Get Mystery Box with random crypto!

ከሞት ሲያመልጡ ሞት የቀደማቸው በዓለማችን አስደናቂ ታሪኮች መካከል ከሞት ሲያመልጡ ሞት የቀደማ | °•°ቢስሚከ ነህያ °•°

ከሞት ሲያመልጡ ሞት የቀደማቸው

በዓለማችን አስደናቂ ታሪኮች መካከል ከሞት ሲያመልጡ ሞት የቀደማቸው ሰዎች አንዱ ነው።

በተለያዩ ጊዜ ከሞት አደጋ ተርፈው ወዲያው በሞት የተቀደሙ ሰዎች አሉ።

ታሪኮቹ እውነተኛ ሲሆኑ 5ቱን መርጬ እነሆ ብያለሁ፦

1. ከአውሮፕላን አደጋ ተርፋ በእርዳታ አምቡላንስ የተገጨችው #ሱዓን

የ16 ዓመቷ ሱዓን ሰንፍራንሲስኮ ኤርፖርት አቅራቢያ ከወደቀችው ኤዥያና 214 አውሮፕላን የተረፈች ብቸኛ ሴት ነበረች። እናም አደጋውን ተከትሎ በርካታ አንቡላንሶች ለእርዳታ ወደቦታው ጎረፉ። ነገርግን ከመሀል አንደኛው ለሱዓን መጨረሻ የተላከ ነበር። ከአደጋው ተርፋ ተደናግጣ በቆመችበት ሄደባት። ታሪኩም ከአደጋው የተረፈ የለም በሚለው ተፃፈ።

2. በቀብር ስነስርዓቷ ላይ የሞተችው #ሙክሃሜትዝያኖቭ

የ49 ዓመቷ ፋጂልዩ ሙክሃሜትዝያኖቭ ሞታ የቀብር ስነስርዓት እየተደረገላት ነበር። በመሀል ፀሎት ሲደረግ ከሳጥኑ ውስጥ ሆና ድምፅ አሰማች። ሰዎችም ተደናገጡና ሲከፍቱት በህይወት አለች። ከዚያም ተነስታ ሁኔታውን ስታይ ሞታለች ተብሎ የቀብር ስነስርዓት እየተፈፀመላት ነበር። ይህ ያልታሰበ ክስተትም የልብ ድካሟን ቀሰቀሰው። በዚህም ምክንያት ዳግመኛ ላትነቃ አሸለበች።

3. ከመኪና አደጋ ሲያመልጥ ባስ የገጨው ካሊፎርኒያዊ
ካሊፎርኒያዊው አሽከርካሪ የራሱን መኪና ይዞ እየተጓዘ ነበር። በመሀል መኪናዋ ከቁጥጥሩ ውጭ ሆነችበትና ወደ ገደል ገባች። በዚህ ጊዜ ባልተጠበቀ ፍጥነት በሩን ከፍቶ አስፖልቱ ላይ ወደቀ። ይሁን እንጅ ከኋላ እየመጣ የነበረው ባስ ሊምረው አልቻለምና ከወደቀበት ተነስቶ ብዙም ሳይረጋጋ የመጨረሻውን ሞት ሞተ።

4. የዜና እረፍቱን ሲሰማ የሞተው #ጋርቬይ_ማርከስ

ጋርቬይ የጥቁር ብሔርተኛ ታጋይ ነበር። እናም አንድ ቀን በውሸት ሞቷል የሚል ዜና ወጥቶ ከመፅሄት ላይ አነበበ። በዚህም እጅግ ከመናደዱ የተነሳ ከዚህ በፊት ሲታከም የነበረው ስትሮክ አገርሽቶበት ህይወቱ አለፈች።

5. ከንብ መንጋ ሲያመልጥ መኪና የገጨው ወታደር የ21 ዓመቱ #ማክ_ጁህ

ከካምፑ መጥቶ ትንሽ አልኮል ከቀማመሰ በኋላ ሲመለስ የንብ መንጋ ያጋጥመዋል። መንጋውን በሚችለው ፍጥነት ካመለጠ በኋላ በመሀል ለፖሊስ ደውሎ ሁኔታውን ያሳውቃል። ከዚያም የተሻለ ቦታ ለመደበቅ አስፓልቱል በሩጫ ሲሻገር በፍጥነት ይጓዝ የነበረ መኪና ገጭቶት በሚሸሸው ሞት ተቀደመ።

አላህ እንዲህ አለ፦


قُلْ إِنَّ الْمَوْتَ الَّذِي تَفِرُّونَ مِنْهُ فَإِنَّهُ مُلَاقِيكُمْ ۖ ثُمَّ تُرَدُّونَ إِلَىٰ عَالِمِ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ فَيُنَبِّئُكُم بِمَا كُنتُمْ تَعْمَلُونَ

«ያ ከእርሱ የምትሸሹት ሞት እርሱ በእርግጥ አግኛችሁ ነው፡፡ ከዚያም ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ወደ ኾነው ጌታ ትመለሳላችሁ፡፡ ትሠሩትም የነበራችሁትን ሁሉ ይነግራችኋል» በላቸው፡፡


ውዶቺ ለአኬራ መልካም ስራን እናስቀድም አደራ !!!!

t.me/HAYAttuna