Get Mystery Box with random crypto!

#ሰውነታችን ማንኛውንም ነገር ለመከወን ለምሳሌ ለመናገር፡ ለማሰብ፡ ለማየት፡ ለመንቀሳቀስም ሆነ ለ | ሄሎ ዶክተር 👂👂👂🏥

#ሰውነታችን ማንኛውንም ነገር ለመከወን ለምሳሌ ለመናገር፡ ለማሰብ፡ ለማየት፡ ለመንቀሳቀስም ሆነ ለሌላ ነገር ኤቲፒ(ATP) የሚባል ንጥረ ነገር ይፈልጋል። ይህ ደግሞ የሚመረተው የበላነውና የጠጣነው ውጤት የሆነው ግልኮስ በኦክስጅን ሲቃጠል የሚገኝ ነው።

ኦክስጅንና ግልኮስ በተለያየ መልክ በሰውነት
ውስጥ በበቂ ሁኔታ ከለለ ሾክ እንድፈጠር ያደርጋል።

#የሾክ አይነቶች
ብዙ ናቸው።
• ከሳንባ ችግር የሚመጣ ኒሞጀኒክ
• ከነርቭ ችግር የሚመጣ ኒውሮጀኒክ
• ከልብ ችግር የሚመጣ ካርድኦጀኒክ
• በኢንፌክሽን የሚመጣ ሴፕቲክ ሾክ
• ከደም ቱቦ መስፋት የሚመጣ ቫዞጀኒክ
• ከፈሳሽ ማነስ የሚመጣ ሀይፓቮለሚክ ሾክ
• ከደም መፍሰስ የሚመጣ ሄሞረጅክ ሾክ
• በአላርጅክ የሚመጣ አናፕላፕቲክ ሾክ
• ከስኳር መጠን መጨመርና መቀነስ የሚመጣና ሌሎችም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
#የሾክ ምክናየቶች
• በቂ ፈሳሽና ምግብ አለመውሰድ
• መድማት
• ተቅማጥና ትውከት
• ከባድ ትኩሳትና ላብ
• የስኳር መጠን መውረድና መጨመር
• የልብ ችግር
• ፍራቻና ጭንቀት
• የአየር ቱቦ መዘጋት
• አደጋ
• የደም ቱቦ መስፋት
• ኢንፌክሽን
• አላርጅክ
• የደም ግፊት መውረድ
#የጋራ የሆኑ የሾክ ዋና ዋና ምልክቶች
1. የመጀመሪያው አካባቢ
#ዋናው ምልክት የደም ግፊት 90/60mmHg በታች ሲሆንና የሚከተሉት ሲታዩ ነው።
• ማቅለሽለሽና ማስታወክ
• የራስ ማዞርና እራስ ምታት
• የሰውነት መቀዝቀዝ ከሙቀት ስሜት ጋር
• ጭንቀት
• ግራ መጋባት
• ብጅታ ከአይን ጭልም ጭልም ማለት ጋር
• የአይን ወደ ውስጥ መግባት ወይም መጎድጎድ
• አይን ሰማያዊ መሆን
• የቆዳ መገርጣት
• የልብ ትርታ መጨመር
• ትንፈሳ መጨመር
• የሰውነት ሙቀት መቀነስ
• የደም ግፊት መውረድ
2. እየቆየ ሲሄድ
• እራስን መሳት
• ትንፈሳ መቀነስ
• ሙቀት መውረግ
• ግፊት መቀነስ
• የልብ ትርታ መቀነስ
#የሾክ ህክምና
1. የአየር ቱቦ እንድከፈት ማድረግ
2. ትንፈሳን ማስተካከል
3. የደም ዝውውርን ማስተካከል
4. የችግሩን ምንጭ ለይቶ ማከም
5. የጉዳተኛውን አቀማመጥ ማስተካከል
6. ፈሳሽ መስጠት
7. ሙቀት ማስተካከል
8. ሲነቃ ስለሾክ ማስተማር
#ውድ የኢንፎ ሄልዝ ቤተሰቦች ከ1-8 ለተዘረዘሩት የሾክ ህክምናዎች በቂ ማብራሪያ ይዘን እንመለሳለን።


