Get Mystery Box with random crypto!

ሀገሬ 𝑛𝑒𝑤𝑠 𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ hgerenewsethiopia — ሀገሬ 𝑛𝑒𝑤𝑠 𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ hgerenewsethiopia — ሀገሬ 𝑛𝑒𝑤𝑠 𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @hgerenewsethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.18K
የሰርጥ መግለጫ

👇🇪🇹🇪🇹👇👇
ኢትዮጵያን መውደድ ባትችል አትጥላት
ማክበር ባትችል አታዋርዳት
ማራመድ ባትችል አታዘግያት
መጠበቅ ባትችል አትበትናት።
ይህን በማድረግ ታሪክ ባትሠራም
ታሪክ አታበላሽም።
ቀዳሚ 👇የመረጃ ምንጭ
ሀገሬ 𝑛𝑒𝑤𝑠 𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎🇪🇹
👇
ምርት እና አገልግሎቶ
ለማስተዋወቅ ከፈለጉ

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2022-06-16 22:28:47
ከሀገር ውጭ (በኬንያ እና በጂቡቲ) በኩል በሚያልፉ ከፍተኛ ባንድዊድዝ ተሸካሚ ዓለም አቀፍ ባህር ጠለቅ የኢንተርኔት መገናኛ መስመሮች ላይ ባጋጠመን ችግር ምክንያት የኢንተርኔት አገልግሎታችን በመጠባበቂያ መስመሮች ብቻ እየሰራ በመሆኑ የኢንተርኔት አገልግሎት መቆራረጥ ወይም የፍጥነት መቀነስ ሊያጋጥም እንደሚችል ከታላቅ ይቅርታ ጋር እያሳወቅን፣ አገልግሎቱን በፍጥነት ለማስቀጠል ባለሙያዎቻችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ በመሆናቸው እስከዚያው በትዕግስት እንድትጠብቁን በትህትና እንጠይቃለን፡፡


https://t.me/HgerenewsEthiopia
5.4K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 15:05:37 Watch "@ሀገሬ youtube" on YouTube
https://youtube.com/channel/UCRliPQx2JOATNrZKeUCn5NA
7.7K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 12:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 23:58:17 https://vm.tiktok.com/ZMNdcTwmb/?k=1

7.1K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , edited  20:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 13:03:42
ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ላለን ግንኙነት ላይ ትልቅ ቦታ እንሰጣለን”- ፕሬዝዳንት ፑቲን

የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር እና የሴኔጋል ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል እና የአፍሪ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ከሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በሩሲያ ሶቺ ከተማ ተወያይተዋል።

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ጋር ተገናኝተው ከተወያዩ በኋላ ባደረጉት ንግግር፣ ሩሲያ “ሁልጊዜም ከአፍሪካ ጎን ናት” ሲሉ ተናግረዋል።

https://t.me/HgerenewsEthiopia
7.5K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 10:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 13:01:36
አሜሪካ በሶማሊያ የመሸጉትንና ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት ያላቸውን የአልሻባብ ተዋጊዎች ኢላማ ያደረገ የአየር ጥቃት ሰነዘረች፡፡

አሜሪካ የወሰደቸው እርምጃ፤ ጆ ባይደን ወታደሮቻቸውን እንደገና ወደ አፍሪካ ቀንዷ ሀገረ ሶማሊያ እንደሚልኩ ካሳወቁ በኋላ የተወሰደ የመጀመሪያ እርምጃ ነው፡፡

በጥቃቱ አምስት የአልሸባብ ተዋጊዎች መገደላቸውን እና በሰላማዊ ሰዎች ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን የሶማሊያ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ገልጿል።

ሆኖም ዋሽንግተን ወሰደችው ስለተባለው እርምጃ እስካሁን ያለችው ነገር የለም፡፡

አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት አልሸባብ በሚያሰጋ ሁኔታ እየጠነከረ መጥቷል፡፡

ለዚህም ከ500 ያላነሱ ከሶማሊያ ውጭ ሲሰሩ የነበሩ የአሜሪካ ልዩ ኦፕሬተሮች ወደ ሶማሊያ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡

ፕሬዝዳንት ባይደን የቀጠናው ስጋት የሆነውን አልሻባብ ለመምታት 600 የሚሆኑ የሃገራቸውን ወታደሮች ወደ ሶማሊያ እንደሚልኩ ባለፈው ወር ማስታወቃቸው የሚታወስ ነው።

