Get Mystery Box with random crypto!

History of islamic

የቴሌግራም ቻናል አርማ historyofislam2 — History of islamic H
የቴሌግራም ቻናል አርማ historyofislam2 — History of islamic
የሰርጥ አድራሻ: @historyofislam2
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 4.21K
የሰርጥ መግለጫ

👉ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል)
👉 ቁርአንና የቁርአን ተፍሲር እንድሁም ነብያዊ ሀድሶች
👉ኢስላማዊ ታሪኮች የነብያት የሱሀቦች የሰለፎች የሀገራት የታላላቅ ዳኢዎች ቃሪወች ሌሎችም ታሪኮች ይቀርባሉ ። 👉 እንድሁም ኪታቦች ይቀርባሉ አስተያየት (Comment)በ @Abureyaan ፃፉልን #channel_crate_june20_2018

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-12 18:05:46 በተጨማሪም ተቋርጦ የነበረው የነብያችን ﷺ
ታሪክ (ሲራ) ይቀጥላል ኢንሻአላህ
437 viewsمصباح, 15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 18:03:55 ; ቁርዓን ተፍሲር

#سورة_النحل 16
ሱረቱ An-Nahl
#ክፍል_16 አቡ ኒብራስ
@historyofislam2
440 viewsمصباح, 15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 21:22:00 #_የብያት_ታሪክ

#_ነቢየሏህ_ሱለይማን_ዐለይሂ_ሰላም

ከእለታት አንድ ቀን ሱለይማን ሰግዶ ቁጭ ባለበት አንዲትን ችግኝ
ተመለከተ'ና፦"ስምሽ ማን ነው" አላት።
ችግኟም፦"አፍራሽ እባላለሁ" አለችው።
ሱለይማንም፦"ለምንድነው የተፈጠርሽው?" አላት።
ችግኟም፦"ይሄን ቤት ለማፍረስ" አለችው።
ይሄን ግዜ ሱለይማንም አላህን፦"ያ አላህ በጅኖች እና በሰዎች የኔን ሞት ደብቅባቸው።የሩቅን ነገር የማያውቁ መሆናቸውን ይረዱ ዘንድ" አለ።

