Get Mystery Box with random crypto!

°•°ቢስሚከ ነህያ °•°

የቴሌግራም ቻናል አርማ hayattuna — °•°ቢስሚከ ነህያ °•°
የቴሌግራም ቻናል አርማ hayattuna — °•°ቢስሚከ ነህያ °•°
የሰርጥ አድራሻ: @hayattuna
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 658
የሰርጥ መግለጫ

🦋አዋቂ ወይም ተማሪ አለያ አድማጭ ሁን
አራተኛን ግን አትሁን ትጠፋለህና

(ነብዩ ሙሐመድ ሰዐወ)
@HAYAttuna
JOIN
አጭርና አስተማሪ ፅሁፎችን
በ @HAYAttuna
ክሮስ ለመስራት ሀሳብ ለመስጥት በ @Muuheee

Ratings & Reviews

1.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-09 12:51:13


تكبيرات العيد .

للشيخ علي أحمد .

اللهــم صــــل وسلــــم
علـــى نبينـــا محمــــدﷺ

25 views°•°Muሄ°•°, 09:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 21:55:42 ማስታዎሻ
=========
ነገ ዕለተ ጁሙዓህ ዙል ሒጃህ 9, 1443 ዓመተ ሂጅራ ነው። ይህ የዙል ሒጃህ ዘጠነኛ ቀን የዐረፋህ ቀን ነው።

①) ይህ ቀን ከአመቱ ቀናት ሁሉ በላጩ ቀን ለመሆኑ በዕውቀት ባለቤቶች ዘንድ ቅንጣትም ውዝግብ የለም።
°
②) በዚህ ቀን የሚሠሩ መልካም ሥራዎች ከሌላው በላጭ ናቸው።
°
③) በዕለቱ ከሚሠሩ መልካም ሥራዎች መካከል አንዱና ዋናው ደግሞ ዱዓእ ነው።
°
④) እርሳቸው ይሁኑ ከርሳቸው በፊት ያሉ ነቢያት በዚህ ቀን ካደረጓቸው ዱዓዎች ሁሉ በላጩ «ላ ኢላሃ ኢለ-ል'ሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁ-ል-ሙልኩ ወለሁ-ል-ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀድር» የሚለው መሆኑን ተናግረዋል – ረሱሉ-ል-ሁዳ ﷺ!
ያልሐፈዛችሁ ሐፍዙት!
°
⑤) ይህን ቀን ሐጅ ላይ ካሉ ሰዎች ውጭ ሌላው በጾም ማሳለፉ የሁለት አመታትን (ከኋላውና ከፊቱ ያሉ አመታትን) ወንጀል ያስምራል ብለዋል ውዱ ነቢይ ﷺ።
°
⑥) በዚህ ቀን በተለይም ከዐስር እስከ መጝሪብ ባለችው ወቅት የሚደረግ ዱዓእ እጅግ በጣም ተቀባይነት አለው።
°
⑦) በተጨማሪም ይህ ቀን የዋለው ነገ ጁሙዓህ እንደመሆኑ መጠን፤ በሌላ ሐዲሥ እንደተዘገበው በዕለተ ጁሙዓህ ከዐስር እስከ መጝሪብ ባለው ወቅት የሚደረግ ዱዓእ ተቀባይነት አለው። Imagine ሁለቱ ተቀባይነት ያለባቸው ወቅቶች አንድ ላይ ሲገጣጠሙ → ተቀባይነት² በሉት።
°
⑧) አላህ ይወፍቀንና፤ ሰሑር ላይ ቢነጋብን እንኳ ጹመን ለመዋል ለአንድት ቀን ብንነይት፣ ይህቺን ከዐስር እስከ መጝሪብ ያለች ወቅትም በኸይር ነገር ብናሳልፋት መልካም ነው። መቼም ሁላችንም ይብዛ/ይነስ እንጂ ከወንጀል የጠራን አይደለንምና እንዲህ አይነት ጌታችን እኛን ለመማር ብሎ ያመቻቸልንን የወንጀል ማበሻ ሰበቦችን በአግባቡ እንጠቀምባቸው።
°
⑨) ተክቢራ ማለት የሚጀመረው ከነገ ጠዋት የፈጅር ሶላት ጀምሮ እስከ ዙል ሒጃህ 13ኛ ቀን ዐስር ድረስ ነው።

