Get Mystery Box with random crypto!

ቢጠቅሞት ካነበብነው እናካፍሎት

የቴሌግራም ቻናል አርማ beteke — ቢጠቅሞት ካነበብነው እናካፍሎት
የቴሌግራም ቻናል አርማ beteke — ቢጠቅሞት ካነበብነው እናካፍሎት
የሰርጥ አድራሻ: @beteke
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 188
የሰርጥ መግለጫ

📖⁣ማንበብ የአስተሳሰብ ልህቀትን ያጎናፅፋል።
📖⁣ማንበብ የእውቀት አድማስን ያሰፋል።
📖⁣ማንበብ የቆሸሸ ስብዕናን ያፀዳል።
📖⁣ማንበብ ምክንያታዊ ፣ጠያቂ እና የሰላ አእምሮን ያጎናጽፋል።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-14 16:06:10 " የምሥጢር ሙዳይ ሁን እንጂ የእሳት ማንደጃ ወናፍ አትሁን ። ሰዎች ሊሰሙህ በሚችሉበት ችሎታቸውና ፍላጎታቸው መጠን ብቻ ተናገር ፣ ቁጥብ እንጂ ዝርው አትሁን ። ለዕውቀት ትጋ ። በከፊል በተረዳኸው ነገር ራስክን እንደ አዋቂ አትቁጠር ። በከፊል ከማወቅ አለማወቅ ይሻላል ። ሥራ ስትሠራ ደግሞ ነገ ትቼው ለምሞተው ወይም ብሠራ የሚጠቀመው ሌላ ነው በሚል ተስፋ ቢስ ሆነህ ሳይሆን ዘላለም እንደምትኖር ያክል በመትጋት ነው ። ትጋት ጥሩ ነው ። ችኮላህ ግን ውጤት አያመጣም ፣ በችኮላ መሥራትና በፍጥነት መሥራት የተለያዩ ናቸው ። ርኩሰት የዕውቀትና ስልጣና መገለጫ አይደለምና ማንነትንና ሰብዓዊ ክብርን ከሚያጎድፉ ተግባራት መታቀብን ገንዘብ አድርግ ። "

" እናም በየዕለቱ በኑሮህ ጠንቃቃ ሁን ። ያለጸጸት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁም ነገር አሳልፍ ፤ ውሳኔዎችህ ትክክለኛ መሆናቸውን መርምር ፤ ልክ እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ወይም እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ደግመህ የምትኖረውንና ለማከናዎን የምትመርጠውን ዐይነት ሕይወት ለመኖር ሞክር ። .... "

እንዲል ዝጎራ
65 views13:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 14:40:53

“ልጄ ሆይ፤ ሰው አንድ ጊዜ ከሞተ በኋላ፤ ሁለተኛ አይገኝምና ምንም ቢሆን ሰውን ለማጥፋት አታስብ። አካሉም ከተቆረጠ በኋላ ሁለተኛ እንደ ዛፍ አያቆጠቁጥምና የሰውን አካል ለማበላሸት አታስብ። በማንም ሰው ላይ አትቆጣ።”


( "ለልጅ ምክር ለአባት መታሰቢያ" ከተሰኘው የመጽሐፉ ክፍል ውስጥ ከገጽ 87 የተወሰደ)
114 views11:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-26 18:02:04 የምትናገረው ነገር ሳይኖርህ የመናገር ዕድል ስለተሰጠህ አትናገር ።በተገኘው ዕድል ሁሉ የምትናገር ከሆነ ምንአልባት ሰዎች ከንግግርህ ይልቅ ዝምታህን ሊናፍቁ እንደሚችሉ አስብ ። አንዳንድ ጊዜ ከንግግርህ ይልቅ ዝምታህ ድምፅ እንዳለው እወቅ ።

ከቻልክ ብዙ ከመናገር ይልቅ ማዳመጥ ምርጫህ ይሁን ። እግዚአብሔር ሁለት ጆሮ እና አንድ አፍ ብቻ የፈጠረልህ ለምን ይመስልሃል ? ብዙ አዳምጠህ ጥቂት እንድትናገር ስለወደደ ነው። ብታምንም ባታምንም ሞገስህ ያለው በብዙ ዝምታህ እና በጥቂት ንግግርህ ውስጥ ነው ።
148 views15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-24 13:14:56
ዛሬ በጣም የተገረምኩትን እዩልኝማ ቤቢ ለምን አንድ ኤክስ ገባብህ እላለሁ አስተማሪው ግን ትክክል እኮ አይደለም እንዴት ደሃ እና ሀብታም እኩል ይላል በየ ቦታው በየ መንገዱ የሚታየሁ ነገር እኮ ነዉ ሁሉም ለሀብታም ነዉ ትልቅ ክብር ያለው ብሎ ከእኔ ጋር ክርክር አይ እንደዛ አይደለም ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ ክብር ይገበዋል ብዬ ብነግረውም አልዋጥ አለው ።ውዶቼ የልጆቻችን አስተሳሰብ እና አመለካከት በዙርያችን ከሚሰሙትና ከሚያዩት ነገር አንፃር ስለምያስቡ መልካም ነገሮችን ቢማሩ እላለሁ ስለገረመኝ ነዉ የፃፍኩት ሰላም እደሩልኝ
146 views10:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-18 10:12:02 "ማወቅ ያለብህ ሕብረተሰባችን እያሰበ ሳይሆን እያሳበበ መኖር የሚወድ ነው"

(ሌላሰው)
149 views07:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-26 15:40:18 ኢትዮጵያዊነት በአምስት አምዶች የታነጸ መኖርያ እልፍኝ ነው። ፩. ጥልቅና ሰፊ ዕውቀት፣
፪. መዛል የሌለበት ትጋት፣
፫. በትዕግስት የታሸ ጀግንነት፣
፬. ርኩሰት የሌለበት ቅድስና፣
፭. ግብዝነት የሌለበት ምስጢራዊ ሕይወት ነው!

