Get Mystery Box with random crypto!

በስፒከር ነው መሰለኛ የምታወራው?›› ‹‹አዎ›› ‹‹ሀፍሳ ካንተ ጋር ናት?›› ‹‹አጠገቤ ተቀምጣለ | ሀላል ትዳር👫💍

በስፒከር ነው መሰለኛ የምታወራው?››
‹‹አዎ››
‹‹ሀፍሳ ካንተ ጋር ናት?››
‹‹አጠገቤ ተቀምጣለች፡፡››
‹‹ሀፊዬ ኧረ በእሁዱ ብቻዬን አታስውዪኝ ባሌን መልሺ!››
ሁላችንም ሳቅን፡፡ እየመጣን እንደሆነ ነግሬያት ተሰነባበትን፡፡
ስልኩ እንደተዘጋ ሀፍሳ ፈገግ ለማለት እየሞከረች ‹‹Trust level መቶ ከመቶ›› አለች፡፡
ቤተል ቢሯቸው ጋር ላወርዳቸው ስል ሀፍሷ ትክዝ እያለች ‹‹please ኢብሮ ከቻልክ ታሪክህን ፃፈው!›› አለችኝ፡፡ በጣም ከፍቷታል፡፡ ፈገግ ብዬ መልስ ሳልሰጥ ተሰናበትኳት፡፡ መኪናዬን በቤተል አደባባይ በኩል አዙሬ አርባ ሜትሩን እየዠለጥኩ ወደ ልቤ ንግስት …. ወደ ደግነት ሀውልት ….. ወደ ውዷ ሚስቴ ከነፍኩ፡፡
.
ተፈፀመ!!!
.