Get Mystery Box with random crypto!

🌹Islamic_deawa 🌹

የቴሌግራም ቻናል አርማ hanan_eslamik_deawa — 🌹Islamic_deawa 🌹 I
የቴሌግራም ቻናል አርማ hanan_eslamik_deawa — 🌹Islamic_deawa 🌹
የሰርጥ አድራሻ: @hanan_eslamik_deawa
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 757
የሰርጥ መግለጫ

✅group @lslamic_daewa_group 📩✍ሀሳብና አስተያየት ካላችሁ
👇👇👇👇👇 @hananoffichihalbot 👆👆👆👆👆

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-06 08:30:30 የዓሹራ ቀን ትሩፋት!
---------------
ዓሹራ ቀን ከአሏህ ወር ከሆነው ከሙሐረም በረከቶች አንዱ ነው። እሱም ከሙሐረም 10ኛው ቀን ነው። ወሩን ወደ አሏህ ማስጠጋት ትልቅ ደረጃና ትሩፋት ስላለው ነው። ምክንያቱም አሏህ ምንንም ነገር ወደሱ አያስጠጋውም ልዩ ፍጡሮቹን በስተቀር። ( ስለሆነም ነው ሙሐረም ወር የአሏህ ወር የተባለው፤ ከሌሎቹ በተለየ መልኩ)።

የአሏህ መልክተኛ – ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም – እንዳሉትም፦ [ ከረመዷን ቀጥሎ በላጩ ፆም የአሏህ ወር ሙሐረም ወር ነው።] ሙስሊም። አስረኛው ቀን (ዓሹራ) ክብር ሲሰጠው የነበረው ከቀምት ጀምሮ ነው። የዚህ ቀን ትሩፋት ደግሞ ትልቅ ነው። ነቢዩሏሂ ሙሳንና – ዐለይሂ አስ–ሰላም – ህዝቦቹን ነጃ ያወጣበት፤ ፊርዓውንን ከነ ሰራዊት በባህር ያሰመጠበት ቀን ነው። ሙሳ – ዐለይሂ አስ–ሰላም – ለአሏህ ምስጋና ብለው ፁመውታል። ቁረይሾች በጃሂሊያ ዘመን ይፆሙት ነበር። አይሁዶችም እንደዛው። ረሱልም – ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም – [ ከእናንተ ይልቅ እኛ ለሙሳ ተገቢና ቅርብ ነን።] አሏቸው። ቡኻሪና ሙስሊም እንደዘገቡት። ነቢዩም ፆመውታል። እንዲፆምም አዘዋል። መጀመሪያ ጊዜ ግዳጅ ነበር፤ የረመዳን ፆም ግዴታ ከመጣ በኋላ ወደ ሱናነት ዞሮዋል።

በመሆኑም 9ኛውንም ቀን ጨምሮ ከ10ኛው ( ዓሹራ) ጋር መፆም ይወደዳል። አይሁዶች 10ኛውን ብቻ ስለሚፆሙ፤ እነሱን ለመቃረን ተብሎ።

ትልቁ ትሩፋቱ ያለፈውን የአንድ አመት ወንጀል ያሰርዛል። ይህ ነው ንፁህ በሆነው ሱና የፀደቀው።

በዚህ ቀን ከፆም ውጪ የተደነገገ አንድም ነገር የለም!
-
ከሸይኽ ሙሐመድ ዐሊይ ፈርኩስ ከፈትዋ ቁ ፡ 592 የተቀነጨበ።
-
ሁሉም በፆሙ ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ ሼር አድርጉላቸው! አሏህ ተጠቃሚ ያድርገን!
87 views🅂🅈🄷, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 08:30:20 የዓሹራእ ፆም

ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን – ረሒመሁሏህ – እንዲህ ይላሉ፦

የዓሹራእ ፆም ④ ደረጃዎች አሉት፦

①ኛው ደረጃ፦
9፣10ና 11ኛውን መፆም። ይህ ትልቁ ደረጃ ነው። ምክንያቱም ኢማሙ አሕመድ በሙስነዳቸው እንደዘገቡት፦
[ (ከዓሹራእ) ከፊቱ አንድ ቀን እና ከኋላው አንድ ቀን ፁሙ። አይሁዳውያንን ተቃረኑዋቸው።] አንድ ሰው ሶስት ቀን በመፆሙ ተጨማሪ በአንድ ወር የሶስት ቀንን ፆም ደረጃ ያገኛል።