:

«ከዝጎራ ገፅ፡ 315»
በዓለማዬሁ ዋሴ እሼቴ
203 views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 20:24:57 ሼር

• የተወለድነው በሌሎች ሰዎች እርዳታ ነው፡፡
• ስማችንን የተቀበልነው ሌሎች ሰዎች ባወጡልን መሰረት ነው፡፡
• የገቢ ምንጫችን የሚመጣው ከሌሎች ሰዎች ነው፡፡
• ክብርና እውቅና የሚሰጡን ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
• ገላችንን ለመጀመሪያ ጊዜ ያጠቡን ሌሎች ሰዎች ናቸው፣ ለመጨረሻ ጊዜ የሚያጥቡንም ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
• ከዚህ አለም ስንሰናበት ቤታችንና ንብረታችን በሌሎች ሰዎች ይወሰዳል፡፡
• እጃችንን ይዘው በመደገፍ መራመድ ያስለመዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው፣ በመጨረሻም እጃችንን ይዘው በመደገፍ የሚያራምዱን ሌሎች ሰዎች ናቸው፡፡
• በመወለዳችን ምክንያት በደስታ የደገሱና የበሉት ሌሎች ሰዎች፣ ስንሞትም በኃዘን የሚደግሱና የቀብር ስርአታችን የሚከናወነው በሌሎች ሰዎች ነው፡፡

ይህ ሁሉ እውነታ እያለ “ነኝ” እና “አለኝ” በምንለው ነገር የምንመካበት ጉዳይ አይገባኝም፡፡ እስቲ ያወሳሰብናትን ሕይወትን ቀለል እናድርጋትና ለመከባበርና ለመዋደድ ቅድሚያን በመስጠት እንኑር፡፡

Dr Mehret debeb
251 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 14:33:58
#የታጨደው_ስንዴ!!!!!
ለመሪዎች ወንበር የታጨደው ስንዴ
እኩል ነው መርምሩት ከሞተው ዘመዴ!!!
ቶሎ እንደታጨደው እንደስንዴው ሁሉ
ለመሪዎች ወንበር አልቋል ሰው በሙሉ!!
በዚህች በኔ ዘመን በዚች በኔ ዓለም
ለመሪዎች ወንበር ያልታጨደ የለም!!
250 views11:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 10:41:27
it seems የአፈ ቀላጤዎችና የምላሳሞች ዘመን . . ነገር ወዲያ ወዲህ ብዙ ምላስ ብዙ ወሬ ብዙ ውሸት ብዙ ብዙ ማታለሎች ብዙ ጉራ ብዙ ክፋት ብዙ ግትርነት ብዙ እዝነት አልባ ቀኖች . . .
ይህ ሁሉ ምላስ እንዲህ ተትረፍርፎ ልቦችና ህሊናዎችስ ከወዴት አሉ ?!
መልካምነቶች ቅንነቶች ትህትናዎች ለፈጣሪ ብሎ መርዳዳቶች ደግነቶችስ . . . ከወዴት ይሆን ማስታወቂያቸው የተለጠፈው
219 views07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 15:35:52
-----
".....የሰረቀን ሁሉ እጅ በመቁረጥ፥ አይን ያጠፋን አይኑን በማጥፋት ልናተርፍ የምንችለው ብዙ እጀ-ቆማጣ እና ብዙ ዓይነ-ስውሮችን ነው!"- ይላሉ ሱፊዮቹ

ስለዚህም ይላሉ...
"ማንም ይቅርታን ያላወቀ ፍቅርን አያውቅም፤ ፍቅርን ያላወቀ ደግሞ በጀሊሉ አልታቀፈም!... ሕግጋቶች(ሸሪዓ) በሙሉ በፍቅር እንጂ አልታቀፉም!

ይቀጥላሉ....
"ስለዚህም ተግባራትን በሙሉ የምንከውነው ከጀሃነም ርቀን ጀነት ለመግባት ሳይሆን ለሱ ካለን ፍቅር ነው! -መፈ'ቀር ስለሚ'ገ'ባው ነው!
'የገነት ጉጉትም ሆነ የገሃነም ፍርሃት ከኛ ይራቅ!'
እንደዛ ካልሆነ ግንኙነቱ የጥቅም ብቻ ይሆናል!" ይላሉ

አስከትለውም....
"ፍቅር-የእርሱ ባህሪና ስሙም ነው፥ አፍቃሪዎችን እንጂ አይወድም፥ ፍቅር የሌለው አምልኮም ጩኸት ብቻ ነው!"

ሰው በፍቅር ለመታቀፉስ ማሳያው ምንድን ነው?- ሱፊዮችን እንጠይቃለን!

እነርሱም ይመልሳሉ!...
"ፍቅር ያለበት ሰው ዋና ባህሪው ይቅር ማለትን [ምህረት ማድረግን]ማወቁ ነው!

...ለሰው ይቅርታን ሳያደርግ ከሰማይ ይቅርታን እንደሚጠብቅ ሰው ከንቱ የለም!"

እስቲ ይቅርታን በደንብ ግለፁልን?- ያለመታከት እንጠይቃለን

"....ይቅርታ[ምህረት ማድረግ] ማለት ልክ እንደ [ፅጌረዳ] አበባው እየቀጠፍከውም እንደሚሰጥህ ጥሩ ሽታ ማለት ነው!"
#ሱፊዝም
184 views12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