Get Mystery Box with random crypto!

hanny❤tube

የቴሌግራም ቻናል አርማ hannytube — hanny❤tube H
የቴሌግራም ቻናል አርማ hannytube — hanny❤tube
የሰርጥ አድራሻ: @hannytube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 861
የሰርጥ መግለጫ

"ያ አላህ ለሰጠኸኝ ፀጋ ሁሉ አመሰግንሀለው
በፍጥረታትህ ስፍር ቁጥር ልክ ምስጋና ይገባህ"
ለማንኛውም ጥያቄ ወይም አስተያየት
@hilarious28

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 15:34:12 ሐዲሶች
===========

1) «ለእያንዳንዱ ነብይ ተቀባይነት ያላት ዱዓ አለችው "የእኔን ዱዓ የቂያማ ቀን ለዑመቶቼ ሸፋዓ ትሆነኝ ዘንድ ለዛ ቀን አቆይቻታለሁ»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ሶሒሁ ሙስሊም

2) «መልካም የዋለላችሁን ሰው እናንተም ለርሱ መልካም በመዋል ካሱት፣ የምትክሱበት ካላገኛችሁ ዱዓ አድርጉለት»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ኢማሙል ቡኻሪ (አል-አደቡል ሙፍረድ) ላይ ዘግበውታል

3) «አላህ ዘንድ ከስሞች ሁሉ ተወዳጅ "አብደላህ እና አብደራህማን" ናቸው»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)

ሶሒሁ ሙስሊም
@hanny tube
83 views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-01 15:34:10 መህሬ "ተውሒድ" ነው ያለችዋ ድንቅ እንስት
≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡≡

ሳቢት ኢብኑ አነስ እንዲህ አሉ፡-
አቡ ጦልሓ የተባለ ሰው ኡሙ ሱለይምን የትዳር ጥያቄ ያቀርብላታል ፡

ከዚያ ኡሙ ሱለይም እንዲህ ብላ መለሰችለት ፡

☞ " አንተ አቡ ጦልሓ ሆይ ! (ወላሂ) በአላህ ስም ይሁንብኝ የአንተ አይነት ሰው ለትዳር ጠይቆ እምቢ የምትባልና የምትመለስ ሰው አልነበርክም " ነገር ግን አንተ ካፊር/ካሃዲ ነህ ፡ እኔ ደግሞ ሙስሊም ሴት ነኝ ፡ እኔ አንተን ማግባት አልተፈቀደልኝም ፡ ከሰለምክ እሱ ነው መህሬ ከዚያ ውጭ ምንም አይነትን መህር አልፈልግም ፡
ከዚያም አቡ ጦልሓ ሰለመና ተጋቡ መህሯም ይሄው ሆነ ። አላህ አክበር

በሌላም
የኡሙ ሱለይም(ረዲየላሁ ዐንሃ) መህሯ ምን ነበር?!
አነስ _ረዲየላሁ ዐንሁ _ እንዲህ ይላሉ፦
"አቡ ጠልሓ ኡሙ ሱለይም(ረዲየላሁ ዐንሃ) ለማግባት የጋብቻ ጥያቄ አቀረቡ።
ኡሙ ሱለይም፦ "አንተ የምትገዛው ጣኦት እነ እገሌ… የሚባሉ ጎሳዎች መንደር ሐበሻዊ ሰው ከእንጨት እንጠረበው አታውቅምን?"ስትል ጥያቄ አቀረበችለት።
አቡጠልሓም፦"አዎን።ጠንቅቄ አውቃለሁ።"ሲል ምላሹን ሰጣት ።
ኡሙ ሱለይም፦"ታዲያ ሐበሺያዊው ሰው ከእንጨት የጠረበውን ጣኦት ስታመልክ ትንሽ እንኳ እፍረት አይሰማህምን?!!"አለችው።
በመቀጠልም፦
"እስልምናን ከተቀበልክ ከሱ ውጭ ሌላ ሰዳቅ ፣ጥሎሽ የምጠይቅህ ነገር አይኖርም።"
አቡጠልሐ፦"እስኪ የማስተውለበትና ከራሴ ጋር የምነጋገርበት ጥቂት ቀናትን ስጪኝ።"ብሏት
ወደ ቤቱ አቀና ብዙም ሳይቆይ ወደርሷ ተመለሰና፦
"አሽሀዱ አን ላ ኢላሀ ኢለ ሏህ፣ወአሽሀዱ አነ ሙሐመደን ረሱሉላህ"በማለት እስልምናን መቀበሉን ከፊትለፊቷ አበሰራት።
ከዚያም፦

ኡሙ ሱለይም፦"አንተ አነስ ሆይ! ወልይ(ሐላፊ)ሆነህ ከአቡ ጠልሐ ኒካሁን ተቀበል።"አለችኝ።"
ሣቢት (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦
"በእስልምና ታሪክ ውስጥ እንደ ኡሙ ሱለይም የላቀ እና ውድ መህር የተሰጣት ሴት ሰምተን አናውቅም፣ምክንያቱም የርሷ መህር አቡ ጠልሐ ኢስላምን መቀበሉ ነበርና።"
【ሲፈቱ ሰፍዋ"(2/247)】
79 views12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:28:53 #አፍላ ፍቅር

ፀሃፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

Part ❷0

በዚህ መሃል የሃናን አባት በተራቸው ሊሰግዱ ነው መሰለኝ ሲመጡ ተገጣጠምን፡ የሃናን አባት ምግብ በአፋቸው ለረዥም ሰአታት ያህል እንዳልዞረ እንኩቶ ሆኖ በነጭ ቀለም ዙሪያው የተለውሰው ከንፈራቸው ይናገር ይዟል። ለዚህ ሁሉ ነገር በህግም ቢሆን ተጠያቂዎቹ እነ አምሪ ናቸው ባይነኝ።
የሰውልጅ ኑሮን እራሱ የሰው ልጅ ለምን ለማናገት ይቸኩላል፡ ማገናዘብ የሚባለው ነገር የት ደረሰ።

እነ አምሪ ይኼኔ ሲስቁና ሲጫወቱ ከቤተሰብ ጋር አድረዋል፡ ያቺ ምስኪን ግን...። ምናልባት ዛሬ ትምህርት ቤት ከገቡ የሃናን ስልክ አለመስራቱና ከክፍሉ ውስጥ አለመገኘቷ ከነሱ መሰወሯ ወደ ቤቷ ሊያስኬዳቸው ይችላል ብዬ እገምታለሁ ፡

ከጎረቤት ወይም ከአካባቢው ነዋሪዎች ውስጥ የተፈጠረውን የሰማ ካለ ስለሃናን መጥፋት ሹክ ይላቸው ይሆናል፡
ያው በመደናገጥ ችግሩ የተፈጠረው በእነሱ ምክንያት መሆኑን በወቅቱ ሊዘነጉት ይችላሉ ባይ ነኝ፡ ግና በነሱ ምክንያት መሆኑን ቆይተውም ቢሆን የተገነዘቡ ጊዜ በሰሩት ድርጊት አፍረው ከመፀፀት መንደር የሚገቡ ይመስለኛል

ከዚያ ውጭ ነገሮች መንገድ ቢቀይሱ ማለትም ፡አላህ ይጠብቃትና ሃናንን ከዚህ በኋላ ከዱኒያው አለም ላይ ካጣናት በሞት ከተነጠኩ ሙሉ ለሙሉ፡ የሃናን ገዳይ እነሱ እንደሆኑ ለሚመለከተው አካል ሁሉ መናገሬ አይቀርም፡፡

