Get Mystery Box with random crypto!

ሀገሬ 𝑛𝑒𝑤𝑠 𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ hgerenewsethiopia — ሀገሬ 𝑛𝑒𝑤𝑠 𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ hgerenewsethiopia — ሀገሬ 𝑛𝑒𝑤𝑠 𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @hgerenewsethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.18K
የሰርጥ መግለጫ

👇🇪🇹🇪🇹👇👇
ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም
ታሪክ አታበላሽም።
ቀዳሚ 👇የመረጃ ምንጭ
ሀገሬ 𝑛𝑒𝑤𝑠 𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎🇪🇹
👇
ምርት እና አገልግሎቶ
ለማስተዋወቅ ከፈለጉ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2022-06-01 20:40:16
ሲጋራ በየዓመቱ 8 ሚሊዮን ሰዎችን ይገድላል

ብዙዎችን ለካንሰር እና ተያያዥ የጤና እክሎች የሚዳርገው ሲጋራ በየዓመቱ 8 ሚሊዮን ሰዎችን እንደሚገድል መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

ሲጋራ ለማምረት በሚል በየዓመቱ 600 ሚሊዮን ዛፎች እንደሚቆረጡም ነው የሚነገረው፡፡

የዓለም የጸረ ትምባሆ ቀን ትናንት ማክሰኞ ተከብሯል፡፡

https://t.me/HgerenewsEthiopia
3.2K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 17:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 07:22:43
መንግሥት በአማራ ክልል ምን እየሠራ ነው?

ኢትዮጵያ ከአራት ዓመት ገደማ በፊት አድርጋው ከነበረ ተስፋ አንጻር አሁናዊ ሁኔታዋ በሕልም እንኳ ቢመጣ ‹ሕልም እልም!› የሚባልና በብዙዎች ሐሳብ ይሆናል ተብሎ የማይገመት ነው።

ይልቁንም በሰሜኑ የተከሰተውን ጦርነት ተከትሎ የታዩ ግጭቶች፣ የብዙዎች ሞትና መፈናቀል፣ እንግልትና መከራ ወትሮም ሲጠየቅ የነበረውን ‹ወዴት እየሄድን ነው?› ጥያቄ በአዲስ መልክ ያስነሳ ሆኗል።

መንግሥት በበኩሉ ተቃውሞዎችንና ቅሬታዎችን ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት፣ ‹እኔ የማደርገውን አውቃለሁ!› በሚመስል አኳኋን የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የተለያዩ አፈናዎችና እገታዎች በመንግሥት እየተፈጸሙ ነው።

ጋዜጠኞች፣ ተጽእኖ ፈጣሪ ሰዎችና በተለያየ አደረጃጀት ውስጥ ያሉ ሰዎች ታሰሩ፣ ተያዙ፣ ታፈኑ የሚሉ ዜናዎች በብዛት እየተሰሙ ነው።

ይህንን ጨምሮ በተለይ በአማራ ክልል መንግሥት ‹ሕግ የማስከበር ዘመቻ› ነው የያዝኩት ይበል እንጂ፣ ከተቃውሞ የዳነ አይደለም።


https://t.me/HgerenewsEthiopia
3.5K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 07:18:15
ሩሲያ በምስራቃዊ የሃገሪቱ አካባቢ የጀመረችው የተጠናከረ ዘመቻ ያሳሰባት የምትመስለው ዩክሬን ከሰሞኑ ረጅም ርቀት ዒላማዎችን ለመምታት የሚችሉ ጦር መሳሪያዎች ድጋፍ እንዲደረግላት አሜሪካን ጨምሮ ምዕራባውያንን ጠይቃ ነበረ፡፡

ጥሪውን ተከትሎም አሜሪካ ረጅም ርቀት ተምዘግዛጊ ሮኬቶችንና ማስወንጨፊያዎችን ለዩክሬን እንደምትሰጥ አስታውቃለች፡፡

ሆኖም ሮኬቶቹ ድንበር ተሻግረው ሩሲያ ለመምታት የሚችሉ እንደማይኑ ዋሽንግተን አስታውቃለች፡፡

https://t.me/HgerenewsEthiopia
3.3K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 04:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 18:35:12
የአለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ ክልል 3 ሺህ ቶን የምግብ ዕርዳታ ማከፋፈሉን አስታወቀ

የምግብ አቅርቦቱም ለ120 ሺህ ዜጎች ተደራሽ መሆኑንም ተገልጿል

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ባሳለፍነው ሳምንት የእርዳታ አቅርቦት የጫኑ 1 መቶ 65 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል መድረሳቸዉንና 3 ሺህ ቶን የምግብ ዕርዳታ ማከፋፈሉን  አስታወቀ።

3 ሺህ 400 ቶን የምግብ ዕርዳታ ደግሞ ወደ ማከፋፈያ ጣቢያዎች መላካቸውን ገልጿል። የምግብ አቅርቦቱም  ለ120 ሺህ ዜጎች ተደራሽ መሆኑንም ገልጿል ።

አሁን ላይም እርዳታ የጫኑ 94 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ እያቀኑ ነው ያለ ሲሆን፥ የምግብ ርዳታ ሥርጭቱ በአፋር እና በአማራ ክልልም በሂደት ላይ ነው ማለቱን ከዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል::

https://t.me/HgerenewsEthiopia
6.7K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 15:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 18:31:16
4.7K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-13 18:26:49
3.8K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