የአሜሪካ ጦር በድጋሚ በሶማሊያ እንዲሰማራ የማድረግ ውሳኔ በ10ኛው የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃሙድ ተቀባይነት ማግኘቱም አይዘነጋም፡፡

ሶማሊያ አሁንም በአልሻባብ እየተፈተነች ነው። በተለይም ከምርጫ ጋር በተያያዘ በሃገሪቱ ፖሊተከኞች መካከል የነበረው ሽኩቻ ለሰላምና ጸጥታ ይሰጥ የነበረውን ትኩረት አላልቶት እንደነበር በርካቶች ያነሳሉ።

የአሁኑ የአሜሪካ እርምጃም ቡድኑን ከማዳከም አንጻር ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተነግሮለታል፡፡

የፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ጽ/ቤትም "ለመረጋጋትና ሽብርተኝነትን ለመዋጋት በምናደርገው ትግል አሜሪካ ወትሮም ቢሆን ታማኝ አጋራችን ናት" የሚል ጽሁፍን በትዊተር ገጹ አጋርቷል፡፡

https://t.me/HgerenewsEthiopia
6.3K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 17:14:32
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባ የ2015 ዓ.ም በጀት 786 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ወሰነ፡፡

ምክር ቤቱ በ2015 ዓ/ም የፌዴራል መንግስት በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ ማሳለፉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ለመደበኛ ወጪ ብር 347 ነጥብ 12 ቢሊዮን ብር፣ ለካፒታል ወጪ ደግሞ 218 ነጥብ 11 ቢሊዮን ብር እንዲሆን ተወስኗል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ለክልል መንግሥታት ድጋፍ ብር 209 ነጥብ 38 ቢሊዮን ብር እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ 12 ቢሊዮን ብር በጀት እንዲያዝ ወስኗል ምክር ቤቱ፡፡

አጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት የ 2015 በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር ሆኖ መቅረቡ ተገልጿል፡፡

በጀቱ ከ2014 በጀት ዓመት ጋር ሲነጻጸር የብር 111 ነጥብ 94 ቢሊዮን ብር ወይም የ16 ነጥብ 59 በመቶ እድገት አለው፡፡

ምክር ቤቱ የ2015 በጀት 786 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር እንዲሆን አጽድቆ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ መወሰኑን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል፡፡

የ 2014 ዓ.ም የፌደራል መንግስት በጀት 561 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር እንደነበር ይታወሳል፡፡

https://t.me/HgerenewsEthiopia
4.6K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 17:07:43
4.0K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 20:57:39
በአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ ከኢትዮጵያ ጋር የጨዋታ መርሃ ግብር ያላት ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር በካይሮ ለመጫወት ጥያቄ አቅርባ እንደነበር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ዋና ጸሐፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን፤ ከወንዶች ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር በሰጡት መግለጫ ግብጽ ከኢትዮጵያ ጋር ለመጫወት ሙሉ ወጪ ለመሸፈን ሃሳብ አቅርባ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ዋና ጸሐፊው "የግብፅ እግርኳስ ፌዴሬሽን ሙሉ ወጪያችሁን እንቻልና ካይሮ ላይ ኑና እንጫወት ብለውናል" ብለዋል፡፡

ሆኖም ይህ የክብር ጉዳይ በመሆኑ ፌዴሬሽኑ ጥያቄውን ውድቅ ማድረጉንም ነው አቶ ባሕሩ ያስታወቁት፡፡

ዋና ጸሐፊው በስም ያልገለጿቸው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን አንድ አመራር "መሐመድ ሳላህን የመሰለ ዓለም አቀፍ ተጫዋች በኢትዮጵያ ስታዲየም እንዲጫወት አንፈቅድም" ሲሉ መናገራቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

አቶ ባሕሩ "አንድ የካፍ አመራር መሃመድ ሳላህን የመሰለ ወርልድ ክላስ ተጨዋች በዚያ ስታዲየም ሄዶ እንዲጫወት የምንፈቅድልህ ይመስልሃል ? ብሎናል" ሲሉም በመግለጫቸው ጠቅሰዋል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ገንዘብ እስካለ ድረስ በውድድሩ እንደሚቀጥል የተናገሩት አቶ ባሕሩ፤ በቀጣይ ግን ውድድሮችን እስከ መሰረዝ የሚደርስ ውሳኔ ሊኖር እንደሚችል ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከግብፅ ጋር በማላዊ ለምታደርገው ጨዋታ የአውሮፕላን ቲኬት የቡድኑ አቅርቦትና አበልን ሳይጨምር እስከ 50ሺህ ዶላር ወጪ እንደሚደረግም ገልጸዋል፡፡

