Get Mystery Box with random crypto!

History of islamic

የቴሌግራም ቻናል አርማ historyofislam2 — History of islamic H
የቴሌግራም ቻናል አርማ historyofislam2 — History of islamic
የሰርጥ አድራሻ: @historyofislam2
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.21K
የሰርጥ መግለጫ

👉ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)
👉 ቁርአንና የቁርአን ተፍሲር እንድሁም ነብያዊ ሀድሶች
👉ኢስላማዊ ታሪኮች የነብያት የሱሀቦች የሰለፎች የሀገራት የታላላቅ ዳኢዎች ቃሪወች ሌሎችም ታሪኮች ይቀርባሉ ። 👉 እንድሁም ኪታቦች ይቀርባሉ አስተያየት (Comment)በ @Abureyaan ፃፉልን #channel_crate_june20_2018

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-06-26 20:56:36 #_የነብያት_ታሪክ

#_ነብዩሏህ_ዳውድ_ዐለይሂ_ሰላም


...በዚህ መሀል ነበር የዚህ ታሪክ ባለቤት እና የበጎች እረኛ የሆነው ዳዉድ ኢብን
ኢሻ ኢብን ዑወይድ ኢብን ዓቢር ኢብን ሰልሙን ኢብን ናህሹን ኢብን
ዑወይናዚብ ኢብን ኢረም ኢብን ሀስሩን ኢብን ፋሪስ ኢብን የሁዳ ኢብን
ያዕቁብ ኢብን ኢስሀቅ ኢብም ኢብራሂም......ሰልፉን እየሰነጠቀ ወደ ጃሉት
ወጣ።ይሁን እንጂ ንግስናንም ሆነ የጣሉትን ልጅ ማግባት ፈልጎ አይደለም።
እስራኢላውያንም ይሄ ደካማ እረኛ ምንም አይነት ጦርም ይሁን ጋሻ ሳይዝ ያን
ተራራ ሚያህል ሰውዬ ሊገጥም ሲወጣ በግርምት ይመለከቱት ነበር።
ዳዉድ እረኞች የሚይዙትን በትር በአንድ እጁ ይዞ በሌላው እጆ ድንጋይ
ይዟል።ጃሉት ለፍልሚያ የቆመበትን ቦታ ዳዉድ ልክ እንደደረሰ ፊት ለፊቱ ቆመ።
ጃሉት ይህን ልጅ እግር እረኛ ሲመለከት እያሾፈ፦"አንተ ልጅ ሞትን ፈልገኸው
ትመጣለህ እንዴ!!! በል ሂድ'ና ከወታደሮቹ እኔን የሚገጥም ትልቅ ሰው
ጥራ።እኔ አንተን ልገድልህ አልፈልግም" አለው።
ዳዉድም፦"እኔ ግን አንተን መግደል እፈልጋለሁ" አለው።
ጃሉትም፦"እሺ ጦርህ፣ ሰይፍህ፣ ጋሻህ፣ ቀስትህ....የታለ? በምንድነው
ምትጋደለው? አለው።
ዳዉድም፦"የኔ ጦር ኢማን ነው።የምጋደልህም በአላህ ስም ነው" አለው።
ይህን ሲሰማ ጃሉት ቁጣ ገነፈለ።ዳዉድንም ሊገድለው ሰይፉን ገትሮ
እየተንደረደረ ሲመጣ፤ዳዉድም ዋዛ አልነበረም'ና በያዘው ድንጋይ አልሞ
ጭንቅላቱን በተነለት።ጃሉትም በዚያች ምት ወድቁ ሞተ።
ጦርነቱም ተጀመረ...ብዙ ከተፋለሙ በኋላም እስራኢላውያን በአላህ ፍቃድ
የጦርነቱን ድል ተቀዳጁ።
ጦነቱ በኢስራኢላውያን አሸናፊነት ሲጠናቀቅ ኢስራኢላውያኑ የቀድሞዋን
ሀገራቸውን ፊለስጢንን ዳግም ሄደው በድል ገቡባት።የጃሉትን ገዳይ የሆነውን
