Get Mystery Box with random crypto!

ብዙዎቹ ምንም ምልክት ባይኖራቸውም ፥ የእንቁላል እጢዎች በተለይም የፈነዱ ከሆነ ከባድ ምልክቶች | ሄሎ ዶክተር 👂👂👂🏥

ብዙዎቹ ምንም ምልክት ባይኖራቸውም ፥ የእንቁላል እጢዎች በተለይም የፈነዱ ከሆነ ከባድ ምልክቶች ሊያስከትሉ ይችላሉ ፡፡ በመጀመሪያ ጤንነትዎን ለመጠበቅ መደበኛ የማህፀን ምርመራዎችን ያካሂዱ እና ከባድ ችግርን ሊጠቁሙ የሚችሉ ምልክቶችን ይወቁ ።

ድንገተኛ፣ ከባድ የሆድ ህመም፣
ትኩሳት ወይም ማስታወክ ያለው ህመም ካልዎት።

እነዚህ ምልክቶች እና በተጨማሪ የቆዳ መቀዝቀዝ፣ፈጣን መተንፈስ እና ራስ ምታት ወይም ድክመት ካሎት ወዲያውኑ ዶክተሮን ያነጋግሩ።

የእንቁላል እጢ ሕክምና

ሕክምናው በእድሜዎ ፣ ሲስቱ ዓይነት እና መጠን እና በምልክቶችዎ ላይ የተመሠረተ ነው ፡፡

የህክምና ክትትል በጥቂት ወራቶች ውስጥ ሲስቱ የሚጠፋ መሆኑን ለማየት ብዙ ጊዜዎችን መጠበቅ እና እንደገና መመርመር ይችላሉ ፡፡ ይህ የመጀመሪያው አማራጭ ሲሆን ዕድሜዎ ምንም ይሁን ምን ምልክቶች ከሌሉዎት እና የአልትራሳውንድ ምርመራ ቀላል ፣ ትንሽ ፣ በፈሳሽ የተሞላ ሲስት እንዳለዎት ካሳየ ይሄ መንገድ ይመረጣል። ሲስትዎ መጠን ይለወጥ እንደሆነ ለማየት ዶክተርዎ በየተወሰነ ጊዜ የክትትል አልትራሳውንድ እንዲያገኙ ሊመክርዎ ይችላል ፡፡

መድሃኒት የእንቁላል እጢዎች እንዳይደገሙ ለማድረግ ዶክተርዎ እንደ የወሊድ መቆጣጠሪያ ክኒን ያሉ ሆርሞናዊ የወሊድ መከላከያዎችን ሊመክር ይችላል ፡፡ ሆኖም የወሊድ መከላከያ ክኒኖች አሁን ያለውን ሲስት አይቀንሱም ፡፡

ቀዶ ጥገና ትልቅ ፣ የሚያድግ ፣ በሁለት ወይም በሶስት የወር አበባ ዑደትዎች የማይጠፋአ እና የማይቀንስ ፣ ህመም የሚያስከትለ ወይም እንደ መፈንዳት እና በ እራሱ ላይ ተጠምጥሞ ደም ወደ እንቁላል እንዳይሄድ የሚከለክል ከሆነ በቀዶ ጥገና መውጣት ይኖርበታል፡፡

ኦቫሪን ሲስት(የእንቁላል እጢን)እንዳለብዎ ከተመረመሩ እና እርጉዝ ለመሆን እየሞከሩ ከሆነ በተለምዶ የመራባት ችግር እንደማያስከትሉ ማወቅ አስፈላጊ ነው ፡፡ ሆኖም ግን ከተለመደው የ እጢn አፈጣጠር ወጣ ያለ ከሆነ እርግዝና እንዳይፈጠር ሊያደርጉ የሚችሉበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል።