Get Mystery Box with random crypto!

hotie preparatory

የቴሌግራም ቻናል አርማ hotiepreparatory — hotie preparatory H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hotiepreparatory — hotie preparatory
የሰርጥ አድራሻ: @hotiepreparatory
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.66K

Ratings & Reviews

4.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-05-19 11:15:00 የረሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ማጠናቀቂያ ጊዜ ተገለፀ።
ግንቦት 10/2015 ዓም. (የትምህርት ሚኒስቴር) በ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በልዩ ሁኔታ በሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ ተማሪዎች ፈተናና ተዘጋጅቶ እንዲላክና አጠቃላይ ሂደቱ እስከ ሰኔ 30/2015ዓ.ም ድረስ እንዲጠናቀቅ በትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ተቀምጧል።
ፈተናውም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በተሰጠው ትምህርት መሠረት ከማዕከል በጋራ ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ ተብሏል ።
በዚህም መሰረት በሴሚስተሩ በተሰጠው ትምህርት የተቋማት የውስጥ ፈተና ውጤት 50 ከመቶ እንዲሁም በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና ውጤት 50 ከመቶ ይይዛል ተብሏል።
ተማሪዎችም በ2016 ዓ.ም ትምህርታቸውን ለመከታተል ብቁ ሆነው ለመገኘት የሁለቱ ድምር አማካይ 50 ከመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋልም ተብሏል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ፈተናውን በማስተዳደርና ውጤት በመግለጽ በ2016 የፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን ለይተው እስከ ሰኔ 30/2015ዓም እንዲያጠናቅቁ ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ የ2016 የትምህርት ካሌንደር የተስተካከለ እንዲሆን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
785 views08:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-18 18:50:43 የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቅያ ሀገር አቀፍ ፈተና መስጫ ጊዜ ይፋ ሆነ።
ግንቦት 10/2015 ዓም. (የትምህርት ሚኒስቴር) የትምህርት ሚኒስቴር የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና የሚሰጥበትን ቀን አሳውቋል።
የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 30/2015 ዓ.ም ድረስ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል።
ዩኒቨርሲቲዎችም ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ ከሐምሌ15/2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
769 views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 16:38:32 ማስታወቂያ
04/09/2015ዓ.ም በጉድኝት ደረጃ በተካሄደው የቀለም ትምህርት የጥያቄና መልስ ውድድር
ከ9ኛ ክፍል ደረጃ
ከ10ኛ ክፍል እና ደረጃ
ከ11ኛ ክፍል ተፈጥሮ ሳይንስ እና ደረጃ
ከ11ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ እና ደረጃ
ከ12ኛ ክፍል ተፈጥሮ ሳይንስ እና ደረጃ
ከ12ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ እና ደረጃ ተማሪዎቻችን የወጡ በመሆኑ ግንቦት 19/2015ዓ.ም በከተማ አቀፍ ለሚካሄደው የቀለም ትምህርት የጥያቄና መልስ ውድድር ጉድኝቱን ወክለው ከሚወዳደሩ 6 ተማሪዎች መካከል 5ቱ የት/ቤታችን ተማሪዎች መሆናቸውን እየገለጽን ለዚህ ውጤት መምጣት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጋችሁ መምህራን ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡
ት/ቤቱ
1.2K viewsedited  13:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 17:23:16 የወሎ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጅ ኢኒስቲቲዩት የኮምቦልቻ ካምፓስ ለሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን መሠረታዊ የኮምፒውተር አጠቃቀም በተመለከተ በሁለት ዙር ለአንድ ወር የሚቆይ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡
980 views14:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 19:54:31 ቀን 18/07/2015ዓ.ም
የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከ መጋቢት 20  - ሚያዚያ 15  ይከናወናል።
         ------------------------
የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባ ከ መጋቢት 20  - ሚያዚያ 15,2015ዓ.ም እንደሚከናወን  የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገለፀ።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተናን የሚወስዱ ተማሪዎች ምዝገባን በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል።
መግለጫውን የሰጡት የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) የ2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምዝገባ በበይነ መረብ እንደሚከናወን ገልፀዋል።

መረጃዎችን በትክክል ባለመሙላት ምክንያት የፈተና ሂደት ላይ ችግር እንደሚፈጥር የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ይህንን ለማስቀረት ተማሪዎች መረጃዎቻቸውን በወቅቱ ማስመዝገብ እንዳለባቸውም ተናግረዋል።  
ያልተመዘገበ ተማሪ የ 2015ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን እንደማይፈተንም ዶ/ር እሸቱ ገልፀዋል።

በ 2014ዓ.ም በነበረው የምዝገባ ሂደት የተፈታኞች ምዝገባ መረጃ ጉድለት የነበረበት እንደነበር እና በዚህም ምክንያት የፈተና አሰጣጥ ሂደቱ የተራዘመ እንዲሆን እንዳደረገው በመግለጫው ተነስቷል ።

