Get Mystery Box with random crypto!

ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች ሰላም ጤና እድገት ብልፅግና በያላችሁ | መርጌታ አለምአየሁ

ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች
ሰላም
ጤና
እድገት
ብልፅግና በያላችሁበት ተመኘሁ

በቅንነት ሸር እናድርግ

ዛሬ ሌባ ገትር ወይም የሌባ መመለሻ የረቀቀ የአባቶች ሚስጥር ላጋራችሁ ወደድኩ

ሌባ ወይም ወንበዴ ሽፍታ የለፋንበትን የደከምንበትን ሀብትና ንብረታችን ( ገንዘባችን ) ሳይደክም ሳይለፋ ብርሃንንና ጨለማን ተገን በማድረግ እየዘረፈንና እየሰረቀን ይኖራል ከዚያም ሲያልፍ በህይወታች ላይ አዳጋን ሲፈጥር ይኖራል።

ታዲያ ይህን ዘራፊ ሌባ ለማገድ ቀደምት አባቶቻችን የተለያዩ ሚስጥሮችን በመጠቀም ሊሰርቅ የመጣው ሌባ ከግቢ ውጭ ሲዞር ሲንከራተት አድሮ እንዲመለስና አጥር ዘሎ ከገባም አንድም ንብረት ሳያነሳ ቁሞ ወይም ተገትሮ እንዲገኝ ያደርጉታል ።

ታዲያ ይህን ሚስጥር ስንቶቻችን እንሆን የምናውቀው ?
የችግሩ ሰለባ የሆናችህና መስራት የቻላችሁ ትጠቀሙበት ዘንድ እንሆ ጥበቡን አቀረብኩላችሁ።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ጸሎት በእንተ ሌባ ማሽን ወቤት ተኳሽ በስመ አብ ግዝዎን ፫ ጊዜ በስመ ወልድ ግዝዎን ፫ ጊዜ በስመ መንፈስ ቅዱስ ግዝዎን ፫

ራፎን ፫ ራኮን ፫ ጋዴዎን ፫ ሂሰዎቴን ፫ ኤሮን ፫ ፍሎን ፫ ብርስባሕልዮን ፫ ባንድ ክንድ ተስንዝር ፫ ያምን ሐሐይን ፫ ሐይን ፫ መድፍን ድፍን ፫ ልቦሙ

በኃይለ እሉ አስማቲከ ሕትም አፉሆሙ ወእፁ ጉርዔሆሙ ወአጽልም አዕይንቲሆሙ ወእሥር እደዊሆሙ ወእገሪሆሙ ለሌባ ወለቤት ተኳሽ ከመ ኢይስርቁ ንዋይየ ወኩሎሙ ዘሃሎ ውስተ ቤትየ ወኢይባዕ ውስተ ቤትየ ወቅጽርየ ሀበ ሃሎኩ አነ ገብርከ እገሌ

ገቢር ( አሰራር )

በስሚዛ ( ሰለሰላ ) እንጨት እንደ ብዕር መፃፊያ ቀርፆ ሰባቱ ቀለማት በጥብጦ አሣ በላሰው ድንጋይ ( አሳ ያለበት ባህር ውስጥ ባለ ድንጋይ )ላይ ጽፎ የተፃፈውን ድንጋይ ቤቱን ወደግራ ፫ ግዜ አዙሮ በመግቢያው በር መቅበር ነው።

ይህ የተፈተነ ሌባ ገትር የሊቃውንት አባቶቻችን ጥበብ ነው ሰርቶ ማየት ማመን ነው።

በቤትዎ ሁነው ጥበብን ይማሩ ዕውቀትን ይሸምቱ

የቀደምት ኢትዮጵያውያን አባቶችና ቅደመ አያቶቻችን የጥበብ ሥራ የሀገር በቀል እፅዋትና የጠልሰም ሥራ ጥቅማቸው በግልጽ ይብራራል

0912999705
በስራ ሰዓት ይደውሉ