②ኛው ደረጃ፦
9ኛውና 10ኛውን መፆም። ነቢዩ – ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም – “ አይሁዶች አስረኛውን ቀን ይፆሙ ነበር ” ተብሎ ሲነገራቸው [ ወደ ቀጣዩ አመት ከቆየሁ ዘጠነኛውንም ቀን እፆማለው።] ማለታቸው።

አይሁዶችን መቃረን ይወዱ ነበር። እንዲሁም ከሃዲያንን በሙሉ።

③ኛው ደረጃ፦
10ኛውን ከ11ኛው ጋር መፆም።

④ኛው ደረጃ፦
10ኛውን ብቻ መፆም። ከፊል ዑለማዎች ይህንን “ይፈቀዳል” ሲሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ “ብቻውን ነጥሎ መፆም ይጠላል” ብለዋል።

"ይፈቀዳል" ያሉ ዑለሞች መረጃቸው፤ ነቢዩ – ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም – ስለ ዓሹራእ ፆም በተጠየቁ ጊዜ “ የበፊቷን አንድ አመት ወንጀል ያሰርዛል ” ብለዋል። እዚህ ጋ ዘጠነኛውን ቀን አልጠቀሱም የሚለውን ንግግር በመያዝ ነው።

አስረኛውን ነጥሎ መፆም "ይጠላል" ያሉ ዑለሞች መረጃቸው፤ ነቢዩ – ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም – [(ከዓሹራእ) ከፊቱ አንድ ቀን እና ከኋላው አንድ ቀን ፁሙ። አይሁዳውያንን ተቃረኑዋቸው።] ማለታቸውን ሲሆን፤ ይህ ሐዲስ አይሁዳውያንን ለመቃረን አንድ ቀን መጨረም ግዴታ መሆኑን ያስገነዝባል። ወይም ነጥሎ መፆም መጠላቱን ያስረዳል። ይላሉ።

#መነጠሉ_ይጠላል_የሚለው_እንደ_መረጃ_ጠንካራ_ነው! ስለዚህ አንድ ሰው ከኺላፉ ለመውጣት ከበስተፊቱ 9ኛውን ወይም ከበስተኋላው 11ኛውን ቢፆም የሚለውን እንደግፋለን።”

ሊቃኣቱ አልባቢል መፍቱሕ 95
84 views🅂🅈🄷, 05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 13:11:07 #እህቴ ልንገርሽ አድምጪኝ

ሀጂ ነብይ ወንድ በተቀላቀለበት ግሩፕ ተጨምረሽ መናገር ያለብሽን ተናገሪ በስተቀር
#ክክክክክክ
@kkkkkkkk
@hahaha አትበይ::

እስቲ ልጠይቅሽ ምላሽ እፈልጋለዉ ካንቺ በአካል ቢሆን ኢሄ የግሩፕ ስብስብ !? በዚህ መልኩ ተጨምሮ እንኳን ለመንካካት መደባለቅም አይቻል አደል እንዴ!?

ማሸአላህ አላህ ይጨምርልሽ ተሳትፎሽ ዒልምሽ ነገር ግን አንዳንድ እህቶች አሉ እንደ ወፍጮ
#ክክክክክክክክከክ የሚሉ::

አድቢ እህቴ አላህ ይመለከትሻል ከቀኝና ከግራ ያሉ መላይካዎች ንግግርሽን ይመዘግባሉ::

በል አንዳንዴ ዝም ብሎ የወሬ ግሩፕ ይከፈትና ስገቡ ሀሜት አሉባልታ ወሬ ሴቷ ከወንዱ ጋ ዉዴ ምኔ እያለች ስትለፈልፍ ትመለከታላቹ:: ፈታ በሉ ይላሉ የግሩፑ አሚሮች ስሙ
#መሀመድ #አህመድ ስሟ #ሀናን #ኸድጃ #ጀሚላ የሆነ ሁላ #ኢናሊላሂ_ወኢና_ኢለይሂ_ራጁኡን

በሀራም ነገር ነዉ ፈታ!? ወንድን ከሴት አደባልቀህ ከኢስላማዊ ንግግር ማይጠበቅ ነገር እንዲያወሩ እየፈቀድክ ነዉ ፈታ!?

