Get Mystery Box with random crypto!

ነስር (Epistaxis) ነስር (epistaxis) ድንገተኛ የሆነ አስደንጋጭ ከአፍንጫ ደም | ሄሎ ዶክተር 👂👂👂🏥

ነስር (Epistaxis)


ነስር (epistaxis) ድንገተኛ የሆነ አስደንጋጭ ከአፍንጫ ደም መፍሰስ ሲሆን በአብዛኛው ለከፋ አደጋ የማይዳርግ የሕመም ዓይነት ነው፡፡ነስርን ከሚነሳበት ክፍል በመነሳት በሁለት ይከፈላል፡፡

1, ከፊተኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Anterior Nosebleeds)
ከአፍንጫ ቀደዳዎች መካከል አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች ሲጎዱ የሚከሰት ሲሆን ከ90 በመቶ በላይ ለሚከሰት የነስር ዓይነት ምክንያት ነው፡፡አብዛኛዉን ጊዜ ህፃናት ላይ ይከሰታል እንዲሁም በቀላሉ መቆጣጠር ይቻላል፡፡
2, ከኋለኛው የአፍንጫችን ክፍል የሚመጣ ነስር (Posterior Nosebleeds)
በአብዛኘው በዕድሜ በገፉ ሰዎች ላይ ይከሰታል፡፡ ወደ ዉስጥ ካሉ የደም ስሮች የሚመጣ መጠኑ በዛ ያለ ደም ይኖረዋል እናም የተለየ ሕክምና የሚያስፈልገው እና ውስብስብ ነው፡፡

ነስርን የሚያመጡ መንስኤዎች

በአፍንጫ ላይ አደጋ/ አፍንጫ መጎርጎር
የደም ግፊት መጨመር
የደም መርጋት ችግር
የደም ማቅጠኛ መድሐኒቶች
የመተንፈሻ አካላት ህመም
ቀዘቃዛ እና ደረቅ የአየር ንብረት
ለኬሚካል ተጋላጭ መሆን
አልኮል እና በአፍንጫ የሚወሰዱ አደንዛዥ እጽ
እርግዝና

ነስርን መከላከያ መንገዶች

በአብዛኛው ነስር የሚከሰተው በቀዘቀዘ እና በደረቅ የአየር ንብረት ስለሆነ አፍንጫ እንዳይደርቅ ቫዝሊን (Petroleum jelly) መጠቀም
አፍንጫዎን በጣትዎ አለመነካካት
የነስር መንስኤ ከሌላ የጤና ችግር ጋር ተያያዥነት ካለው ሐኪም ማማከር
ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ


ነስር ከተከሰተ በኋላ ወደ ሐኪም መሄድ የሚያስፈልገው መቼ ነው?

አፍንጫዎን ለ10 ደቂቃ ያህል ይዘው ቆይተው ነስሩ ካልቆመ
ወዲያዉኑ ወዲዉኑ በተደጋጋሚ የሚነስር ከሆነ
ለነስሩ ጋር ተያይዞ ደም ማስመለስ ካለ
ራስ ማዞር ወይንም ራስ መሳት ካለዉ
ከፍተኛ ትኩሳት ካለ
የልብ ምት የሚጨምር ከሆነ እና ለመተንፈስ መቸገር ካለ
ሰውነት ላይ ሽፍታ/መበለዝ ካለ
ከአፍንጫ ሌላ ከሌሎች የሰውነት ክፍሎች ደም መፍሰስ ካለ
ደምን ለማቅጠን የሚጠቅሙ መድኃኒቶችን የሚወስዱ ከሆነ
የደም መርጋትን የሚያስተጓጉሉ ማንኛውንም ዓይንት ሕመም ካለ
የኬሞቴራፒ ሕክምና በቅርቡ ወስደው ከነበረ

ነስርን ማቆሚያ

ከጭንቅላትዎ ጎንበስ ማለት (ጭንቅላትን ወደ ላይ ቀና ማድረግ የሚፈሰውን ደም ወደ ጉሮሮ በማምጣት ጉዳት ያስከትላል)
ቀጥ ብለው መቀመጥ
ሁለቱም የአፍንጫ ቀዳዳዎች በአውራ ጣት እና በጠቋሚ ጣት ግጥም አድርጎ ለአስር ደቂቃ ይዞ ማቆየት
በአፍ የሚመጣን ደም መትፋት
ነስሩ ካቆመ በኋላ አፍንጫዎን አለመነካካት
ቢያንስ ለ24 ሰአታት ያህል ሞቅ ያሉ መጠጦችን አለመጠቀም

የነስር ህክምና


ደም በሚፈስበት ቦታ የአፍንጫ addrenaline ወይም ስፖንጅ ማስገባት እና ከ 24-48 ሰአት ማቆየት(የሚገባዉም ሆነ የሚዎጣዉም በጤና ባለሙያ እርዳታ ነዉ፡፡)
ለደም መርጋት የሚሆኑ መድሀኒቶች
የተቀደዱ የደም ስሮችን ካሉ በኬሚካል(ሲሊቨር ናይትሬት በመጠቀም) እና በቀዶ ህክምና ማስተካከል