ዳዉድንም ንጉስ አድርገው ሾሙት።
ዳዉድ ምንም እንኳም ንጉስ ቢሆንም በዙፋኑ ቁጭ ብሎ ሳይሆን በእጁ
የሰራውን እና የላቡን ነበር የሚበላው።
ዳዉድ አላህን ሲያወድስ ድምፁ እጅጉን ይማርካል። አላህም ለሱ ዘቡር
የተባለን መፅሀፍ አውርዶለት ነበር።
ዳዉድ ዘቡርን ሲቀራ ድምፁ ከማማሩ የተነሳ፦
፦ተራራዎች አብረውት አላህን ያወድሱ ነበር።
፦ወፎችም አብረውት አላህን ያወድሱ ነበር።
፦የሰዎችም ልብ ይንሰፈሰፍ ነበር።
ዳዉድ ዘቡርን እየቀራ ሲያዜም ጂኖች፣ ሰዎች፣ ወፎች፣ እንስሳቶች በድምፁ
ተማርከው እራሳቸውን በመሳት በረሀብ ይሞቱ ነበር።
ከእለታት አንድ ቀን ዳዉድ በሚህራቡ(ግላዊ የአምልኮ ቦታ) ገብቶ
ወታደሮቹን፦" ማንም ሊገባ እንዳትፈቅዱ" ብሎ በሩን ዘጋ።በዚህ ሁኔታ ላይ
ጌታውን እያመለከ ሳለ ሁለት ሰዎችን ሚህራብ ውስጥ ቆመው
ተመለከታቸው።በሩን ሲያይ በሩ ዝግ ነው....ሰዎቹ ከየት እንደመጡ ግራ
በመጋባት ሲመለከታቸው ሁለቱ ሰዎችም ጠጋ ብለው፦"ዳዉድ ሆይ! አትፍራ።
እኛ ተካሰን እንድትፈርደን ነው የመጣነው።ይህ ወንድሜ 99 በጎች ሲኖሩት ለኔ
ደግሞ 1 በግ ናት ያለችኝ። እሷን ስጠኝ'ና መቶ ሙላልኝ ብሎ እያስገደደኝ
ነው" በማለት አንደኛው አስረዳው።
ዳዉድም የተከሳሹን ቃል ሳይሰማ፦"አይ!! ይሄ እንኳን አንዷን በግህን ስጠኝ
ብሎ በማስገደዱ በርግጥ በድሎሀል" አለው።
ይሄን ግዜ ሁለቱም ሰዎች ተሰወሩ።ዳዉድም አላህ የሁለት ተካሳሾችን ቃል
ሳይሰማ መፍረድ እንደሌለበት ሊያስተምረው መሆኑን በመረዳት ሱጁድ አድርጎ
አላህን ይቅርታ ጠየቀው።
አላህ ለዳዉድ ሱለይማን የተባለን ብልህ እና ሳሊህ ልጅ ረዝቆት ነበር'ና
ከእለታት አንድ ቀን ዳዉድ ልጁን ከጎኑ አስቀምጦ ፍርድ ችሎት ላይ ሳለ ሁለት
ሰዎች መጡ።
ከሳሹ፦"የዚህ ሰውዬ በጎች ማሳዬን ገብተው ያለውን አታክልት በሙሉ
አወደሙብኝ" ብሎ ክሱን አቀረበ።
ዳዉድም ወደተከሳሹ በመዞር፦"ከሳሽህ የሚለው ትክክል ነውን?" በማለት
ጠየቀው።
ተከሳሹም፦"አዎን" ብሎ መለሰለት።
ዳዉድም ከሳሹ በወደመበት ማሳ ምትክ የተከሳሹን በጎች እንዲወስድ ፈረደ።
ይህን ሲከታተል የነበረውም የዳዉድ ልጅ ሱለይማን፦"አባቴ አንድ ግዜ
እንድናገር ፍቀድልኝ" አለው። ዳዉድም ፈቀደለት....
ሱለይማንም፦"እኔ ለየት ያለ ፍርድ አለኝ...እሱም የበጎቹ ባለቤት የከሳሹን
ማሳ ያልማለት። የማሳው ባለቤት ደግሞ ማሳው እስኪለማለት ድረስ
በተከሳሽ በጎች ይጠቀም። የበጎቹ ባለቤት ማሳውን አልምቶ ሲጨርስ
ለማሳው ባለቤት በማስረከብ በጎቹን ከከሳሹ መልሶ ይውሰድ" በማለት
ተናገረ።
ዳዉድም፦"ይህ ጥበባዊ ፍርድ ነው።ጥበብን የሰጠህ ጌታ ምስጋና ይገባው"
አለ
(አደራ ሲረዝም እንዳትሰላቹ።በክፍል እየከፋፈልኩ ከማደነጋግራችሁ በነካ
እጃችሁ ጨርሷት ብዬ ነው።አይሰለቻችሁም አይደል!!!")
ዳዉድ በተፈጥሮው ትንሽ ሲሪየስ ነገር ነው፤ከቤት ሲወጣ ማንም ቤት
