Get Mystery Box with random crypto!

ቡሄ ለምን እናከብራለን ? በደብረ ታቦር ያበራው ኢየሱስ የሙሴም የኤልያስም ጌታ ነው። አብ ከሰማ | ሕያው ቃል

ቡሄ ለምን እናከብራለን ?

በደብረ ታቦር ያበራው ኢየሱስ የሙሴም የኤልያስም ጌታ ነው። አብ ከሰማይ "እርሱን ስሙት" ያለው ኢየሱስ የአዲስ ኪዳን ቃል እና ሕይወት እርሱ ብቻ ስለሆነ ነው። ሰው ኢየሱስን ከሙሴ እና ከኤልያስ ጋር ቢያመሳስሉትም ኢየሱስ ግን እኩያ የሌለው የአብ አንድያ ልጅ እና አምላክ ነው። ሙሴም ኤልያስም ሕይወት አልሰጡም አላሰጡምም። ነገር ግን በሰዎች ልብ ውስጥ ከእግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ እኩል ክብር ነበራቸው። እግዚአብሔር አብ ደግሞ ኢየሱስን አልቆ ማሳየት ፈለገ። በሰማይም ሆኖ ሙሴና ኤልያስ በተገኙበት ሊሰማ የሚገባው አሁን ተራው የኢየሱስ መሆኑን "እርሱን ስሙት" በሚል ግርማ ያለው ቃል ከሰማይ አሰማ። ሐዋርያትም ይሄን ከሰሙ በኋላ ትኩረታቸውን ሙሉ በሙሉ ኢየሱስ ላይ አደረጉ። ጌታም ሞቶ እስኪነሳ ድረስ ያዩትን ነገር ለማንም እንዳይናገሩ አስጠነቀቃቸው። ምክንያቱም ኢየሱስ ከኤልያስም ከሙሴም እንደሚበልጥ ከተሰማ ክርስቶስ አይሰቀልም ምክንያቱም ኢየሱስ አምላክ መሆኑን ካወቁ አይገድሉትምና። ጌታ ግን ሞቶ የማዳን ስራውን መፈጸም እንዳለወት ያውቃል። ሞቶ በደሙ መፍሰስ እኛ መዳን አለብን ምክንያቱም ደም ካልፈሰሰ የኃጢያት ስረየት የለምና "ዕብ 9፡22"።

ጌታ ሞቶ ከተነሳ በኋላ (ድነትን ከፈጸመ በኋላ) ግን ሐዋርያት ያዩትን እና ከአብ የሰሙትን ማሰማት ጀመሩ። ይህ የአብ አላማ አለምን በክርስቶስ ለመጠቅለል ከማሰቡ ጋር (ኤፌ 1፡10) አንድ ነው። ምክንያቱም ኢየሱስ ከዚህ በፊት እንደተላኩት ነብያቶች አይደለም። ያለማንም አጋዥነት ብቻውን ሊያድን እና ወደ አብ የሚያቀርብ ደግሞ የአብን ኃሳብ እንከን በሌለበት አሰራር ፈጽሞ አብን ያስደሰት እና ሊያስደስት የመጣ ብቸኛ አዳኝ ስለሆነ በእርሱ የሚያምኑትን ፈጽሞ ስለሚያድናቸው ይህን አደረገ።

https://t.me/Hiyaw_qal