በመጨረሻም ሱለይማን የዛችን ችግኝ እንጨት ፈልጎ ከቆረጠ በኋላ ጥሩ በትር ሰራባት። ከዚያም ጂኖችን እና ሰይጣናትን በይተል መቅዲስን እንዲገነቡ አዘዛቸው'ና እሱ ሚህራብ(ግላዊ የአምልኮ ቦታ) ገብቶ ዒባዳ ማድረግ
ችግኋም፦" እኬሌ" ብላ ስሟን ትነግረዋለች።
ሱለይማንም፦" ለምንድነው የተፈጠ
ርሽው?" ሲላት
ችግኟም የተፈጠረችለትን አላማ ትነግረዋለች።
ከእለታት አንድ ቀን ሱለይማን ሰግዶ ቁጭ ባለበት አንዲትን ችግኝ
ተመለከተ'ና፦"ስምሽ ማን ነው" አላት።
ችግኟም፦"አፍራሽ እባላለሁ" አለችው።
ሱለይማንም፦"ለምንድነው የተፈጠርሽው?" አላት።
ችግኟም፦"ይሄን ቤት ለማፍረስ" አለችው።
ይሄን ግዜ ሱለይማንም አላህን፦"ያ አላህ በጅኖች እና በሰዎች የኔን ሞት ደብቅባቸው።የሩቅን ነገር የማያውቁ መሆናቸውን ይረዱ ዘንድ" አለ።
በመጨረሻም ሱለይማን የዛችን ችግኝ እንጨት ፈልጎ ከቆረጠ በኋላ ጥሩ በትር ሰራባት። ከዚያም ጂኖችን እና ሰይጣናትን በይተል መቅዲስን እንዲገነቡ አዘዛቸው'ና እሱ ሚህራብ(ግላዊ የአምልኮ ቦታ) ገብቶ ዒባዳ ማድረግ ጀመረ።
ብዙም ሳይቆይ እዚያም ሚህራብ ውስጥ ሳለ በተወለደ በ 52 አመቱ በትሩን እንደተደገፈ የሞትን መራራ ፅዋ ቀመሰ።
ይሁን እንጂ ጂኖችም ሆነ ሰይጣናት የሱለይማንን ሞት አላወቁም ብቻ እሱ ሚያያቸው መስሏቸው ለአንድ አመት ያለ ማቋረጥ ሲገነቡ ከረሙ።
ጂኖች እና ሰይጣናት ሱለይማን በህይወት ሳለ እሱን ማየት አይቻላቸውም ነበር፤ካዩትም ወዲያ ነበር ሚቃጠሉት። አሁን አሁን ግን ሱለይማን አንድ አመት ሙሉ እዚያ ሚህራብ ውስጥ መቆየቱ አጠራጥሯቸዋል።
አንድ ሰይጣን ለማጣራት የሱለይማን ኑር እንዳያቃጥለው በመጠንቀቅ ወደ ሚህራቡ ዘንድ ጠጋ ብሎ ወዲያው ዞር አለ። ግን አላቃጠለውም።
አሁንም እየሮጠ ጠጋ አለ'ና ዳግም በፍጥነት ተመለሰ።ይሁን እንጂ ድሮ ሚያቃጥላቸው ነገር አሁን የለም። ይሄን ግዜ ቀስ ብሎ ወደ ሚህረቡ ውስጥ ዘልቆ ሲገባ ሱለይማን ከሞተ በኋላ አመት ሙሉ የተደገፋት በትር መሬት በልቷት አስክሬኑ ወድቆ አገኘው።ይሄን ግዜ ሰይጣኑ ወጥቶ ለሁሉም የሱለይማንን መሞት ነገራቸው።
(ጋኔኖችም ሩቅን ምስጢር የሚያወቁ በኾኑ ኖሮ በአዋራጅ ስቃይ ውስጥ የማይቆይ እንደነበሩ ተረዱ) ሱረቱ ሰበእ...
[የአላህ ሰላም እና እዝነት #_በሱለይማን ላይ ይሁን]
____
ምንጮች፦
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ /ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻟﺜﺎﻧﻲ/
القرءان الكريم
__

በቀጣይ የነብዩላህ ኢልያስ አለይሂሰላም ታሪክ
ይቀጥላል

@historyofislam2
@historyofislam2
600 viewsمصباح, 18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 06:37:32 ከ አል –ሁድሁድ የሰለፋዮች
ስቱዲዮ ደሴ


የዓረፋ ቀን ደረጃው እና የዑዱሂያ ህግጋቶች 03

በሚል ርዕስ የተዘጋጀ የሆነ ወቅታዊ ሙሀደራ።

ላልደረሳቸው በማድረስ የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ አላህ ተጠቃሚዎች ያድርገን ።

ነስር መስጂድ(ደሴ)


በሼህ :–አቡ ኒብራስ / አላህ ይጠብቀው።/

ـــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــــ
https://t.me/Hudhud_Studio/7208

አጠቃላይ ፕሮግራሞቻችን በሶሻል ሚዲያ ለመከታተል:-

በ Telegram~Channel

https://telegram.me/Al_Furqan_Islamic_Studio/

በ Facebook~page
https://www.facebook.com/104176388231064/page
747 viewsمصباح, 03:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 22:11:32 #_የነብያት_ታሪክ

