Get Mystery Box with random crypto!

“ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን ። — ሮሜ 12፥9 በክርስትና ሕይወት ውስጥ የመጀመሪያው ትል | ሕያው ቃል

“ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን ።
— ሮሜ 12፥9

በክርስትና ሕይወት ውስጥ የመጀመሪያው ትልቁ መመርያ ፍቅር ነው ። “ፍቅር የሌለው እግዚአብሔርን አያውቅም፥ እግዚአብሔር ፍቅር ነውና ይላል ።ለለ መጸሐፍ ቅዱስ ፍቅራችሁ እውነተኛ ይሁን ይለናል ። ይህ እውነተኛ ፍቅር የሚመነጨው ከውስጣዊ ሰውነታችን ማለትም ከመንፈሳችን ነው ። ፍቅራችን ውጪዊ ከሆነ የሐሰት የግብዝነት ፍቅር ይሆናል ። ነገር ግን ይህ ፍቅር አይቆይም ። ፍቅሩ ሐሰተኛና ግብዝ የሆነ ሰው የራሱን ጥቅምና ምቾት ብቻ ነው የሚፈልገው ። ግን ፍቅሩ እውነተኛ የሆነ ሰው የእግዚአብሔር ጥቅምና የሌሎችን ምቾት ነው የሚፈልገው ። ፍቅር ይታገሣል፥ ፍቅር ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር በራሱ አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም ለስው ነወ የሚኖረው ፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። ይህ ነው እውነተኛ ፍቅር

Facebook: https://www.facebook.com/103351765227313/posts/pfbid035mrCdvJhbekf2HguvxTX8L1MgXrHBPACkJVoxsc4wgayHqWiyjbz4ARLxjSnRfYjl/?app=fbl :Telgram: https://t.me/Hiyaw_qal
Telgram: https://t.me/ortohodox_new_mezmur