Get Mystery Box with random crypto!

በምትችላቸው ጉዳዮች ላይ አተኩር እና እነሱን ለመፍታት እቅድ አውጣ። በሥራ ላይ ችግር ካጋጠመዎት | ሄሎ ዶክተር 👂👂👂🏥

በምትችላቸው ጉዳዮች

ላይ አተኩር እና እነሱን ለመፍታት እቅድ አውጣ። በሥራ ላይ ችግር ካጋጠመዎት፣ አስተዳዳሪዎን ለማነጋገር ይሞክሩ። ከልጆችዎ ወይም ከትዳር ጓደኛዎ ጋር ግጭት እያጋጠመዎት ከሆነ ችግሩን ለመፍታት እርምጃዎችን ይውሰዱ። የጭንቀት መንስኤዎችን ያስወግዱ። በሚችሉበት ጊዜ ቀስቅሴዎችን ለማስወገድ ይሞክሩ። ለምሳሌ፣ ወደ ሥራ በሚሄዱበት መንገድ ላይ የሚበዛው የሰዓት ትራፊክ ውጥረት የሚያስከትል ከሆነ፣ በጠዋት ቀድመው ለመሄድ ይሞክሩ ወይም በሕዝብ ማመላለሻ ይውሰዱ። ከተቻለ ለጭንቀት የሚዳርጉዎትን ሰዎች ያስወግዱ። ለመዝናናት እና የሚወዷቸውን እንቅስቃሴዎች ለማድረግ ጊዜ ይመድቡ። በጸጥታ ለመቀመጥ እና በጥልቀት ለመተንፈስ በየቀኑ ጊዜ ይውሰዱ። በጊዜ መርሐግብርዎ ውስጥ ለአስደሳች እንቅስቃሴዎች ወይም በትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎች ጊዜ ይስጡ፣ ለምሳሌ በእግር መሄድ፣ ምግብ ማብሰል ወይም በጎ ፈቃደኛነት። ምስጋናን ተለማመዱ። ለሌሎች ምስጋናን መግለጽ ጭንቀትን ለመቀነስ ይረዳል።

9. የደም ግፊትዎን በቤትዎ ይቆጣጠሩ እና ዶክተርዎን በየጊዜው ይጎብኙ

➥ የቤት ውስጥ ክትትል የደም ግፊትዎን እንዲከታተሉ፣ የአኗኗር ለውጦችዎ እየሰሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ እና እርስዎን እና ዶክተርዎን ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ችግሮችን ሊያስጠነቅቅዎት ይችላል። የደም ግፊት መቆጣጠሪያዎች በሰፊው እና ያለ ማዘዣ ይገኛሉ። ከመጀመርዎ በፊት ስለ ቤት ክትትል ከሐኪምዎ ጋር ይነጋገሩ። የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ከሐኪምዎ ጋር አዘውትሮ መጎብኘት ቁልፍ ነው። የደም ግፊትዎ በደንብ ከተቆጣጠረ ምን ያህል ጊዜ መመርመር እንዳለቦት ከሐኪምዎ ጋር ያረጋግጡ። ሐኪምዎ በየቀኑ ወይም ባነሰ ጊዜ እንዲፈትሽ ሊጠቁም ይችላል።

10. ድጋፍ ያግኙ

➥ ድጋፍ ሰጪ ቤተሰብ እና ጓደኞች ጤናዎን ለማሻሻል ይረዳሉ። የደም ግፊትዎን ዝቅተኛ ለማድረግ ራስዎን እንዲንከባከቡ፣ ወደ ሐኪም ቤት እንዲወስዶት ወይም ከእርስዎ ጋር የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ፕሮግራም እንዲጀምሩ ሊያበረታቱዎት ይችላሉ። ይህ ስሜታዊ ወይም ሞራልን ሊሰጡዎት ከሚችሉ እና ሁኔታዎን ለመቋቋም ተግባራዊ ምክሮችን ከሚሰጡ ሰዎች ጋር እንዲገናኙ ያደርግዎታል።
▬▬ Share ▬▬▬

«ስለአጥንትዎ ጥንካሬ አስበው ያውቃሉ?»

ለመሆኑ ስለአጥንትዎ ጥንካሬ አስበው ያውቃሉ? አመጋገባችንም ሆነ የአኗኗር ዘይቤያችን ከሰውነታችን ክፍል ጠንካራ በሚባለው አጥንት ላይ ሊያስከትለው የሚችል እክል እንዳለስ?