#_ነቢየሏህ_ሱለይማን_ዐለይሂ_ሰላም


ዳዉድ ከሞተ በኋላ ዙፋኑን የዳዉድ ልጅ የሆነው ጥበበኛው እና ብልሁ ሱለይማን ወርሶታል።ግዛቱንም በጥሩ ሁኔታ በማስተዳደር ላይ ይገኛል።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ከእለታት አንድ ቀን ሱለይማን እጁን ወደ ጌታው በመዘርጋት፦"ጌታዬ ሀፅያቴን ይቅር በለኝ።ከኔ በኋላ ለሚመጣ ትውልድ በሙሉ የማይገባ የሆነንንም ንግስናን ስጠኝ" በማለት ተማፀነ።
አላህም ለያንዳንዱ ነቢያት ዱዐቸውን እንደሚቀበለው ሁላ የሱለይማንንም ዱዓ አላህ ተቀብሎት፤ ንፋስን ሱለይማን ወደሚያዘው መንገድ እንዲነፍስ፣ሰይጣናትንም በሱለይማን ቁጥጥር ውስጥ አድርጓቸው እሱ ያዘዛቸውን እንዲፈፅሙ፣ ግዴታ አደረገባቸው።
በመቀጠልም የወፎችን እና የእንስሳቶችንም ቋንቋ በሙሉ አሳወቀው።ሱለይማንም አላህ በሰጠው ወደር የለሽ ፀጋ አላህን አመሰገነው።
ከእለታት አንድ ቀን ሱለይማን ወታደሮቹን(ሰይጣናትን፣ጂኒዎችን፣ ሰዎችን...ብዙ እንስሳቶችን) ሰብስቦ በመጓዝ ላይ ሳለ አንዲት ጉንዳን ለሌሎች ጉንዳኖች፦"እናንተ ጉንዳኖች ሆይ !!! ሱለይማን እና ወታደሮቹ እየመጡ ነው። ሳያውቁ በእግሮቻቸው እንዳይጨፈላልቋችሁ፤ ወደየቤታችሁ ግቡ" በማለት ስትናገር ሰማት።
ይሄን ሲሰማ ሱለይማንም ፈገግ አለ'ና፦"ጌታዬ ሆይ! ያቺን በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስካትን ጸጋህን እንዳመሰግን እና የምትወደውንም በጎ ሥራ እንድሠራ ምራኝ፡፡ በችሮታህም በመልካሞቹ ባሮችህ ውስጥ አኑረኝ" አለ።
ሱለይማን ሰራዊቶቹን ከሰበሰበ በኋላ የቀሩትን ማጣራት ጀመረ።ሁሉም መጥቷል ግን አንድ ሁድሁድ የተባለ ወፍ አልታየው ከዚያም፦"ሁድሁድ ለምን አይታየኝም!!! ወይስ ራቅ ብሎ ሄዶ ነው? ብርቱን ቅጣት በእርግጥ እቀጣዋለሁ፡፡ ወይም በእርግጥ ዐርደዋለሁ፤ ወይም ግልጽ በኾነ አስረጅ(ምክንያት) ይመጣኛል"አለ።
ከዚያም በማግስቱ ሁድሁድ መጣ'ና ሱለይማን ፊት ቆመ።ሱለይማንም የት እንደነበር ሲጠይቀው ሁድሁድ፦"እኔ ሰበእ የሚባል አካባቢ ሄጄ ነበር።አንድ ሁሉ ነገር የተሟላላትንም ንግስት አገኘሁ፣ትልቅ የሆነም ዙፋን አላት።
ነገር ግን እሷንም ሆነ ህዝቦቿን ለአላህ መስገድ ሲገባቸው ለፀሀይ ሲሰግዱ ተመለከትኳቸው" አለው።