እኔምለው ግን ይህችን ሁለት ቀን እዚህ ሆስፒታል ስገባ የሃናንን እናት አልተመለከትኩም። መቼም መሰገጃ አቀባይዋና እንድሰግድ አዛዧ ለሃኑ ታላቅ እህቷ ትሆናለች እንጂ መቼም....።

ምናልባት ግን እናቷ ድንጋጤ የማይችሉ ሁነው ሳይነገራቸውም ቀርቶ ቢሆንስ እስካሁን ያላየኋቸው ፡እረ ወደሃናን መገኛስ መች አቀናሁና እዛ ተቀምጠው ቢሆንስ ውስጥ መግባት ባይቻልም እውጭ ላይ።

እንደጠረጠርኩት የሃናንን አባት ለሶላት ነበር ሲጓዙ የተገጣጠምነው።
ለልጅቷ ከማል ስልክ አላነሳ አለኝ በቃ ሰግጄ መጣሁ ሲሉ ከእኔ ጋር ሰላምታ ተለዋውጠው ወደ መስገጃው ቦታ አብረውኝ ተጓዙ፡ ከሃናን ውጭ አንዳች ነገር ሃሳብ ሆናባቸዋለች።

ኡዱ አድርጌ የሃናን አባት ከጎኔ ሌላ አንድ ሰው ኢማም ሁኖ ከፊት በመቆም ከሌሎች ሰዎች ጋር ጀመአ በመፍጠር ዙሁርን ሰገደን፡

ከሰላት በኋላ ከጎኔ ስለተቀመጡት የሃናን አባት አስብ ጀመር፡
ትንሽ ልብሳቸው በላቸው ላይ ወደ ማደፋ እየቃጣው እንዳለ አስተዋልኩ፡ እንዴት ሁኖ የሃናን እንደዛ መዘነጥ እኮ ኑሯቸውን በኮተታ ኮተት ከሚያሸበርቁት መካከለኛ ወይንም ሃብታም ከሚባሉ ሰዎች ወይንም ቤተሰብ ውስጥ የወጣች ነበር የሚያስመስለው፡ እኔ እንደዛ ነው እስካሁን በክፍል ውስጥ በምታደርገው እንቅስቃሴ የማስባት። ለነገሩ የሰውልጅ ቀርበው ሳያዩት በግምት ባዩት መለፍለፉ አግባብነት የለውም።

ከሰላቱ በኋላ ሃናን ወዳለችበት አቅጣጫ ከአባቷ ጋር አቀናን እንደደረስን በቦታው መስገጃ የሰጠችኝ ልጅ ስለነበረች መስገጃውን መልሼላት በቦታው ካለ ወንበር ላይ ተቀመጥኩ፡ ወደ ውስጥ መግባት አይቻልም ሌላ ታማሚ ያለባቸው ሴት ወንድ ወጣቶች በየቦታው ተቀምጠዋል በየመሬቱ ካርቶን አንጥፈው ተኝተዋል። እዚህ ስትመጣ አፊያ ምን ያህል ውድ ስጦታ እንደሆነ ትገነዘባለህ። አሁንም የሃናን እናት ግን ከዚህ ቦታ የሉም።

የሃናን አባት ከእኔ ጋር ከመጡ ጀምሮ ወዲያ ወዲህ በመንጎራደድ ስልክ በመደጋገም ይደውላሉ ግን ሲያወሩ አይደመጥም፡ ምናልባት ቅድም ለልጅቷ ያሏት አካል አሁንም ስልኩን ሊያነሳ ፍቃደኛ አልሆነላቸውም መሰለኝ።

በዚህ መሃል ልጅቷ ከጎኔ መታ ተቀመጠች፡ የሃናን አባት ወደ ውጭ ስለወጡ ወሬዋን ከእኔ ጋር አድርጋች።

ጥቂት በሃናን ጉዳይና በሆስፒታሉ ዙሪያ ካወራን በኋላ፡ በመሃል

አንቺ እህቷ ነሽ? ስል ጠነኳት።
አዎ ታላቅ እህቷ ነኝ አንመሳሰለም?
ለማንኛውም አሚና አባላለሁ ስትል ስሟን አስከተለች።
እኔ የክፍል ጓደኛዋ ነኝ አቡበክር እባላለሁ።
እ አወኩህ አንድ ቡድናችሁ?። እንዴት አወቀችኝ በሚል እየተወዛገብኩ
አዎ ምነው?
አይ እቤት አንዳንዴ በጫወታ መሃል ሃናን ስምህን ታነሳ ነበር።
ሰው ማማት ሃራም አይደል እንዴ። አልኩ ውስጤ እየሳቀ።
እሷም ምላሽ ስለሌላት ፈገግ አለች በዝምታ።
እኔም ዝምታዋን ተንተርሼ በሃሳብ ተጓዝኩ ሃኑ ትወደኛለች ማለት ነው? ስል እራሴን ጠየኩ።

በዚህ መሃል የሃናን አባት ከሄዱበት ተመልሰው መጡ። ወደ እኛ እንደተጠጉ

አሚ ሲሉ ንግግራቸውን ለልጃቸው አሰሙ።
ወዬ አባ።
ከማል አልፈቅድልህም አለኝ ባክሽ። እንደከፋቸው ፊታቸው ያስታውቃል።
እና?።
ማንም ሳይነካቸው የሃናን አባት በጩኸት ያባረኝ በቃ ለልጄማ አላንስም ሲሉ ሆድ ብሷቸው እንባቸው በፂማቸው በኩል እየተንሸራተተ ከጃኬታቸው ላይ ይንጠባጠብ ጀመረ። ጩኸታቸው በጣም አስደንግጦኛል፡
ምን እንደተፈጠረ አላውቅም ግን ሆዴን ባር ባር ይለው ጀመር፡ ከማል የተባለው ሰው ግን ለሃናን አባት አሰሪያቸው ይመስለኛል ምክንያቱም አከራያቸው ቢሆን ያባረን እንጂ ያባረኝ አይሉም ስለዚህ ነገሩ የስራ ጉዳይ ይመስለኛል።

አሚና የአባቷን ፊት ፊት እያየች ጠንከር ብላ ንግግሯን ቀጠለች፡
በቃ አባ አንተ ሳተኛ ነው ያደርከው
እና አሁን እዚህ ተኛ የዛሬውን ለብቻዬም ቢሆን እኔ አድራለሁ አንተ እረፍት አድርግና ምሳ በልተኽ ስራህ ግባ።
ብላ ከመቀመጫዋ ተነስታ አባቷን ለማጠንከር በሚመስል መልኩ አቀፈች።

አንዳንዴም ሃብታም ቀልብ የለውም የሚባለው የእውነት ነው እንዴ አስባለኝ፡ መቼም ልጅ ታሞባቸው መሆኑን ሳይነግሩት አይቀርም እንዴት ሰው ሰው መሆን አቃተው ያውም ከማል የተባለው አሰሪያቸው እኮ ሙስሊም ነው፡ ብቻ የዚህች አለም አንዳንድ ሰውነን ባዮች ያስገርማሉ ከሰውነት ጥግ እየወጡ ሰው ነን።

ከአሚና ጋር ስንጫወት ቆይተን ማምሻውን ወደ እቤት ሄድኩ፡ ዛሬ ሄኒ እቤት ይገባል ብዬ እገምታለሁ ነገር ግን ተነግሮኝ ባለመጠየቄ አፍሬያለሁ።

ወደ እቤት እንደገባሁ እናቴን ከተቀመጠችበት የጠዋቱን ጉዳይ በሚያስረሳ መልኩ ግጥም አድርጌ ጉንጮቿን በመሳም አለፍ ብዬ ወደ ክፍሌ ልገባ ስል፡

የጠዋቱን ነገር እየጠበኩ ነበር አለችኝ?
ስጋቷን ስለተረዳሁ ፈገግ በማለት አይ እማዬ አላነበብኩትም።
የእውነትህን ነው፡ አቡ እኔ አሁን እውነቱን ልነግርህ ዝግጁ ነኝ አንተን ማጣት አልፈልግም፡ አንብበከውም ከሆነ እውነቱን ንገረኝና ስለተፈጠረው ነገር ሳልደብቅህ ልንገርህ። አለችኝ ነገሩ በጣም እንዳስጨነቃት ከንግግሯና ከአኳኋኗ ስለተረዳሁ ወደ ኋላ በመመለስ ከጎን ተቀመጥኩና፡

እማዬ የእውነቴን ነው አልዋሸሁም ከአንድ ወረቀት ውጭ አላነበብኩም እስኪ ምንድነው ነገሩ ከወረቀቱ ይልቅ ስለ እህቴ ሶፊ ካንቺ አንደበት የተፈጠረውን ልስማ፡

እማዬ ጥቂት መሬት መሬቱን ከተመለከተች በኋላ ጉሮሮዋን በመጠራረግ ስለ እህቴ ሶፊ መናገር ጀመረች

ወቅቱ የአዲስ አበባን ነዋሪን በተለይ ወጣት ተማሪን በዚና(የሀራም ግንኙነት) መአበል....

ክፍል ❷➊ ይቀጥላል

ሶፊ ማናትስ የትናትስ?????
https://t.me/hannyTube
130 views19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 22:28:43 #አፍላ ፍቅር

ፀሃፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

Part ➊❾

በዚህ መሃል የሃናን አባት ቁጥር በስልኬ እስክሪን ላይ ብቅ አለ፡ የትኛውን ማስቀደም እንዳለብኝ አላቅም፡ ደብዳቤውን ወይንስ ስልኩን። ጣቶቼ እኔ ያዝኳቸው አልመስል እስኪለኝ ድረስ ተንደርድረው በመሄድ የስልኩን ጥሪ አቋረጡት።
ምን እያደረክ ነው አቡ ያቺ የምትሳሳላት ሃናን እንዴት እንደሆነች ለመስማት እንዴት ሊያቅትህ ቻለ፡ እያለ ህሊናዬ ይወቅሰኝ ጀምሯል።

ሃሳቤን ወደ አንድ ቦታ ለመሰብሰብ እየሞከርኩ አይኖቼን ከደብዳቤው ላይ ሙሉ ለሙሉ ተከልኩ፡

ደብድዳቤው ከአንድ ወገን ለሌላ አንድ ወገን የተፃፈ ነው፡ እንጂ ስላለፈ የህይወት ታሪክ ወይንም በአንድ ቀን ውሎ ውስጥ ስለተከወነ የራስ ታሪክ የተጫረ ዲያሪ አይደለም። ምክንያት ቀንና ቦታ እንዲሁም የግለሰብ ስምን ያውም አቆላምጦ ሳይቀር ለመግለፅ ይቃጣዋል። በሃሳብ ወደ ሃናን ለመሻገር እየሞከርኩም ቢኾን ዝም ብዬ እላይ እላዩን ገረፍ ገረፍ በማድረግ መመለከቱን ቀጠልኩ፡

አሁን በዚህ ደብዳቤ ላይ ትልቁን ቦታ የምትይዘው ሊዱ የምትባል አንድ ወገን ነች፡ ይመስለኛል ይሄ ወረቀት ምላሽ ለመስጠት ወይንም ለሆነ አጠራጣሪ ነገር እንደ ጥያቄም እንደመልስም እንዲሆን ተደርጎ ነው የተዘጋጀው፡ ሊዱ የተሰኘችው ግለረብ ስሟ በተደጋጋሚ ከወረቀቱ ላይ በመስመሮች ልዩንት በየመሃሉ እኔን እስኪያሰለቸኝ ድረስ ተሞንጭሯል፡

ይሄ ደብዳቤ ካየሁት ጊዜ አንስቶ በጥርጣሬ መንፈስ የሶፊ ይሆን እንዴ ስል በውስጤ ሳስበው የነበረው ወረቀት ቢሆንም፡ አሁን ግን መቶ በመቶ ትክክለኛ ነቱ የተረጋገጠለት የሶፊ የሚስጥር ፅሁፍ ሁኖ አጊንቸዋለሁ።

ምክንያቱ ደግሞ አሁን የጀመርኩት ፅሁፍ ካለቀ በኋላ በቀጣይ የሚገኘው ወረቀት ከሌላኛው ወገን የሶፊ ስምን በተለየ የእጅ ፅሁፍ አቆላምጦ አሰፍሮ ብቅ ብሏል አሁን ለነገሩ አትኩሮት ሰጥቼዋለሁ።

በዚህ መሃል በድጋሚ የሃናን አባት ይደውሉ ጀመር።
ስልኩን አንስቼ ወደጆሮዬ አስጠጋሁና
ቀዝቀዝ ባለ ድምፅ
ሄለው ሰላም አለይክ።
ወአልይኩምሰላም። የሚል የሴት ድምፅ ወደ ጆሮዬ ገባ፡ የትላንትናዋ ከሃናን አባት ጋር የነበረችው ልጅ ትመስለኛለች።

ይቅርታ ደውለህ ነበር መሰለኝ?።
ስትል ንግግሯን ከሰላምታው ምላሽ ጋር አስከተለች፡ ትህትናዋ ደስ ይላል።
አዎ የሃናን አባት ስልክ አይደለም እንዴ?
ነው ነው ማን ልበል።
አንቺ ትላንትና ሆስፒታል አብረሻቸው የነበርሽው ልጅ ነሽ?
አዎ።
እሺ አቡኪ እባላለሁ ትላንት ከአንድ አባት ጋር አብሬያችሁ የነበርኩት ልጅ፡ ትዝ ካላልኩሽ ማታ በሃናን ስልክ የደወልኩልሽ። ስል የማስታወስ አቅሟን ለማጠንከር ሞከርኩ።
እ.. እ.. እሺ አው አወኩህ
ሰላም ነው።
አልሃምዱሊላህ
እ ማታ ያልሽኝ እንዴት ሆነ ሆስፒታል ቀየራችሁ። ሃናንስ እንዴት ናት?

አይ አልቀየርንም በወቅቱ በእረፍት ላይ የነበሩ ትልልቅ ዶክተሮች ሌሊቱን ወደ ሆስፒታል በቀና ትብብር ሊገቡ ችለዋል፡ ሃናን ግን
ግን ምን። ስል ከተቀመጥኩበት አልጋ ዘልዬ ተነሳሁ።
እክካሁን እራሷን አታውቅም ልትነቃ አልቻለችም።
ብላ ወደ ማልቀሱ ተንደረደች።
አይዞኝ አላህ ከኛ ጋር ነው አብሽር፡
በቃ እዛው ከሆናችሁ መጣለሁ እሽ።
እሺ።
ሰላም አለይክ። ስል በኢስላማዊ ሰላምታ ስልኩን ዘጋሁት።

ከአልጋው ላይ ተመለሼ ከመቀመጥ ይልቅ በቆምኩበት፡ ኦው ሃናን በጣም ያሳዝናል ስለ ለብቻዬ አወራ ጀመር።

በአይኔ ላይ ክፍል ውስጥ የምትሆነው ነገር የእኔ በስስት መመልከት ከሄኒ ጋር ስትሆን ትንሽ ቅናት ቢጤ የምከናነበው ነገር ሳቋ ሁሉ ነገሯ በአይኔ ላይ ብልጭ አለብኝ፡ በተለይ አንድ ጊዜ ብቻ ምሳ አብረን የበላንበት አጋጣሚማ ሊያስለቅስኝም ፈለገ።

