Get Mystery Box with random crypto!

Healing School Official

የቴሌግራም ቻናል አርማ healing_schooll — Healing School Official H
የቴሌግራም ቻናል አርማ healing_schooll — Healing School Official
የሰርጥ አድራሻ: @healing_schooll
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.74K

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-06-22 21:24:33 ምድርን የሚያናውጡ ነገሮች

ምሳሌ 30
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²¹ በሦስት ነገር ምድር ትናወጣለች፥ አራተኛውንም ትሸከም ዘንድ አይቻላትም።
²² ባሪያ በነገሠ ጊዜ፥ ሰነፍም እንጀራ በጠገበ ጊዜ፥
²³ የተጠላች ሴት ባል ባገኘች ጊዜ፥ ሴት ባሪያም እመቤቷን በወረሰች ጊዜ።

በዚህ ክፍል ድንቅ የሆኑ ነገሮች እናያለን።

ምድር ሚትናወጠው "ባሪያ በነገሠ ጊዜ" ይላል። ባርያ ከነገሠ መግዛት የሚፈልገው እራሱን እንደ ንጉሥ ሌሎችን ሁሉ እንደ ባርያ አድርጎ በማሰብ ነው። እንደ ተቸገረ ፣ እንድትቸገር ይፈልጋል። ትላንት ባርያ የሆነላቸውን ሰዎች የመበቀል ከፍተኛ ድርጊት በአገዛዙ ይታያል። ብቻ ትልቅ ችግር ይኖራል።

ምድር ሚትናወጠው " ሰነፍ እንጀራን በጠገበ ጊዜ" ይላል። ሰነፍ እንጀራን ስጠግብ ፣ ትልቁ ችግር ጥጋብ መቆጣጠር አለመቻሉ ነው። ሰነፍ ከጥጋብ ይልቅ ፣ ረሃብን ነው መቋቋም የሚችለው። ትልቁ ችግር ፣ ሰነፍ ከጠገበ አምላኩንም ልረሳ ይችላል። በነገራችን ላይ ሰነፍ ፣ በምጠግብበት ጊዜ ፣ ሰው ሁሉ ከእሱ ጋር ከረሃብ ወደ ጥጋብ የመጣ ይመስለዋል። ሰነፍ ከጠገበም ችግር ነው።

ምድር ሚትናወጠው "የተጠላች ሴት ባል ባገኘች ጊዜ"
ይላል። የተጠላች ባል ባገኘች ቀን ፣ ትላንት ባል ፣ ባለማግኘቷ እራሷን የተጠላው ነኝ ፣ ስትል ስለነበረች ፣ ዛሬ ደግሞ ባል ስታገኝ ፣ ለሎቾ ደግሞ ባል ያላገቡትን ፣ የተጠሉ ናቸው ብላ ማለቷ ነው ትልቅ ችግር የምሆነው።
የተጠላች ባል ስታገኝ በባሏ የመመካት ባህር ልታይባት ይችላል። ትላንትና የተገላሽ ነሽ ፣ ያልዋትን ሰዎች ፣ የመናገር ከፍተኛ የስድብ መንፈስ ልገለጥባት ይችላል።
ችግር ፈጣሪ ትሆናለች ሰፍረ ውስጥ።

ምድር ሚትናወጠው "ሴት ባሪያም እመቤቷን በወረሰች ጊዜ" ይላል። እኸ በጣም ከባድ ነው። ሴት ባሪያም እመቤቷን በወረሰች ጊዜ ማለት ትላንት ተገዢ የነበረች ፣ ዛሬ ግን ገዢ የሆነች ማለት ነው። ትላንት ስትታዘዝ ነበር ዛሬ ደግም የሚታዝ ማለት ነው። እመቤቷን የወረሰችው ባሏን ፣ ንብረቷን ፣ ቤቷን ወይ ደግሞ የእመቤቷ ባለቤትነት የተረጋገጠበትን አንድ ነገር ልሆን ይችላል። ትላንት እመቤቷ ፣ ከስቸገረቻት በእጥፍ ነው ዛሬ እመቤቷን የሚታሰቃየው።
ትልቁ ችግር እመቤቷ በሕይወት እንድትኖር ላትፈቅድ ሁሉ ትችላለች ፣ ምክንያቱ ውርሱ እንድፀናላት ስለሚትፈልግ ማለት ነው። አደገኛ የምድ መናውጥ ይሆናል በዚህ ጊዜ።