,እዛ ግሩፕ ለሊት 4:00 6:00 ብገቡ ወሬ ነዉ ሴቷ ሀያዕዋን ትታ ወንዱም እንደዛዉ::
#እህቴ_አላህ_እኮ_ይመለከትሻል_ያይሻል::
በዚ ሰአት አንድ አማኝ ወደ ጌታዉ ሚቃረብበት ሰአት ነዉ::

#እህቴ ሆይ አድቢ ለወንድሞችሽ የፊትና በር አትክፈቺ:: አላህ ሱብሀነ ወተአላህ #ዚናን አትስሩ ሳይሆን #አትቅረቡ ነዉ ያለዉ::

ወደ
#ዚና መዳረሻ መንገዶችን አትቅረቡ:: ቤትሽ ቁጭ ብለሽ በጅሽ በምፅፊያቸዉ ፅሁፎች ወንድሞችሽን ለፊትና እየዳረግሽ ነዉ::

ነገ አላህ ፊት ስቀርቢ የገዛ እጅሽ ጠላት ሆኖ ይመሰክርብሻል የገዛ አይንሽ ይመሰክርብሻል::

ነገ አላህ ፊት ስቀርቢ በጊዜሽ በገንዘብሽ (ዳታ ሚበላብሽ) በያንዳንዱ ነገርሽ ይጠይቅሻል::

ታድያ
#እህቴ ምንድን ነዉ አላማሽ ዛሬ ለጋ ታዳጊ ወጣት ወደ አኸራ ሄደ ኤኬሌ ሞተ ሲባል አልሰማሽም!? አንቺ መሞቻሽን ታዉቂዋለሽ!? ዛሬ!? ነገ!? መች!? አላህ ብቻ ነዉ ሚያቀዉ ድንገት ሞት ይመጣል ሳያስፈቅድሽ ሊወስድሽ ላትመለሺ ወደዚች የዱንያ ሂወት::

ተዉበት አድርጊ ለወንድሞችሽ መበላሸት ወንጀል ሰበብ አትሁኚ::

በየ ግሩፑ
@kkkkkkkkkkkk @Hahahaha አትበይ:: ሰዉ ባያይሽ ረቡና ከላይ እያየሽ ነዉ አንሶላ ብትለብሽሚ ከረቡና አይን አታመልጪም::

#ቁጥብ_ሁኚ_ዉድ_ትሆኛለሽ::

ሀያእ አይናፋርነት መልካም ነገርን እንጂ ሌላን አያመጣም::

bint nesro

https://t.me/+KoYMWLdIV7AzNjk0
129 viewsⓈⓄⒻⒾⒶ, 10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 17:59:56 እህቴ በእለተ ኢድ አል አድሀ አረፋ እህቴ ውድ እህቴ የተከበርሽ እህቴ እነዚህን ነገሮች አትዳፈሪ እህቴ አላህን ፍሪ ኢተቂላህ አላህን ፍሪ እነዚህን ከማድረግ ተቆጠቢ ከዛም አጠገብሽ ያሉትን አስጠንቅቂ ኢተቂላህ እህቴ ምን ያህል እንደማስብልሽ ወላሂ እህቴ በመንገዴ እኮ እናንተን የሚነካ ካለ አለቀውም በቻልኩት አቅም እታገለዋለሁ በአላህ ፍቃድ አሸናፊ ነኝ እነዚህን

1 እህቴ በአላህ ይሁንብሽ ወደ ሰላት ቦታ ከጥሩ ጓደኞችሽ ጋር ሂጂ እነዚያ ክብርሽን ዝቅ ስታደርጊ ደስ ከሚላቸው ጋር አትሂጂ አደራ እህቴ በአላህ