ሱለይማንም፦"እስቲ ይህን ደብዳቤ ይዘህ እሷ ዘንድ ወስደህ ጣለው።ከዚያም ራቅ ብለህ ምን እንደሚከሰት ተመልከት።እውነት እንደተናገርክ እና እንደዋሸህ እናያለን" አለው
ሁድሁድም የሱለይማንን ደብዳቤ ይዞ ወደ ሰበእ ምድር ይከንፍ ጀመር። ልክ የሰበእን ምድር እንደረገጠ ወደ ንግስቲቱ ቤተ መንግስት በመግባት ንግስቲቱ ፀሎት ላይ ባለችበት ሁኔታ ሱለይማን የላከውን ደብዳቤ ጣለላት።
ንግስቲቱም ፀሎቷን አጠናቅቃ ቀና ስትል ይህን ደብዳቤ መሬት ላይ ወድቆ አገኘችው።ደብዳቤውንም ከፍታ ስታነበው፦"ይህ ከሱለይማን የሆነ መልዕክት ነው።በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፤ በእኔ ላይ አትኩሩ፡፡ ታዛዦችም ኾናችሁ ወደኔ ኑ!" የሚል መልዕክት አነበበች።
ይህን መልዕክት እንዳነበበችውም ወዲያው አማካሪዎቿን እና የጦር መሪዎችን በመሰብሰብ ስለጉዳዩ አማከረቻቸው።እነሱም ጉዳዩ ካዳመጡ በኋላ፦"እኛ የበርካታ ወታደሮች ባለቤት ስንሆን ከባድ ጉልበትም አለን። መብቱ ያንች ነው የፈለግሽውን እዘዢን እኛ እንፈፅመዋለን" አሏት።
እሷም፦"ንጉሶች አንድን ከተማ ገብተው ከወረሩ ያን ከተማ እንዳልነበረ አድርገው ያበላሹታል።የከተማይቱንም የተከበሩ ነዋሪያንን ያዋርዳሉ። ስለዚህ እኔ አገልጋዮቼን በርካታ ስጦታዎችን አስጭኜ ወደ ንጉስ ሱለይማን ዘንድ እልካለሁ።ከዚያም ስጦታውን የወሰዱት አገልጋዮች በምን እንደሚመለሱ አያለሁ" ብላ በመወሰን የአማካሪዎቿን ሀሳብ ውድቅ አደረገች።
በማግስቱም የንግስቲቱ አገልጋዮችም የተጫነላቸውን የስጦታ መዐት ጭነው ብዙ ከተጓዙ በኋላ የሱለይማንን ግዛት ሲገቡ በሚያዩት ነገር ሁሉ በጣም ተደመሙ።
ልክ ከተማዋን እንደደረሱም የጫኑትን ስጦታዎች እየነዱ ወደ ሱለይማን ቤተ መንግስት ገቡ።ሱለይማንም ስጦታውን እንደተጫነ መልሱላት ብሎ እሷ እና ህዝቦቿ በአላህ የማያምኑ ከሆነ መቋቋም የማይችሉትን ወታደር አሰልፎ እንደሚመጣባቸው መልዕክት ላከ።
ስጦታውን ያመጡት መልዕክተኞች ስጦታውን ይዘው ከቤተ መንግስት ግቢ ልክ እንደወጡትም ሱለይማን ሰራዊቶቹን ሰብስቦ፦"እናንተ መኳንንቶች ሆይ! ንግስቲቱ እና የንግስቲቱ ህዝቦች ሙስሊሞች ኾነው ሳይመጡኝ በፊት የንግስቲቱን ዙፋን እዚህ የሚያመጣልኝ ማንኛችሁ ነው" ሲል ተናገረ።