ምድርን የሚያናውጡ ነገሮች አናድርግ በጌታ
ምድርን የሚያረጋጉ ነገሮችን እናድርግ
4.6K viewsDegisew, 18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 09:44:51 የጌታ ልጅ
ዘማሪ ኤፍሬም አለሙ

የጌታ የጌታ ልጅ
የኢየሱስ ልጅ ቀና በል እንጂ
የአባቴ የአምላኬ ልጅ
የኢየሱስ ልጅ ኮራ በል እንጂ

ጠላት ሲቆዝም ያቀርቅር እንጂ
ቀና ቀና በል የጌታ ልጅ
እርሱን ለፈራው ላከበረው
እስከ ሺህ ትውልድ በረከት ነው
ጌታን ተማምኖ የለም ዝምታ
በእርግጥ ተሰብሯል ይመለክ ጌታ

ከዚህ በፊት የለመድኩት
የጠየኩት ያሳየሁት ነገር (፪x)
ዞሮ ገባ እጄ ገባ
አልቀረብኝ እግዚአብሔር ሲናገር ነገር
ዙፋኑ ስር መቅደሱ ስር
ማደሪያው ስር ስለምነው ውዬ (፪x)
አላፈርኩም አልከሰርኩም
ተሳካልኝ ጌታ ጌታን ብዬ (፪x)

ብዬማ ጌታ አለ ብዬ
ብዬማ ታለምአልኜ
ብዬማ ነገር ተሳካ
ብዬማ እርሱን ለምኜ

የኢየሱስ ውለታው የበዛባችሁ
ቅኔን ተቀኙለት እልል ብላችሁ
ለክብሩ የሚሆን አምጡ ምሥጋና
እስቲ ጨምሩለት ቅዱስ ነውና

ደግሞ ለጌታ የምን ዝምታ
ደግሞ ለጌታ ከበሮ ይመታ
ደግሞ ለጌታ ሳመልከው ውዬ
ደግሞ ለጌታ ሳመልከው ይነጋ

የጌታ የጌታ ልጅ
የኢየሱስ ልጅ ቀና በል እንጂ
የአባቴ የአምላኬ ልጅ
የኢየሱስ ልጅ ኮራ በል እንጂ

መንግሥተ ሠማይ የጀግና አገር
የእኛም አገር ነች በዚያ እንድንኖር
በምድር መቶ እጥፍ በላይ ደስታ
ትልቅ ዕድል ነው መሆን የጌታ
አክሊል ያገኛል ድል ያነሳው
ለእግዚአብሔር ኖሮ የጨረሰው

ኢየሱሴን ተቀብሎ
. (1) . ጌታ ንጉሥ ያደረገውን ሰውን
እንደ እርሱ የለም የታደለ
ምስጉን ትውልድ ከሞት ያዳነው ሰው
ውኃው ተባርኮለት
ደዌ ችግር ተወግዶለት ሞትን
ተዘልሎ ተቀምጧል
እንደ አንበሳ አርፏል በድፍረት ሕይወት