አላህ እኔንም እናንተንም ለሚወደው ንግግርና ተግባር ይወፍቀን። ወደ መልካም ያመላከተ የሠሪውን ያክል ምንዳ ያገኛልና ቤተሰቦቻችሁን፣ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ለማስታወስ ሞክሩ።


||
t.me/MuradTadesse
102 views•°• ስሜ ግን ማን ይሆን•°•, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 09:45:53
131 views•°• ስሜ ግን ማን ይሆን•°•, 06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-03 21:38:24 የተከፋችሁበትን ነገር ሁሉ ለአላህ ንገሩ። ከርሱ ዉጭ ጉዳታችንን የሚጠግን ማን አለ?

@HAYAttuna

JOIN
205 views•°• ስሜ ግን ማን ይሆን•°•, 18:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-02 10:56:24 አላህን በማውሳትና ተክቢራ በማድረግ እንበርታ
الله اكبر
الله اكبر
الله اكبر
لا إلاه إلى الله
الله اكبر
الله اكبر
ولله الحمد

@HAYAttuna

JOIN
333 views•°• ስሜ ግን ማን ይሆን•°•, 07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 13:41:29 * አሥሩ የዚልሒጃ ቀናት፣ ሁለተኛው ቀን።
* የመጀመርያው ጁምዓ።
* ክብርም፣ ሞገስም፣ ድባብም ያላቸው ዉድ ቀናት።
* አላህ ዋጋቸዉን አውቀው ከሚጠቀሙባቸው ያድርገን።

* መልካም አላህን የማውሳት - የተክቢራ፣ የተህሊል፣ የተሕሚድ ቀን ይሁንልን።
* የእርቅ፣ የመተሳሰብ፣ የመግባባት፣ የስክነት፣ የእርጋታ፣ የምህረት ቀን ይሁንልን።
* የበጎ ነገሮች ሁሉ፣ የመልካም ሥራ እና የመልካም ንግግር ቀን ይሁንልን።

ጁምዓ ሙባረክ !

t.me/HAYAttuna
237 views•°• ስሜ ግን ማን ይሆን•°•, edited  10:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 21:34:37 ኡድሂያ ለማረድ ካቀዱ ከወዲሁ ጥፍርና ጸጉርዎን ከመቁረጥ ይቆጠቡ!
-------------------
አንድ ሙስሊም ሀጅ የማያደርግ ከሆነና በዒድ አል አድሀ እለት ኡድሂያን ለማረድ ካሰበ የዙልሂጃ ወር ከገባበት የምጀመሪያዉ ቀን ጀምሮ ጥፍሩንና ጸጉሩን አይቆርጥም፤ ቆዳውንም አይቀርፍም። ይህም ተከታዩን የኡሙሰለማ ሀዲስ መሰረት ያደረገ ነው።

ከኡሙ ሰለማ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «የዙልሂጃ ወርን ጨረቃ ካያችሁና ከናንተ መካከል አንዱ ኡድሂያ ለማረድን ካቀደ፤ ፀጉሩንና ጥፍሩን ከመቁረጥ ይቆጠብ» አል ኢማም አህመድ ዘግበውታል። በሌላም ዘገባም «ኡድሂያውን እስኪያርድ ድረስ ከፀጉሩና ከጥፍሩ ምንንም አይቁረጥ» ብለዋል። እንደዚሁ፤ «ከሰውነቱ ቆዳ ወይም ከፀጉሩ ምንንም አይቁረጥ» ብለዋል።

ይህ ማንኛውም ሙስሊም እራሱን በሀጅ ላይ ካሉ ሰዎች ጋር የሚያመሳስልበት እና የተወሰኑ የኢህራም ክልከላዎችን ከነሱ ጋር የሚጋራበት ዲናዊ ስርአትና ነብያዊ ትዕዛዝ ነው።

☞ጸጉርንና ጥፍርን ከመቁረጥ የሚከለከለው ለራሱ ወይም ለሰው በራሱ ገንዘብ የሚያርድ ሰው ብቻ ነው። ህጉ የሚመለከተው የሚያርደዉን ሰው ብቻ ነው ሲባል፤ በወኪልነት ለሌላ ስው የሚያርድን ሰው አይጨምርም።