በስብሰባው ጂኖች...ሸይጣኖች...ብዙ ፍጥረታት ነበሩ'ና አንድ በጣም ሀይለኛ ጂን ቆመ'ና፦"አሁን ቁጭ ካልክበት ዙፋን ከመነሳትህ በፊት እኔ ሰበእ ሄጄ የንግስቲቱን ዙፋኑን ላምጣልህ፤ እኔም ታማኝ እና ሀይለኛ ነኝ" አለው።
አንድም የአላህን ስሞች ሁሉንም ጠንቅቆ የሚያውቅ እና ዱዓው ሙስተጃብ የሆነ ሰውዬ በመሀከላቸው ብድግ አለ'ና ለሱለይማን፦"እኔ አይንህ ከመርገብገቡ በፊት ዙፋኑን ፊትህ አስቀምጥልሀለሁ" አለ'ና ሱለይማን የአይኑን ቆብ ዘግቶ እስኪከፍት ድረስ የንግስቲቱ ዙፋን ፊትለፊቱ ቁጭ ብሎ አገኘው።
ሱለይማን ይሄን ሲመለከት፦"ይህ ከጌታዬ ችሮታ ነው፡፡ የማመሰግን ወይም የምክድ መኾኔን ሊሞክረኝ (ቸረልኝ)፡፡ ያመሰገነም ሰው የሚያመሰግነው(ጥቅሙ) ለራሱ ነው፡፡ የካደም ሰው ጌታዬ ከእርሱ ተብቃቂ ቸር ነው" በማለት ጌታውን አመሰገነ።
ከዚያም ሱለይማን ጂኖችን፦"ባህር ላይ መስታወት በማንጠፍ እዚያ መስታወት ላይ ይሄን ዙፋን አስቀምጡበት" አላቸው።ጅኖችም በሱለይማን ትዕዛዝ መሰረት ባህር ላይ መስታወት በማንጠፍ ዙፋኑን መስታወቱ ላይ አስቀመጡት።
ንግስቲቱ የሱለይማንን ግዛት ገብታ የግዛቱን ስፋት እየተመለከተች በጣም ተገረመች።በመጨረሻም ሱለይማን ንግስቲቱን ከተቀበላት በኋላ ባህር ላይ ወዳስገነባው ቤተ መንግስት በመውሰድ፦"ያንች ዙፋን እንዲህ አይነት ነው?" አላት።
እሷም፦" አዎን ልክ እራሱን ይመስላል" አለችው።
እሱም፦"በይ ሂጂ ዙፋንሽ ላይ ቁጭ በይ" አላት።
እሷም መስታወት መሆኑን አላወቀችም ባህሩን ብቻ አይታ ዙፈኗ ጋ ልትሄድ ልብሶቿን ወደ ላይ ስትሰበስብ ሱለይማንም፦"ባህሩ እኮ አንችን አያገኝሽም ይህ ባህር ከላዩ መስታወት ተነጥፎለታል። ሂጂ ግቢ" አላት።
ያን ግዜ ንግስቲቱ ሱለይማን ነቢይ እንጂ ተራ ንጉስ አለመሆኑን በመረዳት፦"ጌታዬ ሆይ! እኔ ነፍሴን በደልኩ፡፡ ከሱለይማንም ጋር ሆኜ ለዓለማት ጌታ ለአላህ ታዘዝኩ" አለች።
ከዚያም ሱለይማን በንግስና ሆኖ ብዙ አመታትን ኖረ።ሱለይማን አንድ ባህሪ አለው..እሱም አንድ ቦታ ሲሰግድ ከአቅራቢያው አንድ ችግኝ ከተመለከተ፦ስምሽ ማን ነው?" ይላታል።
ችግኋም፦" እኬሌ" ብላ ስሟን ትነግረዋለች።
ሱለይማንም፦" ለምንድነው የተፈጠርሽው?" ሲላት
ችግኟም የተፈጠረችለትን አላማ ትነግረዋለች።
ከእለታት አንድ ቀን ሱለይማን ሰግዶ ቁጭ ባለበት አንዲትን ችግኝ
ተመለከተ'ና፦.......