#የኮሶትል

• የኮሶ ትል በዋናነት አንጀትን የሚያጠቃ ትላትል ነው። ከአጀት ውጭ ወደተለያየ የሰውነት ክፍልም ሊሰራጭ ይችላል።

አንድ ሰው የኮሶ ትል አለበት የሚባለው በአንጀት ውስጥ የኮሶ ትል መኖሩ ሲረጋገጥ ነው።

ያደገ የኮሶ ትል እስከ 80 ጫማ ወይም 25 ሜትር ያህል ቁመት ሲኖረው በእድሜም በሰውነት ውስጥ እስከ 30 አመት ሊቆይ ይችላል።

• የኮሶ ትል እጭ ወይም ጉልምስ ከምግብና ውሀ ጋር በመቀላቀል በአፍ በኩል ወደ ሰውነት ይገባል። እጩ ወይም ጉልምሱ ከተወሰነ ጊዜ በሗላ ወደ ሙሉ አዋቂ ትልነት ይቀየራል።
እጩ ወይም ጉልምሱ ከአንጀት በተጨመሪ በሌላ የሰውነት ክፍል ላይም ሊኖርና ሊሰራጭ ይችላል።

• የኮሶ ትል እራስ፡ አንገትና የተከፋፈለ የሰውነት ክፍል አለው። እራሱን ከአንጀት ግድግዳ ጋር ያጣብቅና በሰውነት አካሉ እንቁላሉን በመፍጠር ያሳድጋል።

• በኮሶ ትል የሚመጣ ኢንፌክሽን ብዙ ጊዜ ቀለል ያለ ኢንፌክሽን ነው። በተለይ የትሎቹ ብዛት ከሁለት ካልበለጠ ነው። የትሉ ብዛት ከሁለት በላይ ከበለጠ ህመሙ ሊከብድ ይችላል።

#የኮሶትል_ምልክት
• አብዛኸኛው ሰው ምልክት አያሳይም። ቀሪዎቹም ቢሆኑ በኮሶ ትሉ አይነትና በተቀመጠበት የሰውነት ክፍል ይወሰናል።

#እንደ አጠቃላይ ግን
• ማቅለሽለሽ
• ድካም
• የምግብ ፍላጎት ማነስ
• የሆድ ህመም
• ተቅማጥ
• ድብርት
• ጨው የመፈለግ ስሜት
• ክብደት መቀነስ
• የምግብ ልመት ችግር

#እጩ ወይም ጉልምሱ ከአንጀት ውጭ ያለ የሰውነት ክፍል የሚያጠቃ ከሆነ
• የራስ ምታት
• እባጭ
• ማሳከክ / አላርጅክ
• የነርቭ ችግር በተለይ እንደሚጥል በሽታ አይነት ውስሜት ይኖራል።

#ምክንያቱ
• ከምግብና ውሀ ጋር የኮሶ ትል እጭ ወይም ጉልምስ ወደ ሰውነት መግባቱ ነው።

#ለኮሶትል የሚያጋልጡ ነገሮች
• ንፅህናን አለመጠበቅ
• ከእንስሳቶች ጋር ያለ ንክኪ
• ታዳጊ ሀገር ላይ መኖር
• ጥሬና ያልበሰለ ስጋ መብላት

#ካልታከመ
• የአንጀት መዘጋት
• የነርቭና አንጎል ተግባር መስተጓጎል
• የሰውነት አካላትን ተግባር ማስተጐጎል ያስከትላል።

#መከላከያው
• ንፅህናን መጠበቅ
• ከእንስሳት ጋር ያለን ቅርበትና ንክኪ ማስወገድ
• ከሽንት ቤት መልስ እጅን በአግባቡ መታጠብ
• ምግብን ማጠብና ማብሰል
• ውሀን አፍልቶ መጠቀም
• ጥሬ ስጋ ለመጠቀም ከተፈለገ ባያስተማምንም ቢያንስ ማቀዝቀዝ
• ስጋን ማብሰል
• የከበት፡ በግ፡ ፍየል፡አሳማና አሳ ስጋን ሳያበስሉ አለመጠቀም
• ውሻ በኮሶ ትል የመጠቃት እድል ስላለው ተከታትለው ማሳከም።
#ውድ የኢንፎ ሄልዝ ሴንተር ቤተሰቦች ስለህክምናውና ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ ያማክሩን! ያግኙን።
• በአካል ሊያገኙን ካሰቡ Info Health Center በሚለው የቴሌግራም ቻናል ላይ ገብተው በሚያገኙት ቻት ሊንክ መመዝገብን አይርሱ።