እያወቀ ጥፍሩን ወይም ጸጉሩን የቆረጠ ወንጀል ፈጽሟልና ወደ አላህ በተውበት ሊመለስ ይገባዋል፤ ኡድሂያው ግን አይበላሽም ማካካሻ ከፋራም የለበትም። አንዳንዶች እንደሚያስቡት ሳይሆን ወንጀሉን ቢፈፅምም ኡድሂያ ማረዱን መተው የለበትም።

በስህተት ወይም በመርሳት ፀጉሩን ወይም ጥፍሩን የቆረጠ ሰው ምንም ወንጀል የለበትም። በተመሳሳይ መልኩ በጣም አስፈላጊ ሲሆን ቢቆርጥ ችግር የለውም። ለምሳሌ የተጎዳን የሰውነት ቆዳ ለማከም ወይም የተሰበረ ጥፍሩን ለማስተካከል መቁረጥ ይፈቀድለታል።

፠ ስለ ኡድሂያ ጥቂት ተጨማሪ ነጥቦች

1 - በዙልሂጃ አስር ቀናት ከተወደዱ ተግባሮች መካከል ኡድሂያን በማረድ ወደ አላህ መቃረብ አንዱ ነው።

2- ኡድሂያ በጣም ከጠነከሩ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ሱናዎች መካከል ነው። ኡድሂያ የነብዩ ኢብራሂምን ሱና ህያው ከማድረግ በተጨማሪ ለድሆች እና ችግረኞች መድረስ ነው።

3- ኡድሂያን በተመለከተ አላህ ከኛ የሚፈልገው ለእርሱ ያለንን ፍራቻ ተቅዋና ታዛዥነት ግልጽ ማድረጋችንን ብቻ ነው። አላህ እንዲህ ብሏል፤

‎{ﻟَﻦ ﻳَﻨَﺎﻝَ اﻟﻠَّﻪَ ﻟُﺤُﻮﻣُﻬَﺎ ﻭَﻻَ ﺩِﻣَﺎﺅُﻫَﺎ ﻭَﻟَٰﻜِﻦ ﻳَﻨَﺎﻟُﻪُ اﻟﺘَّﻘْﻮَﻯٰ ﻣِﻨﻜُﻢْ ۚ ﻛَﺬَٰﻟِﻚَ ﺳَﺨَّﺮَﻫَﺎ ﻟَﻜُﻢْ ﻟِﺘُﻜَﺒِّﺮُﻭا اﻟﻠَّﻪَ ﻋَﻠَﻰٰ ﻣَﺎ ﻫَﺪَاﻛُﻢْ ۗ ﻭَﺑَﺸِّﺮِ اﻟْﻤُﺤْﺴِﻨِﻴﻦَ} الحج 37

አላህን ሥጋዎቿም ደሞቿም ፈጽሞ አይደርሰውም፡፡ ግን ከእናንተ የሆነው ፍራቻ ይደርሰዋል፡፡ እንደዚሁ አላህን በመራችሁ ላይ ልታከብሩት ለእናንተ ገራት፡፡ በጎ ሠሪዎችንም አብስር፡፡» አል ሐጅ 37

4- ኡድሂያ የሚታረደው ከዒድ ሰላት በኋላ ነው። የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم ከኢድ ሰላት በፊት ያረደ ሰው እንዲደግም አዘዋል።

5- ሚዛን በሚደፋው የኡለማዎች አቋም መሰረት የዒድ ሰላት ከተጠናቀቀበት ጊዜ ጀምሮ የሶስተኛው ቀን ጸሀይ እስክትጠልቅ ድረስ ኡድሂያን ማረድ ይቻላል።

6- ወንድም ይሁን ሴት ግመል፣ የቀንድ ከብቶች፣ በግና ፍየል ለኡድሂያ ይታረዱሉ።

7- የአላህ መልዕክተኛ صلى الله عليه وسلم እንከን ያለባቸውን እንስሳት እንዳናርድ ከልክለዋል። አንድ አይኑ የታወረ፣ ስብራት ያለበት፣ የከሳና የደከመ ወይም የታመመ እንስሳ ለኡድሂያ አይሆንም።