ኢንሽዓሏህ
ይ.......ቀ.......ጥ......ላ......ል፡፡
993 viewsمصباح, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 18:48:35 - በዒድ ቀን ኡድሂያን ለማረድ አስቦ የዙልሂጃ ወር ከገባ ጥፍሩንና
ጸጉሩን አይቆርጥም። ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህ በሀጅ ላይ ያሉ
ሰዎችን የሚመሳሰልበት ነብያዊ ትዕዛዝ ነው። ይህ የሚመለከተው
የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው። እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ
ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው
ግን አይበላሽም።
የመልካም ስራ በሮች ብዙ ናቸውና የቻልነዉን ሁሉ በመፈጸም ወደ
አላህ እንጠቀምበት ቀጣይ ማን እንደሚያገኘው እና ማን እንደሚለይ አይታወቅም

@historyofislam2
@historyofislam2
1.2K viewsمصباح, 15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 18:48:20 ⇘¹ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው አስርቱ የዙልሂጃ ቀናት①

ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላምና እዝነት በታላቁ ነብይ በሙሀመድ በባልደረቦቻቸው እና በቤተሰቦቻቻው ሁሉ ላይ ይሁን፡፡
ከተከበሩት ወራት መካከል አንዱ የሀጅ ወር ዙልሂጃ ነው። ከቀናት ሁሉ
አላህ ዘንድ የተወደዱት ደግሞ አስሩ የዙልሂጃ ቀናት ናቸው። እንደዉም
ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያለቸው እነኝህ ቀናት ናቸው። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤
عن جَابِرِ بْنِ عَبْدِ االلهِ رَضِيَ االله عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولَ االلهِ صَلَّى االله عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: "أَفْضَلُ أَيَّامِ الْدُّنْيَا أَيَّامُ
الْعَشْرِ، يَعْنِي عَشْرُ ذِي الحْجَّةِ". أخرجه البزار كما فى كشف الأستار (٢/٢٨ ، رقم ١١٢٨ (قال
الهيثمي (٤/١٧ : (رجاله ثقات ، وصححه الألباني (صحيح الجامع ، رقم ١١٣٣.(
ጃቢር ኢብኑ ዓብዲላህ ባስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል
«ከዱንያ ቀናት ሁሉ ብልጫ ያላቸው፤ አስርቱ
የዙልሂጃ ቀናት ናቸው » አልበዛር እና አልሐይሰሚይ ዘግበዉታል
አልባኒም ሰሂህ ብለዉታል (ሰሂሁል ጃሚዕ 1133)
عن ابن عباس رضي االله عنهما، عن النبي صلى االله عليه وسلم قال: "ما من أيام العمل الصالح
فيهن أحب إلى االله منه في هذه الأيام العشر. قالوا ولا الجهاد في سبيل االله !! قال : ولا الجهاد
في سبيل االله، إلا رجل خرج بنفسه وماله ولم يرجع من ذلك بشيء" أخرجه البخاري

ከኢብኑ ዓባስ በተዘገበ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፤
«በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች
አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም፤
“በአላህ መንገድ ላይ
የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?” ተባሉ። እርሳቸውም፤ “ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም” አሉ።»
ቡኻሪ ዘግበውታል
በነዚህ ቀናቶች ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገቡ የዒባዳ አይነቶች መካከል፤
①ጾም፤ ጾም ከስራዎች ሁሉ በላጭ ነውና በእነዚህ ቀናት
#መጾም እጅግ የተወደደ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ዘጠኙን የዙልሂጃ ቀናት ይጾሙ
እንደነበር ተዘግቧል። (አስረኛው ቀን ግን ዒድ ስለሆነ አይጾምም)
②• ዚክሮችን ማብዛት፤ አላህን ማመስገን (አልሀምዱሊላህ) ተክቢር፣ ተስቢህ (ሱብሀነላህ) እና ተህሊል (ላ ኢላሀ ኢለላህ)፤ ኢባዳዉን
ለማስታወስና የአላህን ስም ከፍ ለማድረግ በተለያዩ አጋጣሚዎች
ድምጽን ከፍ አድርጎ እነዚህን ዚክሮች ማድረግ ይወደዳል።
عن عبد الله بن عمر رضي االله عنهما عن النبي صلى االله عليه وسلم قال : "ما
من أيام أعظم عند االله ولا أحب إليه العمل فيهن من هذه الأيام العشر فأكثروا
فيهن من التهليل والتكبير والتحميد" أخرجه احمد 224/7وصحّح إسناده أحمد شاكر
ዓብዱላህ ኢብኑ ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩه እንዲህ ብለዋል፤

«ከእነዚህ አስር ቀናት በበለጠ አላህ ዘንድ ታላቅ የሆኑና መልካም ስራ እጅግ የተወደደባቸው ቀናት የሉም፤ ስለዚህ ተህሊል ተክቢር እና ተህሚድ አብዙ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል አህመድ ሻኪርም
ሰሂህነቱን አረጋግጠዋል።
ከተክቢር አደራረግ መካከል፤
االله أكبر ، االله أكبر لا إله إلا االله ، واالله أكبر والله الحمد
“#አላሁ አክበር፤ አላሁ አክበር፤ ላ ኢላሀ ኢለላህ ወላሁ አክበር
ወሊላሂልሀምድ” የሚለው ዋነኛው ሲሆን ሌሎችም ይዘቶች አሉት።
በእነዚህ ቀናት ውስጥ ሊደረግ የሚገባው ይህ ተክቢር ብዙ

ሰዎች ስለማይፈጽሙት እየተረሱ ካሉ ሱናዎች ማካከል ነው። ሰዎችን
ለማስታወስ እና ሱናን ህያው ለማድረግ ድምጽን ከፍ አድርጎ ተክቢር ማድረግ ያስፈሊጋል። ዓብዱላህ ኢብኑ ኡመር እና አቡሁረይራህ በነዚህ
አስር ቀናት ገበያ ወጥተው ተክቢራ ሲያደርጉ ሰዎችም እያስታወሱ
ተክቢራ ያደርጉ እንደነበር ተዘግቧል። ይህም፤ ሁሉም ሰው የራሱን
#ዚክር ያደርጋል ማለት ነው እንጂ ሰዎች እየተሰባሰቡ በአንድ ድምጽ ተክቢራ ያድርጉ ማለት አይደለም። ይህ መረጃ ያልተገኘለት ውድቅ ስራ
ነው።
⇘³•ሐጅና ዑምራ፤ በነዚህ ቀናት ውስጥ ከሚፈጸሙ መልካም ስራዎች ③ መካከል ሐጅ ማድረግ ይገኝበታል፤ በነዚህ አስር ቀናት
³•የሐጅ ዒባዳ ላይ ተገኝቶ በተገቢው መልኩ ከፈጸመው በአላህ ፍቃድ ከተከታዩ
የአላህ መልዕክተኛ ብስራት ድርሻ ይኖረዋል፤
⇙عن أبي هريرة رضي االله عنه قال: سمعت ه يقول: "الحج المبرور ليس له جزاء
إلا الجنة" متفق عليه.
⇘ከአቡ ሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛه እንዲህ
ብለዋል፤ «ከወንጀል የራቀና ተቀባይነት ያለው ሐጅ (አል-ሐጅ
አል-መብሩር) ምንዳው ጀነት እንጂ ሌላ አይደለም፡፡»
#ቡኻሪና ሙስሊም ተስማምተውበታል
④•ኡድሂያ- በነዚህ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን
በማረድ ወደአላህ መቃረብ ነው።
⇘•የሚከተሉት ነጥቦች አጠር ያለ ግንዘቤን የሰጣሉ…
#ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ ሱናዎች መካከል ነው።
#የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረጉ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው።
#ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ
(ተቅዋ) ነው።
#ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ
ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል።

#ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት
ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ
ኡድሂያን ማረድ ይቻላል።
#ወንድም ይሁን ሴት ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል ለኡድሂያ ይታረዳሉ።
#የአላህ መልዕክተኛه እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል።
#አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ፣ የታመመ
እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም።
#ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን
ወይፈን ወይም በሬ መጋርትም ይቻላል።
#አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን
በህይወት ለሌሉ ለቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል።
⁴⇘•ኡድሂያውን ለራሱ፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ መከፋፈሉ ሱና ነው። ④ ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ
ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም።

@historyofislam2
@historyofislam2
1.1K viewsمصباح, 15:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 00:41:56 ሀሙስ ወይም ጁምአ ይያዛል
999 viewsمصباح, 21:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 00:41:12 በነዚህ አስር ቀናቶች የሚወደድ ተግባር