ኦቫሪን ሲስት የእንቁላል እጢን ስንል ምን ማለታችን ነው።



ኦቫሪን ሲስት ማለት በሴቶች እንቁላል ውስጥ ወይም በላዩ ላይ ፈሳሽ የተሞሉ ከረጢቶች ወይም ኪሶች ናቸው ፡፡ ሴቶች በእያንዳንዱ የመሀፀን ጎን ላይ እያንዳንዳቸው የ ለውዝ መጠን እና ቅርፅ ያላቸው ሁለት እንቁላሎች አሏቸው ፡፡

በእነዚህ እንቁላል ውስጥ በየወሩ የሚያድጉ እንቁላሎች (ኦቫ) ሲኖሩ ወርሃዊ በሆነ ኡደት ይለቀቃሉ አንዳንድ ግዜ ግን እንቁላሎቹ ሳይለከኩ የቀርና እዛው ውሃ በመያዝ እነዚህን ከረጢቶች የፈጥራሉ ማለት ነው ፡፡ በዚህም ምክያት የመውለድ እድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ብዙ ሴቶች በተወሰነ ጊዜ የእንቁላል እጢ የኖራቸዋል ተበሎ የገመታል ፡፡ አብዛኛዎቹ የእንቁላል እጢዎች እምብዛም ምቾት የማየነሱ እንዲሁም ምንም ጉዳት የላቸውም ሲሆኑ ብዙዎች በጥቂት ወራቶች ውስጥ ያለ ህክምና ይጠፋሉ ፡፡

ኦቫሪን ሲስት(የእንቁላል እጢን) መንስኤዎች

1. የሆርሞን መዛባት ዋናው እና ቀዳሚው ሲሆን ለዚህም ነው አነስ ላሉ እጢዎች የ እርግዝና መከላከያ ሚታዘዘው።

2 እርግዝና ፥ እርግዝና ሲፈጠር የተለቀቀው እንቁላል
ከረጢት ላይተፋ ሰለሚቸል እዛው በሚፈጠሩ የሆርሞን ፈሳሾች በመሞላት ይህ እጢ ሊፈጠር ይችላል።

3. ኢንዶምትሪዮሲስ የሚባል ችግር ሲሆን ይህ ሁኔታ ከማህፀን ውጭ የማህፀን ግድግዳ እንዲያድጉ የሚያደርግ ችግር ሲሆን የተወሰኑት የ ማሃፀን ግርግዳ አካላት ከኦቫሪዎ ጋር ተጣብቀው እድገትን እንዲፈጥሩ በማድረግ እጥው እንዲፈጠር ያደርጋል።

3.ከባድ የመሃፀን ህመም ኢንፌክሽኑ ወደ እንቁላሉ ከተዛመተ እነዝህን ወሃየቋጠሩ ከረጢቶች ሊያስከትል ይችላል ፡፡

4. የቀድሞው የእንቁላል እጢ ከዝህ በፊት አንድ ሲስት ካለዎት ከዚህ በኃላ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ ነው።

ምልክቶች

አብዛኞቹ ኦቫሪን ሲስት(የእንቁላል እጢን) ምልክቶች አያስከትሉም እናም በራሳቸው ይጠፋሉ ፡፡ ሆኖም አንድ ትልቅ የእንቁላል እጢ ሊያስከትል የሚችሉት ምልክቶች-

የመሀፀን ህመም - በ እጢው በኩል በታችኛው የሆድ ክፍል ውስጥ ሚጠዘጥዝ ወይም የውጋት ስሜት

የሆድ መነፋት ወይም የመክበድ ስሜት

በፔርየድ ግዜ ከበፊቱ የበለጠ ህመም ስሜት መኖር እና የፔርየድ መዝዛባት ናቸው።

ዶክተር መቼ ማየት ይርኖረብናል