እንዳይገባ ሚስቱ ላይ ዘግቶ ነበር የሚወጣው።
ከእለታት አንድ ቀን ዳዉድ እንደልማዱ ቤቱን ዘግቶ ወጣ።ሚስቱም ዝም ብላ
እቤቱን እየተዟዟረች ሳለ አንድ ሰውዬ እቤቱ መሀል ላይ ፀጥ ብሎ ቆሞ
ተመለከተችው'ና፦"አንተ ማን ነህ? ቤት በኩል ገብተህ ነው? ወላሂ ዛሬ ዳዉድ
ይምጣ እና አዋርድሀለሁ" አለችው።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ዳዉድ እቤቱን ከፍቶ ገባ።ሰውዬው ግን ንቅንቅ
አላለም...ዳዉድም በቁጣ፦"ማን ነህ?" አለው።
ሰውዬውም፦"እኔ ያ ንጉሱችን የማልፈራ...ያ ግርዶሾችም የማያግዱኝ የሆንኩ
ነኝ" አለው።
ዳዉድም፦"አሀ...መለከል መውት ነሃ !! እንኳን ደህና መጣህ የአላህ
መልዐክ" ብሎ ከተቀበለው በኋላ ዳዉድ በተወለደ በ100 አመቱ በእለተ
ቅዳሜ ከሟች ነቢያት ነፍሱ ተቀላቀለች።
ማታውን ጀናዛው ታጥቦ ካደረ በኋላ በነጋታው ለቀብር ብዙ ህዝብ
ተሰበሰበ።ያን ቀን 40.000 (አርባ ሺህ) ባህታዊያንም በቀብሩ ስነ ስርዐት ላይ
ተገኝተዋል።
ህዝቡ ቀብር ቦታ ላይ ሳለ ከፍተኛ የፀሀይ ሀሩር መውረድ ሲጀምር ሱለይማን
ዘንድ ሄደው፦"ፀሀዩን አልቻልንም አንድ ነገር አድርግ" አሉት።
ሱለይማንም አዕዋፍን ሁሉ ጠርቶ ህዝቡን ከፀሀይ እንዲያስጠልሉ አዘዛቸው'ና
በጣም ብዙ ቁጥር ያላቸው አዕዋፍ መጥተው ሰማዩን እንዳይታይ አድርገው
ህዋ ላይ በመንሳፈፍ ሞሉት።
ወፎቹ ህዝቡን ለማስጠለል ሰማዩን ሙሉ በሙሉ ሲከልሉት ሰው ትንፋሽ
ያጥረው ጀመር።
አሁንም ሰዉ መላ በለን ብለው ሱለይማንን ሲያናግሩት ሱለይማንም ወፎችን
ፀሀይዋ ካለችበት አቅጣጫ ብቻ እንዲሆኑ አዘዛቸው።
በዚህ ሁኔታ ነበር እንግዲህ የዳዉድ ቀብር ስነስርዐት የተፈፀመው።
(የአላህ ሰላም እና እዝነት #በዳዉድ ላይ ይሁን።)
___
ምንጮች፦
ﺍﻟﻘﺮﺀﺍﻥ ﺍﻟﻜﺮﻳﻢ
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ / ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ/
ﻗﺼﺺ ﺍﻻﻧﺒﻴﺎﺀ ﻟﻠﺸﻴﺦ ﺍﻟﺸﻌﺮﺍﻭﻯ
ﻗﺼﺺ ﺍﻷﻧﺒﻴﺎﺀ ﻟﻺﻣﺎﻡ ﺍﻟﺤﺎﻓﻆ ﺍﺑﻦ ﻛﺜﻴﺮ
__
#_የነብዩሏህ_ሱለይማን_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ
__
ኢንሽዓሏህ
ይ.......ቀ.....ጥ.......ላ.......ል፡፡
1.1K viewsمصباح, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 20:47:46 ቁርዓን ተፍሲር
#سورة_النحل 12
ሱረቱ An-Nahl
#ክፍል_12 አቡ ኒብራስ
@historyofislam2
1.3K viewsمصباح, 17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-20 03:57:38 #_የነብያት_ታሪክ

