቅዳሜ ጧት፡- የ2013ዓ.ም መደበኛ ተማሪዎች
ማሳሰቢያ፡- በዕለቱ የስም፣የጾታ፣የፎቶግራፍና
የትምህርት ዘርፍ(stream) ስህተት ያጋጠመው
ተማሪ በአካል በመገኘት ማስተካከል ይኖርበታል፡፡
የት/ቤቱን መረጃ በፍጥነት እንዲደርሳችሁ የት/ቤቱን የቴሌግራም ቻናላችንን @hotiepreparatory ይቀላቀላሉ
2.2K viewsedited  12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