Get Mystery Box with random crypto!

ትን ካሳለፍን በኋላ ተሰናበትናቸው፡፡ ወደ መኪናችን እየተመለስን ‹‹ቁርዓን የት ነው የሚማሩት?›› | ሀላል ትዳር👫💍

ትን ካሳለፍን በኋላ ተሰናበትናቸው፡፡ ወደ መኪናችን እየተመለስን ‹‹ቁርዓን የት ነው የሚማሩት?›› አልኳት፡፡
‹‹አሁን እዚህ ትንሽዬ ቁርኣን ቤት አለች፡፡ የወር ክፍያ እኛ እንከፍልላቸዋለን፡፡››
‹‹ድሮ እኮ ምንም አልነበረም! የእውነት ሁሉም ነገር ደስ ይላል፡፡ ዛሬ ያደረግነው ነገር የልጆቹ ህይወት ውስጥ ምን ያህል ቦታ እንዳለው እንደነሱ ተቸግሬ ስለማውቅ እረዳዋለሁ፡፡ በርቱበት ከጎናችሁ ነኝ!››
‹‹አንድ የደፋር ጥያቄ ልጠይቅህ?›› ተሸኮረመመች፡፡
‹‹እስካሁን አንድም የፈሪ ጥያቄ አልጠየቅሽኝም እኮ!››
‹‹ማህሌትን የምትወዳት ስለውለታዋ ነው ወይስ?››
ገርማኝ ፈገግ አልኩ፡፡
‹‹ታውቂያለሽ ….. ቆንጆ ናት፡፡ ግን ደግሞ ከሷ የበለጡ ቆነጃጅት ይኖራሉ፡፡ ገንዘብ አላት ….. ከሷ የበለጡ ሀብታም የሀብታም ልጆች ይኖራሉ፡፡ በህይወት ዘመኔ ግን የሷን አይነት ስነ-ምግባር ማንም ላይ አልተመለከትኩም፡፡ ፍቅር ምንድነው? ከነብሷ በላይ ምኗን ላፈቅር እችላለሁ? ምንም! እሷ እኮ የህይወቴ ተዓምር ናት፡፡ እሷ በእኔ ህይወት ውስጥ ስትመጣ የስንት ሰው ህይወት ውስጥ ነብስ እንደዘራች ታውቂያለሽ? እህቴን ከነበረችበት የሰቆቃ ህይወት ወደተከበረች እመቤትነት የቀየራት …… አብዱኬን ከወያላነት ወደ አባወራነት ያሻገረው ….. አቤላን ያለሀሳብ በሄደበት በምቾት የሚያስተምረው ….. እኔን የሚሊየን ብር መኪና የሚያስነዳኝ …… ምን ይመስልሻል? የእሷ በህይወቴ ውስጥ መምጣት ነው፡፡ ሀብታም ሆና እልም ያልኩ መናጢ የሙት ልጅ መሆኔ እኔን ከመወዳጀት አላገዳትም፡፡ ብዙ ሀብታሞች ነበሩ በእምነትም የሚመስሉኝ! ዞር ብሎ ያየኝ ግን አልነበረም፡፡ እሷ ግን እኔን ለመደገፍ የሐይማኖታችን መለያየት አላገዳትም፡፡ ብቻ ምን ልበልሽ?  ስለራሴ ያለኝ አመለካከት እንኳን የተሻለ እንዲሆን ያደረገችው እሷ ናት፡፡ ሀፍሷ  …. ሚቾ እኮ ተዓምር ናት፡፡ ከፈጣሪ እንኳን ተስፋ ስቆርጥ …… ጨለማው አይነጋም ብዬ ሳስብ የፈነጠቀችልኝ ብርሀኔ ናት፡፡ የማፈቅረው ከሷ የሚወጣውን እያንዳንዱን ትንፋሽ ሳይቀር ነው፡፡ ነገርኩሽ እኮ ገሀነም እንደምትገባ ባውቅ ከሷ ጋር ገሀነም ለመግባት ዝግጁ ነኝ፡፡ ማፍቀር ማለት በአይኗ ማማር ….. በዳሌዋ ስፋት መማረክ ከመሰለሽ ተሳስተሻል፡፡ ማፍቀር ነብስን ነው፡፡ ሁሉ ነገሯን አፍቅሬዋለሁ፡፡ የሷ ስለሆነ ብቻ ሳላውቀው እንኳን ያለአንዳች ማንገራገር ሐይማኖቷን ተቀብያለሁ፡፡››