እርሱማ ያመስግነው
እርሱማ ባለ ዕዳ ነው
እርሱማ ማቁ ተቀዶ
እርሱማ ሊዘምረው

የኢየሱስ ውለታው የበዛባችሁ
ቅኔን ተቀኙለት እልል ብላችሁ
ለክብሩ የሚሆን አምጡ ምሥጋና
እስቲ ጨምሩለት ቅዱስ ነውና

ደግሞ ለጌታ የምን ዝምታ
ደግሞ ለጌታ ከበሮ ይመታ
ደግሞ ለጌታ ሳመልከው ውዬ
ደግሞ ለጌታ ሳመልከው ይነጋ

እርሱማ ያመስግነው
እርሱማ ባለ ዕዳ ነው
እርሱማ ማቁ ተቀዶ
እርሱማ ሊዘምረው

ቻናላችንን ቤተሰብ ይሁኑ
4.3K viewsDegisew, 06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 21:44:25 #ሳይኮሎጂ እንደሚለው አንድን ሰው ተኝቶ እያለ መረበሽ የተኛውን ሰው ላይ ዘላቂ የሆነ የአእምሮ ጉዳት ሊደርስበት ይችላል። ስለዚህ በመንፈሳዊ ሕወይት ደክመው ፤ተኝተው፤በመንፈሳዊ ዓለም የነቁትን የሰዎችን ስም ለማጥፋትና ለማጠላሸት የምትሯሯጡ እባካችሁ ከተኛችበት መንፈሳዊ ዓለም ካነቃን በአዕምሯቹ ላይ ከባድ የአዕምሮ ህመም ከመድረሶ በፍት ተመልሳችሁ ተኙ¡¡...ብቻ ወዴ ዋናዉ ሀሳቤ ስመለስ በመንፈሳዊ አለም የነቁትን ሰዎች ከራሳችሁ ጋር ለማስተኛት አትሞክሩት። በስጋ ከምትወፍሩ ይልቅ በአዕምሮ ብትወፍሩ ይሻላችኃል።
ትልቁ ድህነት የኑሮ ዉድነት ሳይሆን ኢየሱስን ማጣት ነዉ። በሀፍታችሁ አትመኩ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገንዘብ ስናገር እንዴምለዉ ከሆኔ ገንዘብ የጠዋት ጤዛ ነዉ ይላል ይኸ ማለት ጠፊ እንዴሆነ ያስረዳናል።
ቀጪኖቹ እንዴየ ቅጥንነታችሁ ነገሩን አታስቡት ከእናንተ በላይ ከፊ አድጋቹ እንጅ ማሳሰብ ያለባችሁት አለማሰባችሁን ሳይሆን እንዳታስቡ የምያደርገዉን ምንጩን ነዉ። በዓለም ላይ ትልቁ የእዉቀት ጥግ እግዚአብሔርን ማወቅ ነዉ። በምድር ላይ ትልቁ ድህነት የሠማይና የምድር ዳርቻ ፈጣሪ የሆነውን መርሳትና ማጣት ነዉ
4.3K viewsDegisew, 18:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 08:52:06 #የማርያም_መቃብርዋ_ባዶ_ነውን?

መጽሐፍ ቅዱስ ዋና ማዕከሉ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። ብሉይ ኪዳን ውስጥ መሲሑን፣ በአዲስ ኪዳንም ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱሰን የማይጠቅስ ክፍል የለም! ብሉይ ኪዳንን ጸጋ ያትረፈረፈበት፣ አዲስ ኪዳንን ደግሞ የእግዚአብሔር መንግሥት መከፈትና መምጣትን ብሥራት የሠማንበት ምሥራች ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

ቅዱሳት መጻሕፍት በአንድ ቃል የመሲሑ መቃብር ባዶ ነው ይላሉ፤ (ማቴ. 28፥6፤ ማር. 16፥6፤ ሉቃ.24፥5-7፤ ዮሐ. 20፥7-8፤ የሐ.ሥ. 2፥24፡ 31-32፤ 3፥15፤ ሮሜ 1፥4)። የኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን መካከል መነሣት በክብር ማረግ፣ በቀጥታ ከመዳናችንና ከዘላለም ጉዳያችን ጋር የተያያዘ ነው። ከኢየሱስ ትንሣኤና ዕርገት በቀር ከመዳናችን ጋር የሚያያዝ ሌላ ነገር ፈጽሞ የለም። ለዚህ ነው ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ትንሣኤው ሳይዘነጉ ሰፊ ሽፋን ሰጥተው የተናገሩት።

አብዛኞቹ የስህተት መምህራን ይህ እውነት እንዲጐላና እንዲደምቅ አይፈልጉም። ይልቅ ከኢየሱስ እኩል ሌላ "የትንሣኤ" ትርክት ያዘጋጃሉ። በዚህ ረገድ ምሕረተ አብ አሰፋ ተጠቃሽ ነው። ምሕረተ አብ የኢየሱስ አማናዊ ትንሣኤ ግድ ሳይሰጠው፣ የማርያም "ትንሣኤ እና ዕርገት" ግን ያስለቅሰዋል። ተቀበረች በተባለ ቦታው ላይም ሲንከባለል እናየዋለን፤ ነገሩ በረከት ለማግኘት ይመስላል። ሞቶ የተነሣው፤ ታርዶ የቆመው በጉ ኢየሱስ በረከትና ኃይል የእርሱ ብቻ እንደ ኾነ አላስተዋለም።
አዎን፤ ከኢየሱስ በቀር ማርያምን ጨምሮ ኹሉም ትንሣኤን ገና የሚጠባበቅ ነው። የቤተ ክርስቲያን መጻሕፍትም ይህን እውነት በግልጥ ይመሰክራሉ፤

