Get Mystery Box with random crypto!

ከተራራው ላይ ክፍል አስራአምስት የመጨረሻው ክፍል (ፉአድ ሙና) . ‹‹ባጎረስሽኝ ጉርሻ፣ ረሀብ ከ | ሀላል ትዳር👫💍

ከተራራው ላይ
ክፍል አስራአምስት
የመጨረሻው ክፍል
(ፉአድ ሙና)
.
‹‹ባጎረስሽኝ ጉርሻ፣ ረሀብ ከሰመ፣
በደጉ ስብዕናሽ፣ ችጋር ተፈፀመ፡፡
አንቺን አምኛለሁ!››
***
ሚቾዬ እሁድ በጠዋት ቀሰቀሰችኝ፡፡ እኔ በእንቅልፍ አሳብቤ ለመቅረት ሳስብ ነበር፡፡ አልሆነልኝም፡፡ ቱታ ሱሪ በባለኮፍያ ቱታ ጃኬት ለበስኩ፡፡ የሰፈሬ ሰዎች እንዲለዩኝ አልፈለግኩም፡፡ ትንሱዬን ይዘን መሄድ ስለማንችል ሚቾ አትሄድም፡፡ መኪናዬን አስነስቼ ቤተል አደባባይ ስደርስ ሀፍሷ ጋር ደወልኩኝ፡፡ ‹‹ኡሚ›› የሚል ፅሁፍ ያለበት አረንጓዴ ፒፕስ አባያዋ ላይ እንደደረበች እየተፍለቀለቀች መጣች፡፡ 
ፈገግ እንዳልኩ ‹‹መኪና አልያዝሽም እንዴ?›› አልኳት፡፡
‹‹ይዣለሁ ሰጥቻቸው ነው፡፡ እየተጫወትን እንድንሄድ ነው …… ያው የኔ እንግዳ ነህ ብዬ ነው፡፡››
መኪናዬ ውስጥ ከጎኔ ተቀምጣ መንገድ ጀመርን፡፡
ወደኔ ተመቻችታ እየተቀመጠች ‹‹ሚስትህ አልደበራትም አይደል?›› አለችኝ፡፡
‹‹ለምን ይደብራታል?››
‹‹ወደ እስልምና እንድትመለስ ልንሰብክህ መስሏት ምናምን?››
‹‹እና አይደለም እንዴ?›› ሳቅኩኝ፡፡
‹‹አዝግ ነገር ነህ!›› ሳቄ ተጋባባት፡፡
‹‹የምር ግን ሚቾ ልቧ በጣም ንፁህ ነው፡፡ እንደምወዳት ታውቃለች፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ፈጣሪ ጉዳዬ እንዳልሆነም በደንብ ትረዳለች፡፡ ስለዚህ አትሰጋም፡፡››
‹‹ትዳር የማንበጠብጥ ከሆነ መልካም ነው፡፡ የመረዳት ፕሮጀክታችን አካል ነህ! ሐይማኖትህን መቀየርህ ምንም አይነት ኢስላማዊ እውቀት ያልነበረውና ከትክክለኛ ሙስሊሞች ጋር ያልተገጣጠመ ሰው እንደመሆንህ የሚጠበቅ ይመስለኛል፡፡ ሐይማኖትህን በተመለከተ ልንጫንህ አንፈልግም …… አንተ ትልቅ ነህ፡፡ ወደፊት ላንተም ለሚቾም የሚሻለውን ተመራምረህ ትደርስበታለህ ብዬ አስባለሁ፡፡››
‹‹እሺ መልካም እና የመረዳት ፕሮጀክት ማለት ምን ማለት ነው?››
‹‹አንተ በልጅነትህ ስለእስልምና በስርዓቱ ብታውቅ ባሳለፍካቸው የመከራ ጊዜያት ሁሉ ትልቅ ስንቅ ይሆንህ ነበር ብዬ አስባለሁ፡፡ ግን ትምህርቱን አላገኘህም …. እንደነገርከኝ ከባድ ነበር፡፡ ስለዚህ አንተ በጣም ትፈልጋቸው የነበሩ ግን ያጣሀቸውን ነገሮች መረዳት የምናግዛቸውን ቤተሰቦች ለመርዳት በጣም ይጠቅመናል፡፡››
‹‹እናንተ እንኳን ተረድታችሁታል ….››