‹‹ግን ይኼን ሁሉ ነገር ያደረገችው ሐይማኖትህን ለማስቀየር ቢሆንስ?››
ብሶቴን ቀሰቀሰችው፡፡
‹‹ፍቅረኝነትን እስክንጀምር አንድም ቀን ስለሀይማኖቴ አንስታብኝ አታውቅም፡፡ ተርቤ ስታበላኝ ሀይማኖቴን አልጠየቀችኝም፡፡ የሚያስጠላኝን የሙስሊሞችና የኦርቶዶክሶች ወሬ ልንገርሽ? በዘይት ተታለሉ ምናምን የምትሉት ጉድ ነው፡፡ ስንራብ አብሉን ስንል የላችሁም፡፡ ሰው አብልቶን በጨለማችን ጊዜ ሲደርስልንና በእምነቱ ተማርከንም ይሁን በስነ-ምግባሩ ተስበን ሐይማኖታችንን ስንቀይር በዘይት ተታለሉ ትላላችሁ፡፡ የት ነበራችሁ ስንራብ? የት ነበራችሁ ጨጓራችን ሲነድ? የት ነበራችሁ ስንታሰር? የት ነበራችሁ ስንታመም? የናንተ ጭቅጭቅ ሱሪ ማስረዘም ይቻላል አይቻልም ነው አይደል? ለናንተ እምነት ማለት ዘፈን ሰማች፣ ቀሚሷ ተጣበቀ …. ከወንድ ጋር እንዲህ ሆነች እያሉ ሐጥያት መፈላፈል ነው አይደል? ከፈረ ….. መናፍቅ ምናምን ለማለት የሚቀድማችሁ የለም፡፡ በጣም ደግ ከተባላችሁ ደግሞ ቤተ-እምነታችሁ በር ላይ ለተኮለኮሉ ነዳያን እየተመፃደቃችሁ አንድ አንድ ብር ታድላላችሁ፡፡ ምን ይጠቅማቸዋል? ደግሞ ግዴታ መንገድ ላይ ወድቀን መለመን አለብን ማለት ነው? በኛ ቦታ ቆማችሁ የኛን ህመም አይታችኋል?  አላያችሁም፡፡ በወሬ ሳይሆን በተግባር ያሳየንን እንከተላለን፡፡ ይኼ ደግሞ መብታችን ነው፡፡››
ማልቀስ ጀመረች፡፡ ንዴቴ አልበረደም ቀጠልኩ፡፡
‹‹ሌላው ደግሞ እስኪ አንድ ቀን እንኳን ከቤተ እምነታችሁ ውጪ ላለው ሰው ስለሀይማኖታችሁ ጥሪ አድርጋችኋል? አታደርጉም! የሐይማኖቱም ተከታይ ሐይማኖቱን ለማወቅ ገንዘብ ከሌለው አይችልም፡፡ አሊያም ደግሞ በየሰዓቱ ቤተ-እምነታችሁ እየተመላለሰ ካሪኩለም የሌለው የለብለብ ትምህርት ማዳመጥ ግድ ይለዋል፡፡ ገና የራሳችሁን ኮተት ሳትሞሉ ጴንጤው ወይም ሌላው መንገድ ላይ ወጥቶ የገነት መንገድ ተገልጦልኛል ኑ አብረን እንግባ እያለ የገባውን ሲያስረዳ ትቀጠቅጡታላችሁ፡፡ እናንተ ያላሳያችሁትን መንገድ በጠቆመ? እናንተ ያልሞላችሁትን ክፍተት በሞላ? ምን አይነት ሀይማኖተኝነት ነው ይኼ?  እውነቱን ልንገርሽ አብዛኛው የሀገራችን ህዝብ የአባቴ እምነት እያለ ሐይማኖቱን የያዘ ነው፡፡ ስለሐይማኖቱ ገና ምንም የሚያውቀው ነገር የለም፡፡ እናንተ እስክትነቁ ፕሮቴስታንቱም፣ ሐዋርያቱም፣ ጆቫውም ሁሉም ና አብረን ገነት እንግባ እያለ ይጠራዋል፡፡ ሲርበው ያበላዋል፡፡ ሲቸገር ይደርስለታል፡፡ አባቶቼ ልክ አልነበሩም እያለ ሐይማኖቱን ይቀይራል፡፡ እኔ በግልፅ ነግሬሻለሁ፡፡ ፈጣሪ ጉዳዬ አይደለም፡፡ ማህሌት ነገ ሌላ ሐይማኖት እንከተል ካለችኝ ደስ ያላትን እቀበላለሁ፡፡ ለምን መሰለሽ፡፡ እኔ እሷን ተቀብያለሁ! የኔ ሐይማኖት የሷ ደግነት ነው፡፡››