ሃናንን አሁኑኑ ማየት አለብኝ ስል የሶፊ የሚስጥር ቁልፍ የሆኑትን ደብዳቤዎች እደርስበታለሁ በሚል ከምኝታ ቤቱ ውስጥ አውጥቼ ከእኔ ክፍል አስቀምጬ ሰአቱ ቢሄድም ቁርሴን ከበላሁ በኋላ ከቤት ለመውጣት መሰናዳት ጀመርኩ ግን ከዛ በፊት ለእኛ ደግ አባት መደወል እንዳለብኝ አሰብኩ።
ስልካቸውን በሃናን ስልክ ስለነበር የመዘገብኩት ቁጥሩን ለማውጣት የሃናንን ስልክ ከአልጋዬ ጎን ላይ ካለችው ኮመዲኖ አንስቼ ሳበራው ቻርጅ ጨርሶ ስልኩ ዝም ጭጭ ብሏል፡ ለሷ ስልክ የሚሆን ተመሳሳይ ኬብል እኛ ጋር ስለሌለ መደወሉን ትቼው ከቤት ወጣሁ

ትራንስፖርት በመከራ አጊንቼ ቢሆንም ሃናንን ወዳለችበት ሆስፒታል ደረስኩ፡ እንደደረስኩ ቅድም በስልክ ያወራኋትን ልጅ ከጊቢው ውስጥ ዝሁር ሰግዳ የሰገደችበትን ምንጣፍ ይዛ ወደመጣችበት ስትመለስ አገኘኋት፡ ሰአቱ መሄዱን አሁን ገና ልብ አልኩ።

ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ዝሁር ሰግደሃል? ስትል ከሰላምታ በኋላ ቀደም ብላ ጠየቀችኝ።
አይ ከቤት ከዛ በፊት ስልወጣሁ አልሰገድኩም።
እሺ በቃ የኡዱ ውሃ ከሜዳው ጀርባ አለ። ሰግደህ ና ግን የትላንትናው ቦታ አይደለም ሃናን ከትላንትናው ከፍል ተቀይራለች እዛም ቢሆን ግን ቤተሰብ መግባት አይችልም አለችኝ መስገጃውን ከእጇ እየተቀበልኩ።
በዚህ መሃል የሃናን አባት በተራቸው ሊሰግዱ ነው መሰለኝ ሲመጡ ተገጣጠምን፡ የሃናን አባት ምግብ በአፋቸው ለረዥም ሰአታት ያህል እንዳልገባ እንኩቶ ሆኖ በነጭ ቀለም ዙሪያው የተለውሰው ከንፈራቸው ያሳብቃል። ለዚህ ሁሉ ነገር በህግም ቢሆን ተጠያቂዎቹ....


ክፍል ❷0 ይቀጥላል

ሶፊ ማናትስ የትናትስ?????
122 views19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:35:27 #አፍላ ፍቅር

ፀሃፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

Part ➊➑

ከእማዬ ጋር አይን ለአይን ተፋጠጥን
በአግራሞትና በግርታ እየተመለከተኝ፡ ምን እየሰራህ ነው? ስትል አፈጠጠችብኝ እንደፈገግታዋ ሁሉ ቁጣዋም ውስጥን ሰርሳሪ ነው። ደንግጫለሁ።
በድጋሚ፡ ምን እየሰራህ ነው? በሚል ጥያቄ አንባረቀችብኝ። እማዬ ናት አይደለችም ጥርጣሬ ይገጥመኝ ጀመር እንደዛሬ አይነት ቁጣ አይቼ አላውቅምና።

ምን አለህ ከዚህ እቃ ጋር ምንድን ነው ያለኽ? ስትል ከእጄ ላይ ልትመነትፍ ቀኝ እጇን ዘረጋች።

የማውቃት እማዬ ሌላ ሰው ሆናብኛለች የምትይዝ የምትጨብጠውን አታለች።
ግን ለምን አዎ ግን ለምን ይሄ በፔስታል የተቀመጠ እቃን ከተመለከትኩ ቀንና ጊዚ ጀምሮ ከዚያ በፊትም እንደሰሞኑ ባይሆንም ስለ ሶፊ ጥያቄ ባነሳሁ ቁጥር ቁጣዎች እኛ ቤት ላይ ለምን ያንጃብባሉ ከ ሶፊ ጀርባ ምን አለ።

እማዬ የሰነዘረችው የቀኝ እጅ በፌስታል የነበረውን ደብዳቤ ለመንጠቅ ቢሆንም።

ወደ ኋላዬ በመሸሸግ።
አልሰጥም! የሚል አስደንጋጭ መልስ ከእኔ አሰንዝሮባታል።
እንዴ ነችና፡ እማዬ ስትንቀጠቀጥ ይታየኛል።
አይኖቼ እንባን አቅረዋል ልቤ በፍራቻ ድክ ድክ ትልብኛለች
በጉልበት ምንም ማድረግ እንደማትችል ስላወቀች በቃላት ውርጅብኝ ቤቱን ማናጋት ቀጥላለች፡ በቃ ጎረመስክ ጎረመስክ።
በተቻለኝ መጠን እነ ሄኒ ቤተሰብ ጋር ያሰፈነችውን የዲፕሎማሲ አረማመድ ላስታውሳት እየሞከርኩ ነው፡

ወዲያው ጩኸቷን ቀነሰች በዝምታ ልታደምጠኝ ጆሮዎቿን ወደ እኔ ሰደደች፡

እማዬ ተረጂኝ አማርኛ ነው የማወራው መግባባት እንችላለን፡ ሰው ምንም እንዲል አልፈልግም፡ ከ ሶፊ ጀርባ ምን ድን ነው ያለው? ይሄ ነው ጥያቄዬ ወደዚህ ተግባር ያስገባኝም ይህ ነው፡
እኔ ቀጣይ አምት የዩኒቨርስቲ ተማሪ ነኝ እኔ ትንሽ ልጅ አይደለሁም ጥያቄዎቼን እንድትመልሺልኝ እፈልጋለሁ። ሆድ ብሶኝ እንባዎቼን ማንጠባጠብ ጀመርኩ።

እማዬ የዲፕሎማሲ ሰው ነች አምናለሁ የአፍሪካ ሃገራት መሪዎችም በድፍረት ከሷ ቢማሩ እላለሁ፡ በመንሹራ እማይፈታ ነገር እንደሌለ ጠንቅቃ ታውቃለች፡

ጥቂት ዝም ብላ ብሶት የወለዱት የሚመስሉ እንባዎችን ዱብ ዱብ አደረገች። ተሸነፈች አሸነፍኳት ወይስ እኔ ተሸነፍኩ። ልቤ ተሰበረ፡ አንዳች ነገር እንባዋ ሳይደርቅ ተጠምጠምባት ተጠምጠምባት እያለ ይገፋፋኛል፡ ግን ጉዳዩ አንገብጋቢ ስለሆነ ውስጤን አጠንክሬው ከፊቷ በድፍረት ቆሚያለሁ፡ የጥያቄዬን መልስ ለመስማት፡ ግን እናት ስታለቅስ ማየት ምንኛ ያማል፡ አላህ እስከመጨረሻው ስትስቅ እንጂ እናት ስታዝን አያሳየን በተለይ በእኛ በልጆች።