ሰላት


ዋጅብ ሰላት ላይ ከሌላው ግዜ በበለጠ መልኩ ይበልጥ መጠናከር ሱና ሰላትንም ማብዛት ይወደዳል።

ምክንያቱም ሰላት ከትልልቆቹ መልካም ስራዎች መሐከል ነው በነዚህ ቀናቶች ደግሞ መልካም ስራ አብዙ ተብሏል

ፆም


መልካም ስራ ከሚለው ውስጥ ፆምም ስለሚገባ። የአላህ መልእክተኛም ዘጠኙን የዙልሒጃ ቀናቶች ይፆሙ እንደነበር የመጣ ሐዲስ ስላለ

_ኢማመ ነወዊ ዘጠኙን የዙልሒጃ ቀናቶች መፆም የጠነከረ ሱና መሆኑን ይገልፃሉ

ተክቢራን ማብዛት

የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል

‏« ﻣﺎﻣﻦ ﺃﻳّﺎﻡ ﺃﻋﻈﻢ ﻋﻨﺪ ﺍﻟﻠﻪ ﺳﺒﺤﺎﻧﻪ ﻭﻻ ﺃﺣﺐ ﺇﻟﻴﻪ ﺍﻟﻌﻤﻞ ﻓﻴﻬﻦ ﻣﻦ ﻫﺬﻩ ﺍﻷﻳﺎﻡ ﺍﻟﻌﺸﺮ، ﻓﺄﻛﺜﺮﻭﺍ ﻓﻴﻬﻦ ﻣﻦ ﺍﻟﺘﻬﻠﻴﻞ ﻭﺍﻟﺘﻜﺒﻴﺮ ﻭﺍﻟﺘﺤﻤﻴﺪ ‏» . ‏( ﺭﻭﺍﻩ ﺍﻟﻄﺒﺮﺍﻧﻲ ﻓﻲ ﺍﻟﻤﻌﺠﻢ ﺍﻟﻜﺒﻴﺮ ‏)

<< የትኛውም ቀን የለም አላህ ዘንድ ትልቅ የሆነ እና ስራ የተወደደበት ከነዚህ አስር ቀኖች ይበልጥ።

በዛ ላይ ላሊላሀ ኢለላህ, አላሁ አክበር አልሐምዱሊላህ ከማለት አብዙ >>

{ኢማሙ ጠበራኒ ዘግበውታል

ኢብን ኡመርና አቡ ሑረይራ ወደ ሱቅ ወጥተው ተክቢራ ያደርጉ ነበር ሰዎችም የነሱን ተክቢራ ሰምተው ተክቢራ ያደርጉ ነበር።

ተክቢራውን ጮክ ብሎ ማለቱ ይወደዳል

- ከሰሀቦች እና ታብእዮች የመጡ የተክቢራ አይነቶች


◅ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ ﻛﺒﻴﺮًﺍ .
◅ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻّ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻭﻟﻠﻪ ﺍﻟﺤﻤﺪ .
◅ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻّ ﺍﻟﻠﻪ، ﻭﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻛﺒﺮ، ﻭﻟﻠﻪ ﺍﻟﺤﻤﺪ .


- የአረፍ ፆም


የሁለት አመት ወንጀል እንደሚያስምር ኢማም ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ ላይ መጥቷል

ﻗﺎﻝ ﻋﻦ ﺻﻮﻡ ﻳﻮﻡ ﻋﺮﻓﺔ : ‏« ﺃﺣﺘﺴﺐ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﺃﻥ ﻳﻜﻔﺮ ﺍﻟﺴﻨﺔ ﺍﻟﺘﻲ ﻗﺒﻠﻪ ﻭﺍﻟﺴﻨﺔ ﺍﻟﺘﻲ ﺑﻌﺪﻩ ‏» ‏( ﺭﻭﺍﻩ ﻣﺴﻠﻢ ‏) .

- ሰደቃ


መልካም ስራ በነዚህ ቀናቶች የተወደደ ነው ተብሏል። ሰደቃም ደግሞ ከመልካም ስራዎች ውስጥ ነው።

@historyofislam2
@historyofislam2
1.0K viewsمصباح, 21:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 20:19:21 ቁርዓን ተፍሲር

#سورة_النحل 14
ሱረቱ An-Nahl
#ክፍል_14 አቡ ኒብራስ
@historyofislam2
868 viewsمصباح, 17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