መራመድ አቅቷት መንገዱ ላይ ተቀምጣ መንሰቅሰቅ ጀመረች፡፡ ፊቷ ቲማቲም መስሏል፡፡ እሷ ላይ እንደዚህ መጮህ እንዳልነበረብኝ ተሰማኝ፡፡ ስትረጋጋ ይቅርታ ጠየቅኳት፡፡
‹‹ይቅርታ ሀፊ …… እናተን እንደዚህ ማለት አልነበረብኝም …. የቻላችሁትን እየሰራችሁ ነው፡፡››
እንባዋን እያበሰች ከተቀመጠችበት ተነሳችና ‹‹ምንም አላጠፋህም፡፡ ያልከው ሁሉ ልክ ነው፡፡ እኛም የቻልነውን እናግዝ ብለን እየተንቀሳቀስን ነው፡፡ እኛን እንኳን ተረድቶ ከጎናችን የሚቆመው ሰው በጣም ትንሽ ነው፡፡ በጣም ይቀረናል፡፡ በጣም!››
ወደ መኪናችን ተመልሰን እንደተቀመጥን ድጋሚ መንሰቅሰቅ ጀመረች፡፡
‹‹ሀፊ ….. Please በቃ ተረጋጊ!››
‹‹ታውቃለህ ነገ ጌታዬ ተርቤ አላበላችሁኝም ….. ስጠማ አላጠጣችሁኝም ….. ስታረዝ አላለበሳችሁኝም የሚልበት ቀን አለ ….››
‹‹ፈጣሪ ደሞ ይበላል? ይጠጣል? ይለብሳል?››
‹‹ያኔ እኛ አሁን አንተ ያልከውን ጥያቄ እንጠይቀዋለን፡፡ መልሱ ምን መሰለህ? ….›› መንሰቅሰቋ በረታ፡፡
‹‹ምንድነው መልሱ?››
‹‹ባርያዎቼ ሲታረዙ አላለበሳችኋቸውም፡፡ እነሱን ብታለብሱ እኔን ታገኙ ነበር፡፡ ሲራቡ አላበላችኋቸውም፡፡ እነሱን ብታበሉ እኔን ታገኙ ነበር፡፡ ሲጠሙ አላጠጣችኋቸውም ብታጠጧቸው በነሱ ውስጥ እኔን ታገኙ ነበር ይላል፡፡ ላንተ ሐይማኖት መቀየር ተጠያቂው ስትቸገር ያልደረስንልህ እኛ ነን፡፡ ያኔ ጌታዬ በተራቡት ሰዎች ጉዳይ ሲጠይቀኝ ምን ብዬ እመልሳለሁ?›› ተንሰቀሰቀች፡፡
‹‹ራስህ ቀጥታ ለምን አልሰጠሀቸውም ትይዋለሽ አትጨነቂ!››
ሁሉም አባላት መጡ፡፡ ፕሬዝዳንቱ የኔ መኪና ውስጥ ከኋላ ተቀመጠ፡፡
ትህትናውን እንደተላበሰ ‹‹ወደድከው?›› አለኝ፡፡
‹‹እሷ አለቃቀሰች እንጂ በጣም ወድጄዋለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ቤተሰብ ነኝ እንደውም!››
‹‹ደስ ይለናል! …. እና ድሮ የምታውቀውን ሰው አላገኘህም?››
‹‹አይቻለሁ ማንንም ማናገር አልፈለግኩም፡፡ ትዝታዬን መቀስቀስ ይሆንብኛል ብዬ ፈራሁ፡፡ ባይሆን ወደፊት ከደፈርኩ እስኪ ….››
መኪናችንን አስነስተን መመለስ ጀመርን፡፡ እየተመለስን ሚቾዬ ደወለች፡፡ በመኪናው ስፒከር ማዋራት ጀመርኩ፡፡
‹‹አብርሽዬ ማር …..››
‹‹ሚቾዬ ቆንጆ …..››
‹‹ውሎ እንዴት ነው?››
‹‹ምርጥ ነበር በጣም! ያልደፈርኩትን ደፈርኩ፡፡››
‹‹ስማ ደግሞ