ካፍ ያስቀመጠው መመዘኛ በዲፕሎማሲና በንግግር ሊፈታ እንዳልቻለም ነው ዋና ጸሐፊው የተናገሩት፡፡

"ደረጃውን የጠበቀ ሜዳ ባለመገኘቱ ዋጋ እየከፈለ ያለው ብቸኛ ተቋም ፌዴሬሽኑና ተመልካቹ" እንደሆነም ገልጸዋል፡፡

https://t.me/HgerenewsEthiopia
3.9K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 20:50:07
ፖል ፖግባ በወሩ መጨረሻ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር እንደሚለያይ ተረጋገጠ

ማንችስተር ዩናይትድ ከፖል ፖግባ ጋር ከዚህ ወር መጨረሻ ጀምሮ እንደሚለያይ አረጋገጠ፡፡

ከታዳጊነት ጀምሮ በክለቡ ለነበረው ቆይታና ላበረከተው አስተዋጽዖ ያመሰገነው ዩናይትድ የተጫዋቹ ኮንትራት ከያዝነው ሰኔ ወር መጨረሻ ጀምሮ እንደሚጠናቀቅ አስታውቋል፡፡

ከ7 ዓመታት በፊት በ2016 ከጁቬንቱስ ወደ ዩናይትድ የተመለሰው ፖግባ የካራባኦ እና የአውሮፓ ሊግ ዋንጫዎችን ማንሳቱ ይታወሳል፡፡

https://t.me/HgerenewsEthiopia
3.8K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-01 20:45:23
ህዝባዊ የነጻነት ጦር” ተብሎ የሚጠራው የቻይና ጦር የምስራቃዊ እዝ በታይዋን ዙሪያ የውጊያ ዝግጁነት ልምምዶችን ማካሄዱ ተገለፀ።

የቻይና ጦር የምስራቃዊ እዝ በታይዋን አካባባቢ ያደረገው የውጊያ ዝግጁነት በውሃ ላይ እና በአየር ላይ የተካሄደ መሆኑንም ሲ.ጂ.ቲ.ኤን ዘግቧል።

የወታደራዊ እዙ ቃል አቀባይ ከፍተኛ ኮሎኔል ሺ ዪ በሰጡት መግለጫ፤ የውጊያ ዝግጁነት ልምምዱ የተካሄደው አሜሪካና ታይዋን በቅርቡ በጥምረት እያደረጉ ላለው እንቅስቃሴ በቂ ምለሽ ለመስጠት ነው ብለዋል።

“አሜሪካ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በታይዋን ላይ የተለያየ አቋም እያንጸባረቀች ነው” ያሉት ቃል አቀባዩ፤ “የአሜሪካ እንቅስቃሴ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ለታይዋን ነጻት ድጋፍ ለማድረግ ነው፤ ይህ ደግሞ ታይዋንን አደገኛ ሁኔታ ውስጥ የሚከታት ነው” ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

“ታይዋን የቻይና አንድ አካል ነች” ያሉት ቃል አቀባዩ፤ “ቻይና ጦር ማንኛውንም የውጭ ጣልቃ ገብነት መቀልበስ በሚችልበት መልኩ የማጠናከሪያ ልምምዶችን ማድረጉን ይቀጥላል” ብለዋል።

“ታይዋንን ነጻ ሀገር እናደርጋለን የሚሉ ገንጣዮችን እንሰብራለን” ሲሉም ኮሎኔል ሺ ዪ ተናግረለዋል።

ቻይና ባሳለፍነው ሳምንትም “ለአሜሪካ ከባድ ማስጠንቀቂያ ነው” ያለችውን ወታደራዊ ልምምድ በታይዋን አቅራቢያ ማድረጓ ይታወሳል።

ታይዋን የግዛቴ አንድ አካል ናት የምትለው ቻይና በታይዋን ጉዳይ ከአሜሪካ ጋር ጭምር በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ ስትገባ ይታያል።

ባሳለፍነው ሳምንት በእስያ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኀገራቸው ታይዋንን ለመጠበቅ ኃይል ልትጠቀም እንደምትችል መናገራቸው ይታወሳል።

https://t.me/HgerenewsEthiopia
3.4K viewsሀገሬ𝑛𝑒𝑤𝑠𝑒𝑡ℎ𝑖𝑜𝑝𝑖𝑎 , 17:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