ከለቅሶዋ መሃል የደበዘዘ ድምፅ ብቅ አለ፡
አንተም ጥለኸኝ ልትሄድ እንደዛ አሳድጌህ?
እንደ ሶፊ ልትከዳኝ።
ማልቀሷን አላቆመችም ስሜታዊ ሆና ንግግሯን ቀጠለች፡
እውነቱን ልንገርህ አዎ በቃ አይደለህም?
ምን አይደለህም? መልሱን ልሰማ በቆምኩበት እቋምጥ ጀመር፡

ልጄ አይደለህም አይደላችሁምም፡
በሂወቴ ገጥሞኝ የማያውቅ ድንጋጤ በንግግሯ አርበተበተኝ።
እማዬ እንዳለፈው እኔ እንዳጋጠመኝ አቅሏ ላይ ችግር ገጠማት እንዴ ምንድን ነው የምትዘባርቀው ከመጠን በላይ ፈራሁ፡ ከዚህ በላይ በዝምታ ከፊቷ መቆም አልችልም፡ የያስኩትን የደብዳቤ ጥርቅም ከመሬቱ ላይ ዘርግፌ እቅፌ ውስጥ አስገባኋት፡ ሁለታችንም እቤቱን በለቅሶ በጠበጥነው። የእኔን የተለያዩ ሚስጥሮች ደብቃ እኔ የሷን አንድ ነገርማ መደበቅ አያቅተኝም የቅርቡ ትውስታ እንኳ በሄኒ ምክንያት ህይወቴ መስተጓጎል እንዳይገጥመኝ እላይ እታች ብላ የታደገችው ብቻ ከውለታዎቿ ውስጥ በቂ ነው። አትዘን ሶፊያም ትቅር በዚህ ሰአት ሃናንም ብትሆን ትቀራለች ሃናንንም ሶፊንም ለማግኘቴ ቁልፍ ናትና።

ተቃቅፈን ለተወሰኑ ደቂቃዎች ተለቃቀስን።
የቻልኩትን አድርጌ እማዬ እንደተረጋጋች
ከአልጋው ላይ አብረን ተቀምጠን አፉታዋን ሳይረፍድ አሁኑኑ እፈልጋለሁኝና በይቅርታ አንገቷን አንቄ እጨቃጨቃት ጀመር ድሮም በእናት ሆድ ቂም የለምና አፋታዋን አሰምታኝ ፈገግ አለች።
"አቤት ማማር" ከጌታዬ ቁጣም ተቆጠብኩ ከእርግማኖቿ ሸሽቼ ዱአወቿን ዳግም ከጃይ የምሆንበትን መንገድ በፍጥነት ሁሉንም በመተው አመቻቸሁ፡ "ድሮም አራዳ አይደለሁ"

ምንም ጊዜው እሩቅ የሚባል ቢሆንም አንዴ ከአንድ የትምህርት ቤት ወዳጄ ጋር ስለእናት በጨዋታ መሃል ስናወጋ እንደተረት አድርጎ እቺን ሹክ ያለኝን አሁን ድረስ አልረሳትም፡

"አንድ ባልና ሚስት ከአንድ ቤት ውስጥ ተጋብተው ይኖራሉ የባልየውም እናት ከእነሱ ጋር ነው ምትኖረው ያውም አይነበስር ሁና ግን ሚስትየው ከጊዜያት በኋላ እናትህን ከዚህ ቤት አስወጣት በማለት ባሏን ትጨቃጨቅ ጀመረች፡ ከጊዜ ወደጊዜም ነገሩን ታጠነክረው ጀመር፡ በስተመጨረሻም ባል ትዳሩ እንዳይፈርስ በመስጋት የሚስቱን ሃሳብ ተጋርቶ በአንድ እለት ከሚስቱ ጋር ተማክሮ ወደ ትልቅ ገደል እናቱን ጥሎ ሊመጣ አዝሎ ከቤት ይወጣል፡ እናትም ልጃቸው ከሚስቱ ሲማከር ነገሩን ሰምተው ነበርና ልጃቸው ገደል ውስጥ ሊጥላቸው አቀበትና ቁልቁለት ጫካ ለጫካ በማቋረጥ ሲጓዝ እሳቸው በጀርባው እንዳሉ ልጃቸው የመጣበት መንገድ ሲመለስ እንዳይጠፋው ቅጠል እየበጠሱ ወደ መሬት ይጥሉ ነበር"

ያለኝ ላይረሳ በአይምሮዬ ተቀርፆ እስከዛሬ በልቤ ታትሞ የእናትን ውለታ እንዳልዘነጋ አሻራ ሁኖኛል።
አይ እናት ብቻ በሰብካት ቁጥር አንጀት መብላት ብቻ ነው ነገሩ።

እማዬ ደክሞት ይሆናል በሚልና ይበልጥ እራሷን ለማረጋጋት ይጠቅማታል በሚል ከኪችኑ የሚጠጣ ንፁህ ውሃ በብርጭቆ ቀድቼ ሰጠኋት።

ግን አሁንም ይቅርታዋ የእውነት ሊመስለኝ አልቻለም፡ ውሃውን ጠጥታ ሳትጨርስ በድጋሚ አቅፌያት ጠረኗን መማግ ተያያስኩ።

ከእቅፏ አውጥታኝ ቅድም እዚሁ ከጎናችን ያሉ ጎረቤቶቻችን ጋር እንደነበረች ነግራኝ ።

ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ ሻወሩ በመግባት ተጣጥብ ልብሷን ከቀየረች በኋላ በድጋሚ ወደእኔ በመምጣት ተክዤ በተቀመጥኩበት አልጋ ላይ እንዳለሁ፡

ከዚህ በኋላ ምትሄድም ከሆነ ሂድ ካለህ ግን ጥያቄ ካለህ ጥያቄዎችህን እመልስልሃለሁ ክፋ ነሽ እንደማትለኝ አምናለሁ እራስህም ትፈርዳለህ፡ አሁን ማታ እንዳልኩህ ከትምህርት ቤትህ ደርሼ መጣው፡ ስትል በንግግሯ ግራ እንዳልጋባ በሚመስል መልኩ የሶፊ ይሆናል ብዬ የገመትኩትን ደብዳቤ በእግሯ ወደ እኔ ገፋ አድርጋ የመኝታ ቤቱን በር ዘግታው ወጣች

ነገሩ ምንም ሊገባኝ አልቻለም ነገር ግን መሬት ላይ የወደቀውን ደብዳቤ በአትኩሮት ተመልክቼ አነሳሁትና ከአልጋው ላይ ቁጭ ብዬ ከውስጡ አንድ ዘለላ ወረቀት አወጣሁ፡


በዚህ መሃል የሃናን አባት ቁጥር በስልኬ እስክሪን ላይ ብቅ አለ............