አጥንት ከሰውነት ክፍል ጠንካራው ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች ጥንካሬውን ሊያጣ እንደሚችል የአጥንት ህክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። አጥንት ጥንካሬውን ጤናማ በሆነ መልኩ ጠብቆ እንዲዘልቅ በአመጋገብም ሆነ በቂ የሰውነት እንቅስቃሴ በማድረግ መርዳት እንደሚያስፈልግም ይመከራል።  ከዕድሜ መግፋት ጋር በተገናኘ የአጥንት ጥንካሬ ማጣት ወይም መሳሳት እንደሚያጋጥም ቢታመንም ችግሩ በወጣትነት ዕድሜ ሲያጋጥም መንስኤውን ለማወቅ ሊደረጉ የሚገባቸው ምርመራዎች እንዳሉ የዘርፉ ሀኪሞች ይመክራሉ።

«የአጥንት መሳሳት ታምሜ ነው፤ ዕድሜዬ 26 ነው፤ የዩኒቨርሲቲ ሌክቸረር ነኝ ሥራ መሥራት አልቻልኩም፤ እባካችሁ አጭር መፍትሄ ብታመላክቱኝ?» የሚለው መልእክት ከአድማጫችን ሩሃማ  ነው በኢሜይል አድራሻችን የደረሰን። የዩኒቨርሲቲ መምህርት መሆኗን የገለጸችልን እና በወጣትነት የዕድሜ ክልል የምትገኘው ጠያቂያችን፤ ጥያቄያዋን ከዓመታት በፊት ስለአጥንት ጤንነት ያቀረብነውን መሰናዶ ከድረገጻችን በመውሰድ አያይዛዋለች።  መምህርት ሩሃማ ስለምትከታተይን በቅድሚያ እናመሰግናለን። ጥያቄሽን በምሥራቅ ጀርመን ድሬዝደን ከተማ አጥንት እና መገጣጠሚያ ላይ የሚያጋጥሙ የጤና ችግሮችን በሚመለከት የሕክምና ዘርፍ ለረዥም ዓመታት በከፍተኛ ሃኪምነት በማገልገል ላይ ለሚገኙት ዶክተር ውብታየ ዱሬሳ ተክሌ፤ አቅርበናል። ዶክተር ውብታየን ለመሆኑ የአጥንት መሳሳት ምንድነው አልናቸው።



«የአጥንት መሳሳት ኦስቲዮፖሮሲስ እንለዋለን ፤ ይኽም ማለት የአጥንት ጥንካሬው መለስለስ ነው። ምክንያቱም አጥንታችን በየቀኑ ይገነባል፤ በአንድ በኩል ደግሞ የተገነባው ይፈርሳል። ግን በብዛት የሚበልጠው መገንባቱ ነው። መገንባቱ ሚዛኑን ጠብቆ ከሆነ የአጥንት ጥንካሬውን አያጣም። የአጥንት ዴንሲቲው ነው ዋናው። ዴንሲቲው ማለት የአጥንቱ አሠራሩ ጠበቅ ያለ ሲሆን፤ በአንድ በኩል እየተገነባ በአንድ በኩል ሲፈርስ የአጥንታችን ጥንካሬው ጤናማ ይሆናል። የማፍረሱ ሂደት ሲያይል በዚያን ጊዜ ነው የአጥንት መለስለስ የሚመጣው።»

አጥንት ከሰውነት ክፍላችን ጠንካራ የሚባለው መሆኑ ነው የዘርፉ ምሁራን የሚገልጹት። ለመሆኑ የአጥንት መለስለስ በምን ምክንያት ይመጣል? ችግሩ በሴቶችም ሆነ በወንዶች ላይ ሊከሰት እንደሚችል በማስገንዘብ ባለሙያው  በርከት ምክንያቶቹን ይዘረዝራሉ። የአጥንት መሳሳትን ሊያስከትሉ ከሚችሉ ምክንያቶች ዕድሜ አንዱ ነው። ጥያቄው የተላከልን ግን በወጣትነት የዕድሜ ክልል ከሚገኙ የዩኒቨርሲቲ መምህርት ነው። በወጣትነት ይኽ ችግር ሲያጋጥም መንስኤ ሊሆን የሚችለው ምን ይሆን ብለናል ለአጥንት ህክምና ከፍተኛ ባለሙያው።



 ወደ ህክምናው ለመድረስ ግን በመጀመሪያ የአጥንት መሳሳት እንዲከሰት ምክንያት የሆነውን እንከን በደም ምርመራም ሆነ ተያያዥ ይኽን ችግር መለየት በሚያስችሉ ምርመራዎች ተለይቶ መረጋገጥ እንደሚኖርበት ነው ዶክተር ውብታየ አጽንኦት የሰጡት። የቫይታሚን ዲ እና የካልሺየም እጥረት፤ እንዲሁም የእንቅርት በሽታ ለዚህ አይነተኛ መንስኤዎች ሊሆኑ እንደሚችሉም በዋናነት አሳስበዋል። የአጥንት መሳሳት ችግሩ መጠነኛ ከሆነ በምግብ ማለትም ቫይታሚን ዲ ያላቸውን በመመገብ፣ በካልሺየም የበለጸጉትንም በማዘውተር፤ በዚያም ላይ እንቅስቃሴን አዘውትሮ በማድረግ ጥንካሬውን ማሻሻል እንደሚቻልም የአጥንት እና መገጣጠሚያ ህክምና ባለሙያው መክረዋል። በ26 ዓመት የአጥንት መሳሳት ችግር መከሰቱ የተለመደ አይደለም ያሉት ዶክተር ውብታየ የአካል እንቅስቃሴ ለማድረግ ቀስ በቀስ መጀመር እንደሚገባም ይመክራሉ።