8- ኡድሂያን ለብቻ ማረድ እንደሚቻለው ሁሉ ለሰባት ሆኖ አንድን ወይፈን ወይም በሬ መጋራትም ይቻላል።

9- አንድ ሰው ኡድሂያ ሲያርድ ለራሱ እና በህይወት ላሉም ይሁን በህይወት ለሌሉ ቤተሰቦቹ አስቦ ሊያርድ ይችላል።

10- የኡድሂያውን ስጋ፣ ለቤት፣ ለስጦታ እና ለሰደቃ አድርጎ ሶስት ቦታ መከፋፈሉ ሱና ነው። ይህ ማለት ግን እንደ አስፈላጊነቱ ለሶስቱም ያውለዋል ማለት እንጂ ሶስት እኩል ቦታዎች ይከፋፍለዋል ማለት አይደለም።

አቡጁነይድ ሳላህ አህመድ

t.me/HAYAttuna
221 views•°• ስሜ ግን ማን ይሆን•°•, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-30 18:18:24 ሲጠየቁ አልሐምዱ ሊላህ ደህና ነን የሚሉ፣ ግን በዉስጣቸው የደከሙ ባሮችህን ሁሉ እርዳቸው ያ ረብ።

@HAYAttuna

JOIN
180 views°•°Muሄ°•°, 15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 21:31:24
በሐላሉ የተጣመሩ መደበኛ ባለትዳሮች እንዲህ ኮራ ብለው ደረታቸውን ነፍተው እንደ ልባቸው ይንቀሳቀሳሉ።

ኢ-መደበኛ ኃይሎች ማለቴ ባለትዳሮች ግን እንዲህ ጥግ ለጥግ፣ ጢሻ ለጢሻ ተሸማቀውና ደፍጠው እንደተሳቀቁ ይኖራሉ።


አላህ ህዝባችንን ከሐራሙ በሐላሉ ያብቃቃልን።
259 views•°• ስሜ ግን ማን ይሆን•°•, 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 20:17:02 ....እርግጥ ነው ብዙ ተከታይ ሊኖርህ ይችላል ።
አድናቂህም በርካታ ሊሆን ይችላል። 
ግና ተከታይህ ሁሉ አድናቂህ አይደለምና ይህን ማወቅ ይኖርብሃል።
 ስህተትህን ለማጋለጥ፣ ዉድቀትህን ለማሳየት፣ ምን እንዳልክ ለማየት፣ አለማወቅህን ለማስረዳት፣
~ በ ሲ ፈርስት የሚከታተልህ አለ፣
~  በሴቭ ዶክመንት የሚያቆይልህ አለ፣
~ በስክሪን ሹት የሚጠባበቅህ አለ፣
 ~ በተለያዩ ወጥመዶች ሊይዝህ የተዘጋጀ አለ፣

ዛሬ ላይ ብዙ ተከታይ ለማግኘት ካሰብክ ለየት ያለ ሀሳብ ፃፍ፣ ወጣ ያለ አቋም ያዝ።
ያኔ ማን ይሆን እሱ! እያለ ሁሉም ካለበት ቦታ እየሮጠ ይመጣልሃል። በአሥር ሺ የሚቆጠር ተከታይ ያላቸው ግና መቶ ተቀባይና አዳማጭ የሌላቸው ብዙ ናቸው።

ወዲህ ግን ቁምነገር የሚጽፉ ተከታያቸው ግን ጥቂት ብቻ የሆነ ጠንካራ ሠራተኞች አሉ።

ሰው ስለራሱ ነውርና እንከን የተወበት፣ የረሳበት ዘመን ላይ ነው ያለነው። ከዕውቀት ይልቅ መረጃን ያስበለጠበት ዘመን ላይ እንገኛለን።

አንዳንዱን ሰው ሲከታተልህ እንደነበረ የምታውቀው በኮሜንቱና በስድቡ ነው።


ቁምነገሩ የሰው ክትትል አይደለም፤ ከፈጠረህ አምላክ አንፃር ትክክል ከሆንክ የፍጡራን ክትትል አያሳስብህ።

t.me/HAYAttuna
280 views•°• ስሜ ግን ማን ይሆን•°•, 17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