Get Mystery Box with random crypto!

ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች ሰላም ጤና እድገት ብልፅግና በያላች | መርጌታ አለምአየሁ

ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች
ሰላም
ጤና
እድገት
ብልፅግና በያላችሁበት በሀገራችን ኢትዮጵያና በዓለም ሁሉ ላላችሁ ሕዝቦች በሙሉ ተመኘሁላችሁ ።

ዛሬ የብዙቻችሁ ጥያቄ ስለሆነው የግራዋ ትክል በተወሰነ መልኩ ላብራራላችሁ

#ግራዋ ከመካከለኛ ዛፍ የሚመደብ እረጅም ቁመትና ሰፋ ሰፋ ያለ ቅጠል ያለው ዛፍ ሲሆን ከመካከለኛ ዛፍ ይመደባል ።
እንጨቱ ጠንካራ ቅጠሉ መራራና ሸካራ ሲሆን መገኛውም ፦
በብዛት በወይና ደጋና በደጋማው አካባቢ ነው ።
የግራዋ ጥቅሙ።

፩. #ለመፍትሔ ሥራይ ወይም ሰው መተት ሲደረግበት ቤቱ ሲረጭ የግራዋ ቀንበጥ ቀንበጡን ቆርጦ ጭቅጭቆ ሰባት የሎሚ ፍሬ ክትፎ ጨምሮ ሀሉቱን ቢገኝ በመራራ ቅል ካልተገኘ በንፁህ እቃ በእለት ውሀ ዘፍዝፎ ፯ ( 7) ቀን ቤቱን ወይም ግቢውን ቢረጩት የተመተተውን መተት ይፈታዋል።
፪. #ለማንኛም የመፍትሔ ሥራይ ቅመማ ከሌሎች እፅዋት ጋር ማንገሻ ሁኖ ይገባል ይቀመማል።

፫. #ለሆድ ቁርጠት አምስት ወይም አራት ለጋ ቅጠል ቆርጦ ጭቅጭቆ በውሀ አሽቶ ጨምቆ አንድ ስኒ ቢጠጡት የሆድ በሽታ ያድናል ።

፬. #ለወባ በሽታ እንዲሁ ቅጠሉን ጨቅጭቆ በእለት ውሀ አጥሎ አንድ ስኒ ቢጠጡት ወባን ፈፅሞ ያድናል መራራ ስለሆነ አባሮ መጠጣ ።
፭. #ለታይፎድ
፮. #ለአሜባ
፯. #ለሆድ ትላትል
፰. #ለጃርዲያ
እንዲሁ እንደ ላይኛው ። (2 . 3) አሰራር መጠቀም።

፱. #ተቀፅላውን ቆርጦ መሬት ሳያስነኩ ከትክል ድንጋይ ላይ ቀጥቅጦ ለ ፯ ቀን ቢታጠኑት አይነ ጥላ ያስለቅቃል ።
ለህልመ ሌሊት የግራዋ ተቀፅላውን ከርክሞ ከትቦ ቢይዙት ህልም ሌሊት አይመታም።

፲. #ለግፊትና
ለስኳርም ያገለግላል ነገር ግን ለእነዚህ ለሁለቱ ግን ባለሙያ ቢቀምመው የተሻለነው።

፲፩. #እንዲሁም በገጠር እናቶች ጌሾ በሌለበት ቦታ እንደጌሾ ተጠቅመው ጠላ ይጠምቁበታል ለጠላ መጥመቂያ ያገለግላል።
ግራዋ ከዚህም በተጨማሪ ለተያዩ የመድኃኒት ቅመማዎች ይውላል።

ጥበብ_ታላቋን_ታከብራለች
09 12 99 97 05
በስራ ሰዓት ይደውሉ