በመግለጫው ምዝገባው ከ መጋቢት 20 እስከ ሚያዚያ 15/2015ዓ.ም  ድረስ ለመደበኛና የማታ ተማሪዎች በመንግስት የመደበኛ ትምህርት ቤቶች ለ ድጋሜ ተፈታኞች እና የርቀት ትምህርት ተማሪዎች በተመረጡ የወረዳ ትምህርት ጽ/ቤቶች አማካኝነት በበይነ መረብ ብቻ እንደሚያካሂዱ ተገልጿል።

መደበኛ ተመዝጋቢዎች ከ 9-12ኛ ክፍል በተከታታይ ሲማሩ የነበሩ እና በ2015 ዓ.ም  በመማር ላይ ያሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

ተማሪዎች ለምዝገባ ሲመጡም  ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ በመያዝ በአካል ተገኝተው በበይነ መረብ መመዝገብ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።
በመግለጫውም ተማሪዎ፣ ወላጆች ፣ መዝጋቢዎች እና ከመምህራን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ  ጥሪ ቀርቧል።

ፈተናው የሚሰጥበት ቀንን በተመለከተም  ፈተናው በዩኒቨርስቲ ውስጥ እንደሚሰጥና ቀኑ ወደ ፊት የሚገለፅ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር
714 views16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 21:16:48 ቀን 19/6/2015 ዓ.ም
#ማስታወቂያ
የRemedial ፕሮግራም ምደባ ይፋ ሆኗል።
በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከአሁን ሰዓት ጀምሮ ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑንና በተመደባችሁበት የትምህርት ተቋሞች በሚያስተላልፉት ጥሪ መሰረት የ Remedial ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ  እንገልፃለን ።

ማሳሰቢያ :-
የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ ለመግለጽ እንወዳለን።
የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት የቀረቡ አማራጮች
Website:
https://placement.ethernet.edu.et
SMS: 9444
ትምህርት ሚኒስቴር
479 views18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-26 17:56:27 ቀን 19/06/2015ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል Remedial ተማሪዎች በሙሉ
የት/ቤቱን መረጃ በፍጥነት እንዲደርሳችሁ የት/ቤቱን የቴሌግራም ቻናላችንን @hotiepreparatory ይቀላቀላሉ
የመረጃው ምንጭ፡- ትምህርት ሚኒስቴር ነው
533 views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 18:12:40 ቀን 15/06/2015ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለሆጤ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በሙሉ
የ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና የወስዳችሁ ተማሪዎች የፈተና ውጤታችሁ ሪፖርት ካርድ ስለመጣ መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ት/ቤቱ ያሳውቃል፡፡
የት/ቤቱን መረጃ በፍጥነት እንዲደርሳችሁ የት/ቤቱን የቴሌግራም ቻናላችንን @hotiepreparatory ይቀላቀላሉ
383 views15:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 07:20:25 ማስታወቂያ
አቅም ማሻሻያ (Remedial )ፕሮግራም የዩኒቨርሲቲ ምርጫን በተመለከተ
በ 2014 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ምርጫችሁን በየትምህርት ቤታችሁ በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ የካቲት 10/2015 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ማሳሰቢያ:- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፣ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ና የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲዎች በዚህ ፕሮግራም የማይካተቱ መሆኑን እንገልጻለን።
ትምህርት ሚኒስቴር!
411 views04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 13:53:34
#የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች እና በተለያዩ አማራጮች ለመከታተል የመቁረጫ ነጥብ ማሳወቂያ

የትምህርት ሚኒስቴር በ2014 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና  ወስደው 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያመጡትን ከግምት ውስጥ በማስገባት እና በተመሳሳይ ሁኔታ ፈተናው የተሰጠበትን አግባብ እና ሌሎች ጉዳዮችን ከግምት በመውሰድ ለአንድ ጊዜ ብቻ  የሚያገለግል የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) እንዲተገበር መወሰኑ ይታወቃል።

በዚሁ መሰረት በ2015 የትምህርት ዘመን ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው በ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉ ተማሪዎችን አነስተኛ የመግቢያ ውጤት መወሰን አስፈላጊ በመሆኑ 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ ያላስመዘገቡ ነገር ግን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የሚያሟሉ ተማሪዎች የ Remedial ፕሮግራም ተጠቃሚዎች ይሆናሉ ።

1. በሁሉም አማራጮች (በግል እና በመንግስት ተቋማት) የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል ተማሪዎች እንደተፈተኑት የትምህርት አይነት ብዛት 30% ከመቶ እና ከዚያ በላይ ማለትም (210 ከ 700፣  180 ከ 600 እና 150 ከ 500) የተቆረጠ መሆኑን።

2. ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ  በመንግስት ተቋማት(ወጪያቸው በመንግስት ተሸፍኖ) የ Remedial ፕሮግራም የሚከታተሉት የሚከተሉትን መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ ብቻ ይሆናል።

MOE
381 views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