“ስለዚህም ጌታ … በፈቃዱ ሞተ፤ ከተነሣም በኋላ ዳግመኛ አይሞትም፤ ከትንሣኤው በኋላ ግን ጌታ ይህን አልተናገረም፤ ከሰውም ወገን ማንንም ተነሥ፤ ከመቃብር ውጣ አላለም፤ ዳግመኛ እስከሚመጣባት ቀን ድረስ ለሰዎች ኹሉ አንድ ኾነው በሚነሡበት ቀን ሙታን ይነሣሉ አላቸው።”

“ … ከሙታን ተለይቶ እርሱ ብቻ ስለ ተነሣ ነው እንጂ ሥጋውን ብቻ ሕያው አድርጎ ከኹሉ አስቀድሞ በአስነሣ ጊዜ፤ በተዋሐደው ሥጋ በሞተው ሞትም የሞትን ሥልጣን በአጠፋ ጊዜ ለባሕርያችን ወደ ትንሣኤ የሚያደርስ መንገድ እንደ ኾነ ነገሩ የተገለጠ ነው፤ …” (ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ፤ 1988 ዓ.ም፤ ገጽ 209 እና 326)።

ምሕረተአብ ግን ከዚህ በተቃራኒ ግብዝነት በተሞላበት መንገድ፣ የማርያምን መቃብር ልክ እንደ ኢየሱስ ባዶ ነው ሊለን ይዳዳዋል። ከዚያም አልፎ ከኢየሱስ ይልቅ የማርያም ባዶ መቃብር እንደሚደንቀውና እንደሚያስለቅሰውም ሊናገረን ይወዳል፤ ይህ ማርያምን መውደድ የሚመስላቸው ብዙዎች ናቸው። ቅድስት ማርያም የጌታ ኢየሱስ እናት ናት፤ ከዚህ በዘለለ እንደ ኢየሱስ ሞታ በሦስተኛ ቀን ተነሣች ማለት ግን መውደድና ማክበር ሳይኾን፣ ግልጥ መናፍቅነትና የጌታችን ኢየሱስን ትንሣኤ መቃወምና አለማመን፤ ማክፋፋትም ነው። በሰማይና በምድር መካከል መቃብሩ ባዶ ነው የተባለው ኢየሱስ ብቻ ነው! አሜን!

#ኢትዮጵያ #አቤንኤዘርተክሉ #Ethiopia
5.2K viewsDegisew, 05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 08:51:17
3.4K viewsDegisew, 05:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 07:22:20
ድሮ ልጅ ሆኜ አባቴ የሚነግረኝን ተረት
ነው ያስታወሰኝ 5 ወይም 6አመት
አካባቢ እያለሁ ተረት ሲነግረኝ እውነት ይ
መስለኝና እውነት ነው? ብዬ ጠይቅ ነበረ
የአሁን ልጅ እንደውም በ5 አመቱ ኧረ በጣም ነቄ ነው አይሸወድም ተረት ራሱ
አይመቻቸውም አብዛኞቹ ልጆቻችን
መምህር ዘበነ ልክ ተረት እንደሚነገረው
ህጻን ልጅ አድርጎ መጽሀፍ ላይ የሌለ ነገር ሲነግራቸው መልሰው ቤታቸው ገብተው ወይም እዛው ቦታ ላይ እንደማያ
ነቡት እርግጠኛ ስለሆነ በተረታ ተረት ይ
ጫወትባቸዋል !! ያሳዝናል በጣም!!