2 አደራ ታክሲም ላይ የትም ላይ ድምፅሽን ቀነስ አድርገሽ አደራ እህቴ ኢተቂላህ

3 አደራ ተክቢራ ስትዪ ከወንድ ጋር ተቀላቅለሽ እንዳይሆን በሴትነትሽ ድምፅሽን ዝቅ አድርገሽ አላህን አወድሺው እህቴ አደራ

4 አደራ ኢተቂላህ አላህን ፍሪ አላህን ፍሪ አላህን ፍሪ እህቴ ሰዎችን የሚጣራ ሽቶ ልብስ ጌጣጌጦች አደራ እህቴ የኢዱ ቀን እኮ አላህን የምናወድስበት የምናመሰግንበት ነው መሆን ያለበት ወላህ አንድ ቤት አውቃለሁ ለአረፋ እየተዘጋጁ ከቤታቸው አንድ ሰው ሞተ እና እህቴ አደራ አላህን ፍሪ

5 ኢተቂላህ እህቴ ወንድሞችሽን ወደ ዝሙት አትጥሪ እህቴ ኢተቂላህ በልብስሽ በጌጥሽ በሽቶሽ አደራ እህቴ ለዝሙት ብሎ የሚወጣ ወንድ አይጠፋም አንቺ ከተሰተርሽ ሀሳቡ አይሳካም አንቺ ግን ከተገለፅሽለት ያሀ ስሜቱ ይቀሰቀስበታል ከሸይጣን ጋር አንድ ላይ ያብሩበታል

6 አደራ እህቴ አላህን ፍሪ ከሰገድሽ በኋላ ከወንድጋር ሳትቀላቀይ ወደ ቤትሽ ከተቀላቀልሽ ሰዎች አሉ እነዚያ ለወሲብ ስሜታቸው የሚኖሩ መንገድ በተጨናነቀ ጊዜ ረጋጣሚውን በመጠቀም የእህቶቼን የተከበረ ሰውነት በቆሻሻ እጁ ይነካል አላህ እጁን ይያዘው እህት ምን ያህል ያስጠላል እህት ትወጂዋለሽ ይህን ተግባሩ መጥቶ የተከበረ ሰውነትሽን ሲነካ ደስ ይልሻል እህቴ በዚህ ወጥመድ ላለመግባት ጠንቀቅ በይ እህቴ


7 አደራ ከተሰገደ በኋላ በፍጥነት ወደ ቤት በመመለስ እኖቶቻችንን አቤቶቻችንን እንግዳዎቻችንን እንካድም ወላጆችን መካደም አላህን ማስደሰት ነው አደራ እናቴን ካድሚያት ያቺ በምድር ላይ ምትክ የሌላት አባትንም አደራ እንግዶቻችንን እናክብር ኢተቂላህ

8 የማከብርሽ የምጠነቀቅልሽ የምሳሳልሽ እህቴ ቀኑን በተክቢራ እንዳንረሳ አላህን እናስደስት አላህን እናጥራ ኢዳችን አላህን የምንገዛበት ነው መሆን ነው ያለበት አደራ እህት ስሜቱን ለሚከተል ወራዳ ፊት አትስጪ በሸሪአ አላህ በደነገገው ነብዩ ባዘዙት መሰረት ነው መሆን ያለበት እህቴ አላህን ፍሪ ኢተቂላህ




እህት ይህን ስፅፍ አንቺን በነዚህ ተግባራት ጠርጥሬሽ አይደለም ግን ሰው ይፈተናል በሁለት ነገሮች አንደኛው በደስታው አመቱን ወሩን በሙሉ እሱ ሚታወቀው በኸይር ስራው ነውየደስታው ቀን ባልጠበቅነው ቦታ እናገኘዋለን የአላህን ዲን ጥሶ ሁለተኛው ደግሞ በሀዘን ወቅት ሰዎችን በሰብር ያዝ ነበር በራሱ ሲደርስበት ሰዎችን ሲከለክል በነበረው ተግባር ይገኛል ለዚህ ነው እህቴ ተረዳሽኝ ? እህቴ አስብልሻለሁ እጨነቅልሻለሁ እህቴ እነዚህ ላለማድረግ ከልብሽ በአላህ ስም ቃል ግቢልኝ ፅሁፋ በኢተቂላህ ታጅቧል ይህን ከተዳፈርን ያሳዝናል እህቴ አላህ ይዘንልን ፈተናዎች ወደ እኛ ነጎዱ ወላሂ እኛ ደግሞ ቀን በቀን በአመፃችን ብሶብናል ማክሰኞ ወደ ቀራኒዮ አካባቢ የዘነበው ዝናብ ሀይለኛ እንደሆነ ሰምቻለሁ መስጂዶች አዛን እስከማለት ደርሰው ይህን ቢያንስ በእኔና በአንቺ ምክንያት ፈተና አይምጣ ለኸይር ሰበብ እንሁን