#_ነቢዩሏህ_ዳዉድ_ዐለይሂ_ሰላም


ሙሳ አለይሂሰላም ከሞተ በኋላ ኢስራኢላውያን ለረጅም አመታት በፊለስጢን ምድር
በሰላም በመኖር ላይ ሳሉ ክህደታቸው እና ጥጋባቸው አፍንጫቸው ላይ
ወጥቶ አላህን ማምለክ አሻፈረን አሉ።
ይህን ግዜ አላህም ጨካኝ እና ጉልበተኛ የሆኑ ህዝቦችን ልኮባቸው እነዚያም
ጨካኞቹ ህዝቦች ፊለስጢንን በመውረር ኢስራኢላውያንን ከሀገራቸው ወደ
በረሀ አባረሯቸው።
በዚህም ሁኔታ ኢስራኢላውያን የማይቻለውን እና ያልለመዱትን የበረሀ
እንግልት ለረጅም አመታት ተጋፈጡት።ይህ ሁሉ ሲሆን በመሀከላቸው አንድ
ስሙ በታሪክ መዛግብት ያልሰፈረ ነቢይ አለ።
(ነቢታቶች ቁጥራቸው 124,000 አንድ መቶ ሀያ አራት ሺህ ናቸው።ከነዚያ
ውስጥ ለኛ የተጠቀሱልን 25 ብቻ ናቸው። ለዚያ ይህ አሁን ያልኩት ነቢይ
ስማቸው ካልተጠቀሱልን ነቢያት አንዱ ነው።)
ኢስራኢላውያን የበረሀው እንግልት አላስችል ሲላቸው እዚህ ነብይ ዘንድ
በመምጣት፦"ተበዳዮች አይደለንምን?" አሉት።
ነቢያቸውም፦"ናችሁ" አላቸው።
እነሱም፦"ከቤቶቻችን አልተፈናቀልንምን?" አሉት።
ነቢያቸውም፦"ተፈናቅላችኋላ" አላቸው።
እነሱም፦"ለዚህ እንግልት ሁሉ የዳረገንን የበደለንን እና ያሰቃየንን
ሀገራችንንም የወረራትን ጃሉት የተባለውን ንጉስ መዋጋት እንፈልጋለን።ስለዚህ
አንተም የጦር መሪ ሹምልን'ና ጃሉትን እንዋጋው" አሉት።
ነቢያቸውም ባህሪያቸውን ስለሚያውቅ፦"ለመዋጋት ዝግጁ መሆናችሁን
እርግጠኞች ናችሁ?" አላቸው።
እነሱም፦"ከሀገራችን ተሰደን...ከቤቶቻችን ተፈናቅለን....ልጆቻችንን ይዘን
በረሀ ለበረሀ እየተንገላታን እንዴት ለጦርነት ዝግጁ አንሆንም !!!" አሉት።
ነቢያቸውም በወረደለት ዋህይ መሰረት፦"አላህ ከመሀከላችሁ ጣሉትን የጦር
መሪ አርጎ ሾሞላችኋል" አላቸው።(ጣሉት ወጣት እና ደሀ ልጅ ቢሆንም ግን
ጠንካራ እና ብልህ ነበር።የጣሉት የዘር ሀረግም ከቢንያሚን ነው
የሚመዘዘው)
ይን ሲሰሙ፦"እንዴ !!! ለምንድነው ጣሉት የጦር መሪያችን የሚሆነው? እሱ
እኮ ድሀ ነው በዚያ ላይ መሪዎች ከሚወለዱበት ቤተሰብም አይደለም" አሉ።
(የየሁዳን ቤተሰብ ፈልገው ነው)
ነቢያቸውም፦"አላህ ጣሉትን በብልህነቱ እና በጉልበቱ ክናንተ ውስጥ
መርጦታል" አላቸው።
እነሱም፦" እሺ ተአምር ያምጣልን" አሉ።
ነቢያቸውም፦"የሱ ተአምር አንድ ሳጥን ከሰማይ መላዕክት ተሸክመው
ይመጣሉ።በዚያ ሳጥን ውስጥም የሙሳ እና የሀሩን ውርስ እና የልብ እርጋታም
አለበት" አላቸው።
