Get Mystery Box with random crypto!

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን።” / 1ኛ | ሕያው ቃል

“ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን።” / 1ኛ ዮሐንስ 1፥7/

ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ማድረግ ማለት እርሱ ማወቅ ፣ማፍቀርና ልጁ መሆን ማለት ነው ። ከእርሱ ጋር እውነተኛ ኅብረት ካለን በብርሃን እንኖራልን ። በጨለማና በኃጢአት የሚኖር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት የላቸውም ። ከእግዚአብሔር ኅብረት አለን ብለው ነገር ግን በኃጢአት ውስጥ ከተመላለሱ የሚኖሩትም በእውነት አይደለም ሐሰተኞች ናቸው ።እውነት የምንናገረው ብቻ ሳይሆን የምናደርገውና የምንኖረው ነው ። ሰለዚህም በእውነት መኖር አለብን ። በእውነትና በመንፈስ እግዚአብሔርን ማምለክ አለብን ። (የሐ 4:23) ። እውነት የሕይወት መንገድ ነው ። በእወነት ከኖርን ማለትም ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ካለን ሁለት ነገሮች ይሆናሉ ። በመጀመሪያ እርሱ በእርሳችን አንድነት ይኖረናል በሁለተኛ ደረጃ የልጁ የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል ። “ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ ለእያንዳንዳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።” /1ኛ ዮሐንስ 1፥7/ ።

Facebook: https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid035mrCdvJhbekf2HguvxTX8L1MgXrHBPACkJVoxsc4wgayHqWiyjbz4ARLxjSnRfYjl/?app=fbl :Telgram: https://t.me/Hiyaw_qal
Telgram: https://t.me/ortohodox_new_mezmur