ውድ የተከበርሽ የምድር ማጣፈጫ ለህይወት ቅመም የሆንሽ እህቴ ይህን ፅሁፍ ለእህቶችሽ አስተላልፊ አደራ ሼር አድርጊ እህቶችሽንም አስጠንቅቂ አላህ ይጠብቅሽ አላህ ሁሉንም ኸይር ያድርገው ኸይሩን ያምጣልን ከሸረኞች ይጠብቀን ቃል ግቢ እህቴ

https://t.me/joinchat/KoYMWLdIV7AzNjk0
352 viewsAlhamdulillah, 14:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 23:26:00 አትገረሙም!?

በሶሃቦች ዘመን ሃላሉን ነገር አግርተው ሃራሙን አክብደውት ነበር!
በኛ ዘመን ደግሞ ሃላሉን አከበድነው ሃራሙን አቀለልነው!

ድሃ የሆነ በዲን ጠንካራ የሆነ ወጣት አንዲትን ሴት ለትዳር ባስጠየቀ ጊዜ ቤተሰብ እሽ አይልም ድህነቱን አይተው..

ሃብታም አመፀኛ የሆነ ወጣት የጠየቃቸው ጊዜ ደግሞ እሽ ብለው ይቀበላሉ.. ያንን አመፀኛም ችግር የለውም አላህ ያቀናዋል ብለው ይቀበሉታል..

ለምን ከድሃው ላይስ አላህ ይሰጠዋል ብለው አላሰቡም አላህ አይደል እንዴ ለሁሉም ሃብት ሚሰጠው!?

አረ ወዴት እየሄድን ነው!
t.me/umumahi1 t.me/umumahi1
260 views🅂🅈🄷, 20:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 07:34:50 ክፍል አራት


በጋብቻ ስም የሚሰሩ የሃራም መንገዶችና ሌሎች የማናስታውላቸው ወደ ሃራም የሚወስዱን መንገዶች።


በጣም ወሳኝ ማስታወሻ ሁሉም እህቶቻችን ማወቅ ያለባቸው እሳት ውስጥ ከመግባታቸው በፊት።
ሃቅን ፈላጊ ለሆናችሁ እህቶቻችን ማስታወሻው ይጠቅማችኋል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ። እያወቁ ለሚያጠፉትም አላህ ሰበብ ያድርግላቸው።

የሃራም መንገዱን /መፍትሄውን /እና ምክር


ክፍል አራት


አንዳንዶቹ ደግሞ ፍቅረኛ ተብየ ወንዶች ሴቶችን ዚናን ይጠይቋቸዋል ሴቷም ጠንካራ ሆና አልፈልግም ትለውና እንደዚህ የምታስብ ከሆነ እንለያይ ስትለው አይ በቃ አላስብም ከዚህ በኋላ ይላታል። ይሄ ውሽት ነው ዚና የሚጠይቃችሁ ወንድ ካለ በቃ የመጣውም ህይወትሽን ሊያጨልመው እንጂ ለጥሩ ነገር ፈልጎሽ እንዳልሆ ማሰብ አለብሽ እናም ልትርቂው ይገባል።
አይ መጠየቁን ከተወውማ ብልሽ በዛው ከቀጠልሽ ልጁ የሚጠብቀው የተመቻቸ ሁኔታ እንጂ ሃሳቡን ቀይሮት እንዳልሆነ ታይዋለሽ እናም ከመፈተናችን በፊት ከዚህ መንገድ እንራቅ!