እነሱም፦"እንዴት" አሉ።
ነቢያቸውም፦"እሱን ሳጥን ለመመልከት ተራራ ላይ ውጡ" አላቸው።
እነሱም ምንም ሳይዋጥላቸው ለግዳቸው ያን ሳጥን ለማየት፦"ምን አይነት
ሳጥን ነው !!!" እየተባባሉ ተራራው ላይ ወጡ።
ተራራው ላይ ወጥተው ያን የተባለውን የውርስ ሳጥን በመጠባበቅ ላይ ሳሉ
መላዕክት በኑር አሸብርቀው ሳጥኑን ይዘው ህዋእ ላይ ተንሳፈፉ።
እስራኢላውያኑ በአግራሞት ይመለከቱም ነበር።በመጨረሻም መላዕክት
እርጋታ በተሞላበት መልኩ ቀስ አድርገው ሳጥኑን በዚያ ነብይ ፊትለፊቱ
አስቀመጡት።ልክ ሳጥኑ መሬት አርፎ እስራኢላውያን ሲመለከቱት ልባቸው
እርጋታ ተሰማቸው፣ኢማናቸውም ጨመረላቸው።
በዚህ ሁኔታ ኢስራኢላውያን በጣሉት መሪነት ተስማሙ።ነገር ግን ጦር ሜዳ
ለመውጣት ሁሉም ፍቃደኛ አልሆነም'ና የተወሰኑት ቀርተው፤ሌሎቻቸው
በጣሉት መሪነት ጉዞ ጀመሩ።
በጉዞዋቸውም ላይ ጣሉት አስቆማቸው'ና፦"አላህ አንድን ወንዝ ፊትለፊታችሁ
ላይ ለፈተና ያመጣባችኋል።ስለሆነም አፋችሁን ለማርጠብ ትንሽ ተጎንጩ
እንጁ እንዳትጠጡ።ከጠጣችሁም ከኔ አይደላችሁም" አላቸው።
ያን ግዜ በርካታው የወታደር ክፍል ውሀውን ድርግም አድርጎ በመጠጣት
ከመሪያቸው ጣሉት ሲለይ፤ የጣሉትን(የመሪያቸውን) ትዕዛዝ በማክበር
ውሀውን ሳይጠጡ የቀሩትም ሶስት መቶ አስራ ምናምን ብቻ ነበሩ።
ከዚያም ወደ ጦር ሜዳው ሲቃረቡ የጠላቶቻቸው ቁጥር እጅግ አዳጋች
ነበር።ይህን ሲያዩ አንዳንድ የኢማን ደካማዎች፦"ይሄን ሁሉ ወታደር እንዴት
ነው የምናሸንፈው" በማለት ድክመታቸውን ማውራት ሲጀምሩ ሙእሚኖቹም
ድል ከአላህ መሆኑን መከሩ።
አሁን ሁለቱም የጦር ቡድኖች ሰልፋቸውን ይዘው ቆመዋል።ጃሉት የጠላቶችን
ሰራዊት ሲመራ ጣሉት ደግሞ የሙእሚኖችን ሰራዊት ይመራል።
ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ጃሉት የብረት ልብስ ለብሶ ከሰራዊቱ ወጣ
በማለት፦"ማን ነው ከኔ ጋር የሚገጥመኝ?" ሲል ተጣራ።(ጃሉት በጣም ግዙፍ
እና ጉልበተኛ የጦር መሪ ነው።ማንም አይደፍረውም....)
ይህን ግዜ ሁሉም በጣም ፈሩ፣እኔ ብሎ እሱን ሊታገል የሚወጣ ወንድ
ጠፋ።ሁሉም እርስ በርስ ይተያያል።የሙእሚኖቹ ጦር መሪ የሆነው
ጣሉት፦"ይሄን ጃሉትን ወጥቶ የተፋለመ ልጄን እድረዋለሁ።የኢስራኢላውያ
ንም ንጉስ ይሆናል" አለ።
በዚህ መሀል ነበር የዚህ ታሪክ ባለቤት እና
የበጎች እረኛ የሆነው #ዳዉድ_ኢብን_ኢሻ_ኢብን_ዑወይድ_ኢብን.......

