2022-11-22 09:09:01
ቀን 13/03/2015 ዓ.ም
አስቸኳይ የጥሪ ማስታወቂያ
ለ2014 ዓ.ም 12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለወሰዳችሁ መደበኛ ፣ ድጋሚ ተፍታኝ እና የማታ(የግል) ተፍታኝ ተማሪዎች በሙሉ
የ2014 ዓ.ም የትምህርት መስክና የዩኒቨርስቲ ምርጫ በትምህርት ቤት ደረጃ የሚሞላው ከህዳር 13_14/03/2015 ዓ.ም ብቻ መሆኑን እየገለፅን ማንኛውም ተማሪ :-
1. ህዳር 13/03/2015 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት በአካል ትምህርት ቤት በመገኘት ገለጻ በመውሰድ ህዳር 14/03/2015 ዓ.ም ከጧቱ 2፡00 ላይ ትምህርት ቤቱ አይሲቲ ትምህርት ክፍል ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
2.ማንኛውም ተማሪ ፎርም ከሞሏ በሗላ በምንም አጋጣሚ መቀየር ስለማይቻል ቀድሞ ከቤተሰብ ጋር በመመካከር ትክክለኛ የዩኒቨርስቲ ምርጫ ከ1-40 ሁሉንም ዩኒቨርስቲ እና ፌልድ መሙላት አለበት፡፡
3.በሚዘጋጀው ቅፅ ላይ ትክክለኛሙሉ ስም ከነ አያት በእንግሊዝኛ Capital Letter መፃፍ
4. Registration Number በትክክል መፃፍ
5.ሁሉንም መረጃዎች ያለ ምንም ስርዝ ድልዝ መፃፍና መጨረሻ ላይ የተማሪው ፊርማ ማስቀመጥ
6.የመሙሊያ ቅፅ ትምህርት ቤቱ ባዘጋጀው ብቻ በመሆኑ ከትምህርት ቤት መውሰድ አለበት
7.በውክልና መረጃ የማይሞላ መሆኑ ይታወቅ።
8.በተባለው ዕለት መጥቶ ዩኒቨርሲቲ እና ፌልድ ያልሞላ ተማሪ ሙሉ ኃላፊነቱን ተማሪ የሚወስድ መሆኑ ይታወቅ ፡፡
ማሳሰቢያ :- ሁሉም ተማሪዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ለምታውቋቸው ጓደኞቻችሁ እና ቤተሰብ እንድታስተላለፉ ትምህርት ቤቱ ያሳውቃል ።
የት/ቤቱን መረጃ በፍጥነት እንዲደርሳችሁ የት/ቤቱን የቴሌግራም ቻናላችንን @hotiepreparatory ይቀላቀላሉ
1.2K views06:09