ክፍል ➊❾ ይቀጥላል

ሶፊ ማናትስ የትናትስ?????
153 views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 13:35:17 ልጅት… እማ በጠዋቱ ወዴት ነው ?
እናት … አብሲት ልጥል ነው ልጄ
ልጅት … ምነው አትፈልጊውም እንዴ ?
እናት ... በጥፊ ቸምቧ ወየው
126 views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 23:38:57 #አፍላ ፍቅር

ፀሃፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

Part ➊❼

የዛሬዋን ቀን ደስ ከሚያሰኙት ነገራቶች ውስጥ የሄኒ ከሆስፒታል መውጣት አንዱ ነው። ነገር ግን ስለ ቀን ሲነሳ ብዙዎቻችን ቀናችንን እራሳችን ማሳመርም ማበላሸትም የምንችል እኛው እራሳችን እንደሆንን አንዳንዴ ሲዘነጉ አስተውላለሁ ከኔ ጭምር
አይ ዛሬስ ይሄ ቀፉፊ ቀን ይሄ ሚደብር ውሎ ደስ የሚል ቀን ብቻ ብዙ ነገር በቀን ተንተርሰን እንላለን፡ እንደእኔ አሁን ላይ ለኔ ቀን ቀን ነው ሚደብር ማይደበር የሚባለውን ነገር አልቀበለም እራሴ ነኝ ቀኔን ማሳመርም ማበላሸትም የምችለው ብዬ አምናሉሁ። የዛሬ ደስታ ግን የኔ ብቻ ሳይሆን የሃኑም የሌሎችም በሄኒ ምክንያት ለተጨነቁ ሰዎች ሁሉ ዛሬ ደስታቸው ነው።

የደወልኩትን ስልክ የሃናን አባት አያነሱም እኔም በተደጋጋሚ መደወሌን ቀጥልኩ፡ ምናልባት ሃናን ላይ ችግር ገጥሟቸው ይሆን። ስል አሳብ ውስጥ ገባሁ አላህ ኸይሩን እንዲያሰማኝ ውስጤ ይማፀን ጀምሯሪ።
አሊያም ደግሞ ስልኬን ስለማያውቁት ይሆን ማያነሱት፡ ስል እራሴን ለማጠንከር እሞክራለሁ፡

በስልክ ስለ ሃናን ሁኔታ ለማጣራት በተደጋጋሚ ያደረኩት ሙከራ ሊሳካልኝ አልቻለም። አለማንሳታቸው ከልክ በላይ ያስጨንቁኝ ጀምሯል።

ከኔ ክፍል በመውጣት ወደ ሳሎኑ አቀናሁ በሩ ዝግ ነው ጀንበሯ በመስኮቱ በኩል ብቅ ብላ ከመጋረጃው ላይ በማረፍ ለእቤቱ ደስ የሚያሰኝ ቀለም አላብሳዋለች፡
የኪችኑ በር ክፍት ስለነበር ምንም በሃናን ጉዳይ በጭንቅ ላይ ብሆንም የራብ ስሜት እየተሰማኝ ስለሆነ የተዘጋጀ ቁርስ ካለ ለመመገብ በመሻት ወደ ውስጥ ገባሁ፡
ፊት ለፊት ተከድኖ የተቀመጠውን ሰሃን እንደከፈትኩት እማዬ የምታዘጋጀው እጅ አስቆራጣሚ ምግብ ተዘጋጅቶ በሽታው አወደኝ። ትኩስ መሆኑ ብዙም አላስደነቀኝም ምክንያቱም እማዬ ማታ እንዳለችው በዚህ ጠዋት ወደ ትምህርት ቤት ሄዳለች ማለት ነው። ለዛም ነው በጠዋት ትኩስ ቁርስ ያገኘሁት፡

ግን እማዬ ምን አስባ ነው በዚህ በለሊት የሄደችው። በልጅነት በጠዋት ትምህርት ቤት ስንሄድ አርፍደው የሚመጡ የሰፈር ጓደኞቻችን ሰፈር ውስጥ ሲያገኙን "ጥበቃውን ቅስቀሳ ነው እንዴ የምትሄደው" ይሉ ነበር። አይ እማዬ ስል ፈገግ አልኩ።

በዚህ መሃል ወዳላሰብኩት ጥልቅ አልም በትምህርት ዙሪያ በመመሰጥ እምዘገዘግ ጀመር። የልጅነት ጊዜው ማስገረሙ፡ ዛሬ አፍቃሪ ለመሆን መበቃት፡ በእነዚህ ሁሉ አስከፊና አስደሳች የእድሜ ቆይታዎች ውክጥ ያገጠሙኝ ነገራቶች በማስታወስ ስማስን ሶፊ ብልጭ አለችብኝ።
"አሃ" ስል ከሄድኩበት አለም ተመለስኩ። እማዬ የለችም ስለዚህ ከአልጋው ስር ወዳስቀመጥኩት እቃ መድረሻው ሰአት አሁን ነው፡ ግን እንዴት እማዬ መኝታ ቤቱን ዘግታው ቢሆንስ የወጣችው፡

በፍጥነት ለማረጋገጥ ወደ መኝታ ቤቱ አመራሁ እንደደረስኩ የበሩን መክፈቻ ተጫንኩ "ፂጥ" የምትል ድምፅ በሯ አሰማች በፍጥነት ወደ ውስጥ ዘልቄ ከግርግዳው ላይ የተለጠፈችውን የመብራት ማብሪያና ማጥፊያ ተጫንኩ፡ ምንም ብርሃን ላገኝ አልቻልኩም፡ መብራት ጠፍቷል። በፍጥነት የስልኬን መብራት አብርቼ ከጉልበቴ በርከክ ስል ወደ አልጋው ስር እመለከት ጀመር

ፌስታሉ እንደተቀመጠ ስለሆነ ያለው ወደሳሎኑ በመመለስ ከቤቱ ውስጥ ያለውን የቁም መጥረጊያ ማሰስ ጀመርኩ፡ ካለሁበት ቦታ ላይ የለም ወደ ኪችኑ በፍጥነት አመራሁ ከእንጀራ ምጣዱ ጎን ቆሞ ተመለከትኩት አንስቼው ስጣደፍ ከክፍሉ ስወጣ ገርበብ ያለው የኪችኑ በር የእግሮቼን ጣቶች ገጫቸው በጣም ስላመመኝ አጎንብሼ ጣቶቼን ተመልክቼ አጠፍ ዘርገት ካደረኳቸው በኋላ ወደ መኝታ ቤቱ ገባሁ፡

የስልኬን ፍላሽ እንዳበራሁ ወደ አልጋው ስር የቁም መጥረጊያውን ሰደድኩና ከፌስታሉ ላይ አሳረፍኩ ፌስታሉ ወደ ውስጥ ስለራቀ ለማውጣት አልመች አለኝ በሁለቱ አቅጣጫዎች አልጋው ከግድግዳ ጋር የተጋጠመ ስለሆነ ቦታ ቀይሮ ስራውን ለመከወን አይሆንም ረዘም ላለ ደቂቃ በማታገል ስላቆየኝ ስሜታዊ በሆነ መንፈስ ታጅቤ በትግልና በጉልበት ስቤ ወደ ጫፍ አደረስኩት።
እጄ የሚደርስበት ቦታጋ እንዳደረስኩት መጥረጊያውን ወደ ጎን በመወርወር የሶፊ ደብዳቤ ይሆናል ብዬ የገመትኩትን ዶክሜንት በድጋሚ በጣቶቼ ውስጥ አስገባሁት ከተንበረከኩበት ቀና ብዬ ከፌስታሉ ውስጥ በማውጣት በእጄ ይዤው ወደ እኔ ክፍል ለመሄድ ስል የመኝታ ቤቱ በር ተከፈተ፡

ከእማዬ ጋር አይን ለአይን ተፋጠጥን.....