የአሁን ልጅ ገና በልጅነቱ በጣም የሰላ
አይምሮ ነው ይዞ ሚወለደው እነኚህ ት
ልልቅ ሰዎች ግን ከዛም ያነሱ ሆነዋል እኮ እንደፈለገ የፈለገውን ይተርታል የእነሱ ስራ አሜን እና ጭብጨባ ነው
እሱም ደሞ በጣም ይንቃቸዋል አለማ
ወቃቸውንና ለማወቅ አለመፈለጋቸውን
እንደመልካም አጋጣሚ ይጠቀምበታል
ተረቱን ለማስተማር! ጎልያድ ሙሉ ሰው
ነቱን በብረት ተሸፍኖ በነበረ ሰአት ዳዊት
ግንባሩን ሊመታው የቻለው ሚካኤል የራስ ቁሩን መሸፈኛውን ከፍ አድርጎ ለዳዊት እንዲመች አድርጎለት ነው አለ ጉደኛው ዘበነ!! ይሄ ቃል ያለው 1ኛ ሳሙኤል 17 ሙሉውን ስታዩት እንዲህ የሚል ነገር የለም!! ይሄ ማለት እኮ እግዚአብሄር ያለ ሚካኤል ያለ መላእክት
እርዳታ ጎልያድን መምታት አይችልም እር
ዳታ ከሆነ አካል ያሻዋል ብሎ ጌታን በጣ
ም ከመዳፈር የሚመነጭ አነጋገርን ተናግሯል!!

ሲቀጥል አለምን የሚያሸንፈው ማነው??
ብሎ ጠየቀ ህዝቡ ደሞ እንደቃሉ እምነ
ታችን ብሎ በትክክል ሲመልስ እሱ በድ
ፍረት አለምን የሚያሸንፈው ሚካኤል ነው
በማለት ለራሱ ክብር ዝና ገንዘብ ማግኛ
መንገድን አበጅቷል፡ለሰዎች ለሞኞች
መጥፊያ መንገድን አሰማምሯል በዚህ ንግግሩ


@Giyonitube @Giyonitube
@Giyonitube @Giyonitube
4.0K viewsDegisew, edited  04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-03 18:00:18 አንዲት ሴት በአንድ ወቅት እንዲህ ተብላ ተጠየቀች ፦
አዘውትረሽ ወደ እግዚአብሔር በመፀለይሽ ምን #ትርፍ ታገኛለሽ?
………………………………………………………
እሷም መለሰች ፦
ብዙውን ጊዜ"ምንም አላገኘሁም"ይልቁንም ነገሮችን አጣለሁ"
እናም ወደ እግዚአብሔር በመፀለይ ያጣችውን ሁሉ ጠቀሰች፦
"ኩራቴን" አጣሁ።
"ትዕቢቴን" አጣሁ።
"ስግብግብነቴን" አጣሁ።
"ክፉ ፍላጎቴን" አጣሁ።
"ቁጣዬን" አጣሁ።
"ፍትወትን" አጣሁ።
"የመዋሸት ደስታን" አጣሁ።
"የሀጢአትን ጣዕም" አጣሁ።
"ተስፋ መቁረጥን" አጣሁ።
ሀያላን በፊቱ መገኘት ሁሌም #ማትረፍ ነውና ጥያቄዎቻችሁ ያልተመለሱ ቢመስሏችሁ እንኳን ከእግዚአብሔር ፊት #አትታጡ!!
ስላጣችኋቸው ነገሮች እግዚአብሔርን አመስግኑ!!


sʜᴀʀᴇ  sʜᴀʀᴇ   sʜᴀʀᴇ
4.0K viewsDegisew, 15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 15:57:09
#በእውነት ልብ የሚነካ ታሪክ ነው ምናልባት መርዳት እንኳን ባንችል ወንድማችንን አይዞን እያልን መልዕክቱን በቅንነት ሼር እናድርግለት አደራ!!

#የልጆቼን እናት አጣዋት

#ከወንድማችን አንደበት...

ነፍሰ ጡር የነበረችዋ ባለቤቴ ልትወልድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት በዘውዲቱ ሆስፒታል ክትትል ጀመርን ከዛም ቀናት እየገፉ በመጡ ቁጥር የባለቤቴ ጭንቀቷ ጨመረ

በስተመጨረሻም ባለቤቴ ደሟ ከፍ ብሎ ስለነበር ምጥ እስከሚመጣ አንጠብቅም ስለዚህ በኦፕራሲዮን ነው መውለድ ያለባት ብለው ዶክተሮች ሲያማክሩኝ እኔም በውሳኔያቸው ተስማማውና ባለቤቴን ኦፕራሲዮን አደረጓት

በጣም በሚገርም ሁኔታ ሁለት የሚያማምሩ መንታ ልጆችን በሰላም ተገላገለች እኔም ደስ ብሎኝ ነበር ግን ባለቤቴ ድጋሚ ታመመች የተወለዱት ልጆች ገና 5 ቀን ይቀራቸው ስለነበር ማሞቂያ ክፍል ሲገቡ ባለቤቴን ለከፍተኛ ክትትል ይዘዋት ሄዱ