ትንሽ ዝም ካለች በኋላ ትንሽዬ ማስታወሻ ደብተሯን ገልጣ እያየች ‹‹ኢብሮዬ ባለፈው ከተለያየን በኋላ ብዙ ጥያቄዎች ተፈጥረውብኝ ነበር ….. ልጠይቅህ?››› አለች፡፡
‹‹ይቻላል ….››
‹‹ጓደኛህና እህትህ እንዴት ተጋቡ?››
‹‹በጣም ቅርርብ ነበረን፡፡ ወንድሜ ብዬ ነው የማስበው! ኢንቱ የአዕምሮ ህመም የገጠማት ጊዜ የምትቀርበን እኔን፣ እሱንና ሚቾን ብቻ ነበር፡፡ እሱ ደግሞ ከድሮም በጣም ይወዳታል፡፡ በጣም ያስብላታል …. ይረዳታልም፡፡ እሷም ይኼን ነገሩን በጣም ትወድለታለች፡፡ እኔና ሚቾ ከተጋባንና እሱ የሚቾ አባት ወሳኝ ጉዳይ አስፈፃሚ ከሆነ በኋላ ከአንፎ ለቅቆ ቤተል ቤት ተከራየ፡፡ እናቱ ወዲያው ስለሞተች ከአባቱ ጋር ቤቱ በጣም ሰፋው፡፡ እና የዚያን ጊዜ የልቡ እውነተኛ ፍላጎት ምን እንደሆነ ማሰብ ጀመረ፡፡ በመጨረሻም ኢንቱዬ ገና እያገገመች እያለ ሀሳቡን አካፈለኝ፡፡ መጀመሪያ በጣም ደነገጥኩ፡፡ አንደኛ በእድሜ እኔ እንኳን እሱን በአንድ አመት እበልጠዋለሁ፡፡ኢንቱዬ ደግሞ በጣም ታላቁ ነበረች፡፡ በሰባት አመት ምናምን መሰለኝ የምትበልጠው!  እና እንዴት ይሆናል አልኩት፡፡ አንተ ለወደድካት ልጅ ሐይማኖትህን ቀይረህ እኔ ላይ እንዴት እድሜ እንቅፋት ይሆናል ሲል ሞገተኝ፡፡ ውሳኔውን ለሷ እንድንተወው ግን በደንብ እስከሚሻላት ሀሳቡን ላናቀርብላት ተስማማን፡፡ በደንብ ሲሻላት ነገርናት፡፡ ኢቦዬ ከፈቀደ አልቃወምም አለች፡፡ ያው እሺ ማለቷ ነው እንግዲህ በግሪክኛ! ድሮም እንደሚዋደዱ ስለማውቅ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እህቴን አስረከብኩት፡፡ አሁን ድረስ እንደሁለቱ መጋባት የሚያስደስተኝ ነገር የለም፡፡ አብዱኬ ተዛመደኝ፡፡ ደግሞ ቶሎ ቶሎ ወለዱ፡፡ ሁለት ልጅ አላቸው፡፡ በጣም የምወዳቸው ሁለት ሰዎች ተጣምረው እንደማየት ለእኔ ደስ የሚል ነገር የለም፡፡››
‹‹ይቅርታ ይረብሽህ ከሆነ አላውቅም ግን አሰሪዋን ምንም አላልከውም?›› መረበሽ አለመረበሼን ከፊቴ ላይ ለማንበብ ሞከረች፡፡ ፈገግ አልኩኝ፡፡
‹‹ታውቂያለሽ ዲያሪውን እንዳነበብኩ ሀሳቤ ሙሉ ንብረቱን ለማውደም ነበር፡፡ ውስጤ በጥላቻ ተሞልቶ ነበር፡፡ ከአብዱኬ ጋር ሆነን ስለሰውየው አጣራን፡፡ ባለትዳር ነው፡፡ ልጆችም ነበሩት፡፡ በመሀል ግን ማህሌት አወቀችብን፡፡ መጀመሪያ ተባባሪ መስላ ሁሉንም እንቅስቃሴያችንን አወቀች፡፡ ከዚያ ግን በአጭር ንግግር ረታችን፡፡ ‹‹የሱን ንብረት አውድማችሁ ወይም እሱን ጎድታችሁ ልጆቹ እናንተ የማቀቃችሁበትን አይነት ህይወት እንዲኖሩ ትፈልጋላችሁ ወይ?›› አለችን፡፡  ስናስበው ልክ ነበረች፡፡ እሱ ለኛ መጥፎ ቢሆንም ለልጆቹ ግን አባት ነው፡፡ እናም በጣም እየከበደኝ ይቅርታ አደረግኩለት፡፡ ያኔ ሁሉም ነገር ቀለለኝ፡፡››