ኢንሽዓሏህ
ይ........ቀ........ጥ........ላ........ል፡፡

@historyofislam2
@historyofislam2
1.2K viewsمصباح, 00:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 12:02:36 በቀጣይ የነብዩላህ ዳውድ አለይሂሰላም ታሪክ ይቀርባል ኢንሻአላህ
1.1K viewsمصباح, 09:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 12:01:41 ቁርዓን ተፍሲር
#سورة_النحل 11
ሱረቱ An-Nahl
#ክፍል_11 አቡ ኒብራስ
@historyofislam2
1.0K viewsمصباح, 09:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 21:18:22 #የነብያት_ታሪክ

#_ሙሳ_ዐለይሂ_ሰላም
          #_የመጨረሻዉ_ክፍል



ዩሹዕም የሙሳን ቀሚስ ይዞ ሲመለስ ህዝቡ አይቶት፦"አንተ የአላህን ነቢይ ገድለህ ነው እንዴ ልብሱን ይዘህ የመጣኸው" በማለት ዩሹዕን እራሱን ሊገድሉት ፈለጉ።
ዩሹዕም፦"እኔ አልገደልኩትም። ንፋስ ሲመጣ በርሱ ልከለል ቀሚሱን ስይዘው ሙሳ ቀሚሱን ትቶ ተሰወረብኝ።አናምንህም ካላችሁኝ ሶስት ቀን ከሀገር አስወጡኝ" አላቸው።
እነሱም ከጠባቂዎች ጋር ከሀገር አስወጡት።አላህም ዩሹዕ ሙሳን እንዳልገደለው በህልማቸው ባሳያቸው ግዜ ዩሹዕን ለቀቁት።
ሙሳ ከዩሹዕ ከተሰወረበት በኋላ እቤቱ ተጋድሞ ሳለ መለከል መውት እንደልማዱ ድንገት ዘው ብሎ ገባ።
ሙሳም፦"ያለ ፍቃዴ ማን ነው እቤቴ ሚገባው" በማለት ብድግ አለ'ና አንድ ግዜ በቦክስ ወቃ ሲያደርገው የመለከል መውት አንድ አይኑ ፈሰሰ።
መለክል መውትም ወደ አላህ በመመለስ፦"ጌታዬ ሞትን ወደማይፈልግ ባሪህ ዘንድ ነው የላክከኝ።አይኔ በቦክስ መትቶኝ አጠፋው።ለሱ ያለህ ቦት ልዩ ባይሆን ኖሮ ለሁለት እስነጥቀው ነበር" አለ።
አላህም የመለክል መውትን አይን አበራለት'ና፦"ተመልሰህ ሂድ እናም ለሙሳ እንዲህ በለው፦እጅህን በከብት ቆዳ ላይ ዳስስ እጅህ ባካለለው በቆዳው ፀጉር ልክ አመት ትኖራለህ" ብሎ ወደ ሙሳ ሸኘው።
መለከል መውትም ሙሳ ዘንድ ተመልሶ መጣ'ና፦"እጅህን በከብት ቆዳ ላይ ዳስስ እጅህ ባካለለው በቆዳው ፀጉር ልክ አመት ትኖራለህ" ሲለው....
ሙሳም፦"ከዚያስ..." አለው።
መለክል መውትም፦"ከዚያማ ትሞታለሃ" አለው።
ሙሳም፦"በቃ ሞት ካልቀረ አሁኑኑ ግደለኝ" አለው።
መለክል መውትም ሙሳን አንድ ግዜ አሸተተው'ና በተወለደ 120 አመቱ ዱንያን አሰናበተው።
{የአላህ ሰላም እና እዝነት በሙሳ እና በሀሩን ላይ ይስፈን}




ይ........ቀ......ጥ.......ላ........ል::
1.2K viewsمصباح, 18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 21:14:10 ቁርዓን ተፍሲር
#سورة_النحل 09
ሱረቱ An-Nahl
#ክፍል_9 አቡ ኒብራስ
@historyofislam2
937 viewsمصباح, 18:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