ክፍል ➊➑ ይቀጥላል

ሶፊ ማናትስ የትናትስ?????
https://t.me/hannyTube
121 views20:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:38:03 ድንቅ ስብዕና

አነስ ኢብን ማሊክ ለአመታት በነብዮ ቤት ውስጥ አገልጋይ ነበረ። ለእሳቸውም በጣም ቅርብ በመሆኑ ከማንም በላይ ባህሪያቸውን ያውቃል ። በረመዳን ወር ነው ።ነብዮ ሙሀመድ በፆም መፍቻቸዉ ሰዐት ቤት አልተገኙም ። ምሽቱ እየዘለቀ ቢሆንም አሁንም ብቅ አላሉም ።አነስ ኢብን ማሊክም የአንዳንድ ተከታዮቻቸውን ጥያቄ ተቀብለው ከእነሱ ጋር ፆም ፈትተው ይሆናል ብሎ በማሰብ ለእሳቸው አዘጋጅቶ የነበረውን ምግብ ሁሉ ተመገበ። እሳቸው ግን ብዙም ሳይቆዩ ወደ ቤት ተመለሱ።አነስም ከእሳቸዉ ባልደረቦች አንዱን "የአላህ መልዕክተኛ ፆማቸውን የት ነው የፈቱት" ሲል ጠየቀ።
የተጠየቀዉ ሰሀባም "እሳቸዉ ገና ፆማቸዉን አልፈቱም አንድ ጉዳይ አጋጥሞአቸዉ ነበር የዘገዩት " ሲል መለሰ።አነስ በጣም አፈረ።ምግቡን ለማዘጋጀት የሚቻለዉ አልነበረም ከጠየቁትም ይቅርታ ሊጠይቃቸዉ አሰበ።
እሳቸዉ ግን የሆነውን አዉቀውት ስለነበር ምንም ሳይሉ እየራባቸዉ ተኙ።
ምንኛ የተባረከ ስብዕና
152 views09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:20:50 #አፍላ ፍቅር

ፀሃፊ ካሊድ ታረቀኝ (ye umi)

Part ➊➏

ወደውስጥ እንደገባሁ በቀጥታ ከሰዎች ጋር ግንኙነት ወደ ምትፈጥርበት ቦታ(in box) አመራሁ ቆየት ብላለች ማለት ነው ስል የመጀመሪያ ላይ የተቀመጠውን የሄኖክን መልእክት ለራሴ ምላሽ በመስጠት አየሁ። ወደ ውስጥ እንድገባ ነብሲያዬ ትፈታተነኝ ጀመር፡ እረ ነውር ነው እልና የስልኩን እስክሪን አጠፋለሁ። ከራሴ ጋር የጀመርኩት ጦርነት(ሰጣ) ገባ በስተመጨረሻ በአንድ አቅጣጫ ላይ ፀና

ስልኩን ከፍቼ ወደ ውስጥ ገባሁ
በዚህ መሃል የክፍሌ በር ይንኳኳ ጀመር ከእማዬ ውጭ ማንም ስለማይሆን ምን ፈልጋ ይሆን በሚል ከአልጋው ያለምንም ንግግር በመውረድ ወደ በሩ አመራሁ፡

በሩን እንደከፈትኩት ወዷ እናቴ ወደ ውስጥ ለመግባት እንደማትፈልግ ለመግለፅ በሚመስል መልኩ ፊቷን ወደመጣችበት አቅጣጫ አዙራ ቆማ ነበር የተመለከትኳት፡

ወዬ እማ ስል በሃናን ምክንያት ከፊቴ የጠፋውን ፈገግታ በማምጣት ወብ ገፅታዋን እመለከት ጀመር።
እኔ እምልህ የቅድሙን በስልክ የነገርኩህን ነገር ልድገምልህ ብዬ ነው የመጣሁት።
ጓደኛህ ነገ ከሰአት አካባቢ ከሆስፒታል ይወጣል ቤት እንደገባህ ሄደ ጠይቀው
እሺ።
እሽ እማ ግን ወላሂ በጣም ትገርሚያለሽ ከእናትየው ጋር እንዴት ልትግባቢ ቻልሽ፡ ማለቴ ያ ሁሉ ግርግር የት ገባ እናትየው በህግ እንዲያዝ ያዙኝ ልቀቁኝ ስትል አልነበር ትምሀርት ቤቱን ሁላ ካልከሰስኩ ብላ? አልኩ ኮስተር በማለትም በእናቴ ጥረት በመገረምም ፊትፊቷን በሃዘን ስሜት እየተመለከትኩ።

እንዴ ልክ ናታ አቡ ልጇ እኮ ነው እንደራስህ አስብ እንጂ።
አለች ፈገግ በማለት ወደራሷ ስባኝ ከእቅፏ ውስጥ በማስገባትና ፀጉሬን በመደባበስ።
ከእቅፏ ውስጥ ወጥቼ ጭንቅላቴን በመነቅነቅ ንግግሯ ትክክል መሆኑን አረጋገጥኩላት።
ለማንኛውም ትምህርት ቤት ጠዋት እሄዳለሁ ቀጣይ ሳምንት ወደ ትምሀርትህ ትመለሳለህ። አሁን ግባና ተኛ ብላኝ ወደመጣችበት ተመለሰች። የምር ግን ሁለት አባባሎች በጣም በጣም ትክክል ናቸው አለም ያለ ኢስላም እንዲሁም ያለ እናት ጨለማ ናት የሚሉት።

ዛሬ የሃናን ነገር ባይፈጠር ኖሮ ደስታዬ ለጉድ ነበር፡ ግን ምን ያደርጋል ከልብ የሚወዱት ሰው ለመሞትና ለመኖር በመሃል ሜዳ ላይ ሲማቅቅ እየታየ፡

የትምህርቱ ነገር ከሄኒ ሂወት ባይበልጥም በከፊሉም ቢሆን አስጨንቆኝ ነበር ብቻ አልሃምዱሊላህ እቤት መዋል እንዴት አሰልችቶኝ እንደነበር
ግን ሃናንንና ሄኒ በሌሉበት እንዴት ሁኜ ልማር ነውግን።

እማዬ ወደ መጣች በት አቅጣጫ በመመለስ ላይ ሳለች፡ እሺ በቃ እኔም በጠዋት ሃናን ጋር ሄጄ ያለችበትን ሁኔታ በስልክ ካልሆነም በአካል አጣራለሁ።
ሆስፒታል ሳይቀይሩ አልቀረም አልኳት።

እማዬ ሄኒ ሆስፒታል ገብቶ በተኛበት ጊዜ ሃናን ስትመላለስ ታያት ስለነበር ቅድም ወደ ቤት ስመጣ እንደነገርኳት ነበር ሃናንን በደንብ ያወቀቻት፡
አላህ አፊያ ያድርጋት ስትል ወደ መኝታ ክፍሉ ገባች።

አልጋዬ ላይ ወጥቼ በድፍረት ከሄኒ ጋር የተደረጉ ንግግሮችን ያለሃፍረት እመለከት ጀመር። በዛ ያሉ ነገሮች በፅሁፍ ተለዋውጠዋል ድምፆችም አሉት ግን እነሱን ከመክፈት ተቆጥቢያለሁ፡ አብዛህኞቹ ፅሁፎች በፍቅር ቃላት የተሽቆጠቆጡ ናቸው። ከታች ወደላይ በመውጣት ስለነበር ሳነብ የነበረው አስደንጋጩና አሳዛኙ ነገር ተቀምጦ ጠበቀኝ፡ የሃናን ፎቶዎች በተከታታይ ተደርድረዋል አንድ በአንድ በከፈትኳቸው ቁጥር ሃናንን ብርድ ልብስ ውስጥ ተኝታ ያለ ሂጃብ በፓካውት እና ሰውነት እጅግ በጣም አጋልጠው በሚያሳዩ ልብሶች የተነሱ ፎቶዎች ተለቀዋል፡ በእያንዳንዱ የፎቶ ክፍተት አፈቅርሻለሁ የእኔ ጣፋጭ የሚሉ ቃሎች ተልከዋል። የሄኒ ነገር ምንም ፍቅር አይመስለኝም ቃላቶቹም ቢሆኑ መሸንገያ እንጂ ለፍቅር የመነጩ አይደሉም። የፎቶዎቹ መዳረሻቸውስ የትኞቹ ግሩፕና ቻናሎች ይሆኑ ስል ለሃናን እጨነቅ ጀመር። ወደ ላይ በጣቶቼ በመታገዝ በተጓዝኩ ቁጥር በአይኖቼ ብዛት ያላቸው ቁጥሮች እመለከት ጀመር፡