‹‹እህትህ ዲያሪ ለምንድን ነበር የምትፅፈው?››
‹‹ያኔ ህመሟን የምታዋየው ሰው ስላልነበረ ይመስለኛል፡፡ ሲቀጥል ደግሞ ያሳለፍነውን ታሪክ ሁሉ ለእኔ ልታሳውቅ ስለምትፈልግም ነው፡፡ እሷ አሁንም ዲያሪዋን እንዳነበብኩ አታውቅም፡፡ ሁሌም ከተመረቅኩ በኋላ እንደምትሰጠኝ ትነግረኛለች፡፡››
አንፎ ባጃጅ ተራው ጋር ስንደርስ መኪናዬን አቆምኩ፡፡
‹‹ምነው?›› አለችኝ፡፡
‹‹ከዚህ በኋላ መንገዱ መኪና ይጎዳል!››
ሳቀች! ከሳቋ ሳታባራ ‹‹አንተ እውነትም ከመጣህ በጣም ቆይተሀል! ተራራው ድረስ እኮ መንገድ ተሰርቷል፡፡›› አለች፡፡
መኪናዬን አስነስቼ በፒስታው መንገድ ላይ በዝግታ እያዘገምኩ ወደ ተራራው መሄድ ጀመርን፡፡ ተራራው ጋር ስንደርስ የልብ ምቴ ፍጥነት ጨመረ፡፡ ከዚህ ተራራ ስር የእናቴን እና የአባቴን ሬሳ በተለያየ ጊዜ አንዲት አሮጌ ፒካፕ መኪና ላይ ጭነናል፡፡ ድርጊቱ ሁሉ አሁን እየሆነ ያለ ያህል ፊቴ ላይ ድቅን አለብኝ፡፡  ማልቀስ ጀመርኩ፡፡ መሪው ላይ ተደፍቼ ተንሰቀሰቅኩ፡፡
‹‹አይዞን ኢብሮ ….. አይዞን!›› ሀፍሷ ልታፅናናኝ ትሞክራለች፡፡ አንብቼ ሲወጣልኝ ይቅርታ ጠየቅኳት፡፡ ሌሎች መኪናዎች ከኋላችን መጥተው ሲቆሙ ከመኪናችን ወረድን፡፡ ፕሬዝዳንቱ ከሀፍሷ መኪና ወርዶ ሀፍሷ የለበሰችው አይነት ፒፕስ ሰጠኝ፡፡ ከኋላ ከነበረችው አሮጌ ታክሲ ላይ ለወር አስቤዛ የተሸመተውን ተሸክመን ወደምንጠይቀው ቤተሰብ ሄድን፡፡ ተራራውን ትንሽ እንደወጣን ህፃናት እየተሯሯጡ እየመጡ ያቅፉን ጀመር፡፡ የምናልፍበት ቤት ሰው ሁሉ ሰላምታ ይሰጠናል፡፡ አንዲት ደከም ያለች ጎጆ ጋ ስንደርስ ህፃናቱ ‹‹ኡሚዎች መጡ …… ኡሚዎች መጡ ….›› እያሉ ወደኛ መሮጥ ጀመሩ፡፡ ሀፍሷና አብረውን የነበሩ ወጣቶች ህፃናቶቹን አቅፈዋቸው ወደ ቤት ገባን፡፡ አንዲት ህመም ከአልጋ ላይ የጣላት እናት በፈገግታ ተቀበለችን፡፡ ቤቱ ውስጥ አረፍ እንዳልን አባላቱ ስለጤናዋ መጠያየቅ ጀመሩ፡፡
‹‹አቡኪዬ ና እስኪ የቀራኸውን አሰማኝ!›› ሀፍሷ ከመካከላቸው አንዱን ህፃን በእጇ እየጎተተች አቀፈችው፡፡
ቀይዋን ትንሽዬ ቁርዓን ከፍቶ በሚገርም ፍጥነት ማንበብ ጀመረ፡፡ ሌሎቹም በተራ በተራ አሰሟቸው፡፡ በግርምት እንደተዋጥኩ ፈገግ ብዬ ተመለከትኳቸው፡፡ ሀፍሷ የቆሸሹ ልብሶቻቸውን ሰብስባ አወጥታ ማጠብ ጀመረች፡፡ ሌሎቹ ምግብ ለማብሰል ከሰል ማያያዝ ጀመሩ፡፡ ምግብ መስራቱ ላይ ተሳተፍኩ፡፡ የህፃናቱን ገላ አጥበንና ቤቱን አፀዳድተን ግማሽ ቀን ያህል እየሰራንና ከልጆቹ ጋር እየተጫወ