እኔም ሁኔታውን በጭንቀት ነበር የምከታተለው ፈጣሪ አሳይቶ አይነሳኝም ብዬ በጣም ተስፋ አድርጌ ነበር ግን አልተቻለም ከዶክተሮቹ አቅም በላይ ሆነና ባለቤቴ ልጆቿን በወለደች በአምስተኛ ቀኗ አረፈች

እኔም ልቤ ክፉኛ ተሰበረ እነዚህን መንታ ልጆች ጥላልኝ ባለቤቴ ለእስከወዲያኛው ዳግም ላትመለስ አሸለበች እኔ በአሁን ሰአት ምንም የገቢ ምንጭ የለኝም ኑሮዬ ከእጅ ወደ አፍ ነው እባካችሁ በምትችሉት አቅም ሁሉ አግዙኝ
እያለ ወንድማችን በእንባ ይማፀናል...
#ውድ የሀገሬ ልጆች ከተረዳዳን የማናልፈው መከራ ፣ የማንወጣው ዳገት የለምና አይዞህ ማለትም ትልቅ ነገር ነው መርዳት ካልቻላችሁ እንኳን ሼርር አድርጉለት
#ንግድ ባንክ ፦ 1000096209316...ጌትነት አምፅ አለንቦ
#ስልክ
09 13 73 81 80......( ጌትነት )
#ሰውን ለመርዳት ትክክለኛው ግዜ አሁን ነው !!
5.1K viewsDegisew, edited  12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 16:12:38 ራዕይ ያለው ሰው ሁን
ነገ ዛሬ ለተዘጋጁላት ናትና ዛሬ ላይ አላማ ያለው ሰው ሁን። ነገን አርቀህ ተመልከት።
በራስህ ማስተዋል ላይ አትደገፍ: ነገርህን እሚያበጃጀው እሚፈፅመው እሚያከናውን እግዚአብሄር ስለሆነ እግዚአብሄርን አስቀድመህ መንገድን ጀምር።
ስንፍናን ከህይወትህ አስወግድ። ነገ አረገዋለው ብለህ ዛሬን አትለፈው ማረግ ያለብህን ነገር ሁሉ በሰአቱ አድርገው።
ከፊትህ የሚጠብቅ ብሩህ ቀናቶች እንደሆኑ እንጂ ጨለማ ውድቀት ክስረት እንደሆኑ እያሰብክ በተስፋህ ላይ ፍረሀትን አትዝራ። ተስፋህን ውብ እሚያረገው ኢየሱስ ነውና።
ራዕይ የተቀበልከው ከእግዚአብሄር ነውና አላማ ;ታላቅ የሆነ ተልእኮ እንዳለበት ሰው መኖር ጀመር።
ቅን እና ትሁት መልካም አድራጊ ሁን ።
ራዕይ ካለህ የሚታይህ ኢየሱስ እና ኢየሱስ ብቻ ይሁን።ከተረት አለም ውጣ።
የይቅርታ ልብ ይኑርህ።ወንድምህን ውደድ ክፉ ለሚያርግብህ ፍፁም ፍቅርን ስጠው::
ራዕይ ያለው ሰው ህይወቱን እንዴት መምራት እንዳለበት ያቃል።መኖር ስላለብህ ብቻ አትኑር።እመሠራው ታላቅ አጀንዳ እንዳለበት ሰው ሁን።
ባለ ራዕይ ሰው ለሚያረጋት እያንዳንዷ ነገር ምክንያታዊ ነው።
ራዕይ ያለው ሰው ተቅበዝባዥ አደለም።የተረጋጋ ህይወት ያለው መሠረቱን ያስተካከለ ነው።ስለዚህ መሠረትህ ኢየሱስ ነውና ኢየሱስን በሁለንተናህ ላይ ትከል።
ከሁሉ የሚልቀው ይህ ነው

ራዕይ ያለው ሰው ልቡ ላይ ኢየሱስ ብቻ ሊሳል ይገባልና; በሁለንተናህ ላይ ኢየሱስ ብቻ ይገለጥ ኢየሱስ ደምቆ ይታይ።
ተባረኩልኝ
3.6K viewsDegisew, edited  13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 16:17:57
3.8K viewsDegisew, 13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