ቆም ብዬ ሳነብ እያንዳንዱ ቁጥር አላስፈላጊ የሆኑ ጥያቄዎችን ይዝዋል።

በዚህ መሃል የሃኑ ስልክ የነበረው ካርድ አለቀ፡ አሁን ያለሁበት ቦታ ላይ ብዛት ያላቸው ቪዲዮዎች ከ ሄኖክ በኩል ተልከው ነበር። ከፍቼ ምንነታቸውን ለመመልከት ያለው ካርድ ስላለቀ አልቻልኩም። ግን ለፎቶዎቹ አላህ ግልፁንም በድብቅ ያለውንም ተመልካች መሆኑን ሃናን ዘንግታው ነው?።

ወዲያና ወዲህ ያለምንም እንቅልፍ ስገላበጥ የፈጅር አዛን ከቀን በተሻለ ድምፅ ተሰማ፡ ቀን ላይ አካባቢው በተሽከርካሪዎችና በሰዎች ድምፅ ስለሚዋጥ ከርቀት ያለው መስጂድ አዛኑ በከፍተኛ ሁኔታ እንደፈጅር አይሰማም

ሰላቴን ሰግጄ በክፍሌ ውስጥ ሳለሁ የጀንበሯን ብቅ ማለት በመከተል ከሃናንን ስልክ የአባቷ ቁጥር በመውሰድ በእራሴ ስልእክ ደወልኩኝ፡ የዛሬን ቀን ደስ ከሚያሰኙት ነገራቶች ውስጥ የሄኒ ከሆስፒታል መውጣት አንዱ ነው...

ክፍል ➊❼ ይቀጥላል

ሶፊ ማናትስ የትናትስ?????

https://t.me/hannyTube
148 views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 12:20:44 ከሰአታት ቆይታ በኋላ የሃናን አባትና አንድ ተለቅ ያለች ሴት ልጅ ተያይዘው ሲጣደፋ ወዳለንበት ቦታ መጡ።
እኛ ያለንበት ጋር ሲደርሱ ከእኛ ውጭ ምንም ሰው በቦታው ስለሌለ
የደወላችሁልን እናንተ ነበራችሁ?

የሃናን አባት?። አሉ ሽማግሌው ቀደም ብለው
አዎ
አዎ እኛ ነን የደወልነው።
ልጄ ሃናንን ምን ሆነች ብኝ
አለች ደህና ናት።

የት ናት ምንሆነችብኝ ልጄ የት ናት አሳዩኝ ያለ እናት ያሳደኳት ሃናን የታለች።

የሃናን አባት ከመጠን በላይ ሆስፒታሉ በጠበጡት እኔ ሆድ ብሶኝ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ። ከውስጥ የነበሩ ጥቂት ዶክተሮች ወደ ውጭ በመውጣትና ጥበቃዎች በጋራ በመሆን ያረጋጎቸው ጀመር አብራቸው የመጣችው ልጅ ለብቻዋ ግድግዳ ተደግፋ ትነፋረቃለች።

እኛ ሽማግሌ አባት የሃናን አባት ከተረጋጉ በኋላ የተፈጠረውን በስሱና በእርጋታ አስረዱ።

ሰአቱ እጅግ በጣም እየሄደ ስለሆነ ለነሱ አስረክበን እኔና ሽማግሌው አባት ከሆስፒታሉ ወጣን። ወዴት እንደሆኑ ጠየኳቸው እኛ ሰፈር አካባቢ እንደሆኑና ዘመድ ጥየቃ በቅርቡ እንደመጡ ነገሩኝ። እንዴ እንዲህ ሲጠፋ የመጡበት ቤተሰብ አይጨነቅም እንዴ ስል ጥያቄ አቀረብኩላቸው። የመጡበት ቤተሰብ ለመስጂድ ከቤት እንደወጡ እንደሚያቅ ነገሩኝ፡
አብረን ሰፈር ድረስ ዘለቅን ስልካቸውን በሃናንን ስልክ መዝግቤ ተለያየን።

ወደ ጋራ መኖሪያ ቤቱ እንደዘለኩ እማዬ በኔ ምክንያት እጅግ በጣም ተጨንቃ ከበረንዳው ላይ እንደቆመች አገኘኋት ተጠምጥሜባት ሰላም ካልኳት በኋላ ከብርዱ ወደ ቤት ውስጥ ይዣት በመግባት እንዳትቆጣኝ በተረጋጋ መንፈስ ለመስጠም እየሞከርኩ።

ያ ዘግናኙን በነ አምሪ ምክንያት የተፈጠረውን ነገር በሙሉ ነገርኳት። ከልቧም አዘነችም ደነገጠችም።

እሷ እኔን እቤት ስታጣ እጅግ በጣም ተጨንቃ ነበር። ምክንያቱ ደግሞ በተለየ መንገድ ቅድም ሃናን ይዛ በመጣቸው ያልተጣራ ወሬ በስልክ ስላወራኋት ይበልጥ ስጋቷን እንዲጨምር አድርጎት ነበር። የእኔም የቅድሙ እንደዛ መሆን በእነሱ ምክንያት የሃናንም ችግር በእነሱ ምክንያት አይ እነ አምሪ! አልኩ በመማረር

ወደ ክፍሌ ከመግባቴ በፊት በኪሴ እረስቼው ይዤው በመጣሁት የሃናን ስልክ ወደ አባትየው ጋር ደወልኩ። ስልኩን አባትየው ሳይሆን ሴቷ ልጅ አንሳትው አወራችኝ።

አሁን ወደ ሌላ ሆስፒታል ልንሄድ ነው አንፑላንስ እስኪመጣልን እየጠበቅን ነው ዱዓ አድርግልን የሚል መልእክት አስተላለፈች። ሃናን በጣም ምስኪን ሰው ላጣሽ ነው ስል አሁንም አለቅስ ጀመር።

እንቅልፍ ባይወስደኝም እማዬ እንዳትቆጣኝ በሚል ከክፍሌ ውስጥ ገብቼ ከአልጋዬ ላይ ጋደም አልኩ።

የሃናንን ስልክ በእጄ ላይ ስለሆነ የነበረው በተደጋጋሚ እከፍተዋለሁ እዘጋለሁ ግን አንድ ነገር ወደ አላስፈላጊ ብልግና ሲወስደኝ ይታወቀኛል።
አሁን ግን ከፍቼ ስልኩን አልዘጋሁትም በጣቴ የቴሌግራም አፑን ተጫንኩት እሱም ፓስዋርድ ጠየቀኝ በግምት የቅድሙን ሞከርኩ ወዲያው ተከፈተ ወይ ሃናን ሁሉንም በሄኒ ስም አድርጋ ግን ትችለዋለች። አልኩ በውስጤ በመገረም ጭምር።

ወደውስጥ እንደገባሁ በቀጥታ ከሰዎች ጋር ግንኙነት ወደ ምትፈጥርበት ቦታ(in box) አመራሁ ቆየት ብላለች ማለት ነው ስል የመጀመሪያ ላይ የተቀመጠውን የሄኖክን መልእክት አየሁ ወደ ውስጥ እንድገባ ውስጤ ይፈታተነኝ ጀመር እረ ነውር ነው.....

ክፍል ➊➏ ይቀጥላል

ሶፊ ማናትስ የትናትስ?????
124 views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