ሲጀመር አብዘሃኛውን ሰው ማየት እንችላለን ይሄን የፍቅር ግኑኝነት ለወሲብ ነው ሚፈልጉት እንደውም አንዳንድ ወንዶችም አብረን ካልተኛን በምን አምንሻለሁ ወሲብ ካላረግን ምኑን ጓደኛ ሆን ይላሉ የሚገርመው በዚህ ተራ ሰበብ ተታለው ዚና ላይ የወደቁ ብዙ ናቸው። አላህ ይጠብቀን
እኔ ምለው ግን ፍቅር ማለት ይሄ ነውንዴ አብሮ መተኛት ነው፣ መሳሳምና ተቃቅፎ መሄድ ነው?
እስከመቸ እህቶቻችን እንደሚሸወዱ አይገባኝም ውድ እህቴ ንቂ ወላሂ ይሄ ግኑኝነት የውሸት ነው!!


አንዳንዶች ደግሞ ማለትም በዚሁ በሃራም ፍቅር ያሉ ሰዎች ሴቷ ከሃራም መራቅ ፈልጋ እንራራቅ በዚህ ሰአት መጋባት ካልቻልን ስትለው
ወንዱም የሴቷን የዋህነት በመረዳት
ታንቄ አወሞታለሁ፣ በባህር እሄዳለሁ፣ እጠፋለሁ፣ ምግብ አልበላም፣ ከቤተሰብ እወጣለሁ ሌሎችንም ማስፈራሪያ ይጠቀማል በመጀመሪያ እህቴ እንድታምኚኝ የምፈልገው ነገር ይሄ ሁሉ ነገር ውሽት ነው በጭራሽ እንዳታምኚው አንቺን ለማስቀረት የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው። በዚህ መንገድ ብዙ እህቶች ተታለው ከሃራም መራቅ ፈልገው መውጣት ያልቻሉ አሉ እና እህቴ ይሄ የውሸት ማታለያ ነው ምንም ነገር እንዳታምኚ
አደርገዋለሁ ካለ ያድርገው አንቺ ምን አሰጨነቀሽ አንቺኮ ወደ አላህ ልትቀረቢ ነው ይሄን ነገር የምታደርጊው ስለዚህ ምንም ነገር መጨነቅ የለብሽም። አንቺ ብቻ ለአላህ ብለሽ ልጁን እራቂው ለሌላው ነገር አትጨነቂ ወደ አላህ እንቃረብ ሃላል ማድረግ ካልቻልን እንለያይ ስትይው የማይሰማሽ ከሆነ እንደፈለገ መሆን ይችላል ቅንታት ታክል እንዳትጨነቂ።


ውድ እህቴ ካለፉት እህቶችሽ ተማሪ!

(አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)

ክ ፍ ል አምስት ይ ቀ ጥ ላ ል


በዚህ መንገድ ሌላ ጥያቄ ካላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ እንዲሁም ይሄንንም መንገድ አስተላልፈው ትምህርት ይሆናል የምትሉት ካላችሁ በውስጥ ፃፉልኝ። ከሃራም መንገድ ለመውጣት ከአላህ በታች እገዛ ካስፈለጋችሁ ማማከር ትችላላችሁ።

@Jezakellah
@Jezakellah


ሟር ሟር ሟር ሟር ሟር ሟር

ለሴት ጓደኞቻችሁ በምትችሉት ሼር አድርጉት።
አንዲት ሴት ከ15 ላላነሱ እህቶች ሼር ታድርግ እንዲሁም በግሩፖች ሼር አድርጉት። ጀዛከላሁ ኸይረን


ያለፉትንና የቀሩትን አስተማሪ ፁሁፎች ቻናሉን ተቀላቅላችሁ ተከታተሉን
በዝሙት አንዘምን ๓
Join us on
telegram channel

https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
280 views🅂🅈🄷, 04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 07:34:33 ክፍል ሶስት


በጋብቻ ስም የሚሰሩ የሃራም መንገዶችና ሌሎች የማናስታውላቸው ወደ ሃራም የሚወስዱን መንገዶች።


በጣም ወሳኝ ማስታወሻ ሁሉም እህቶቻችን ማወቅ ያለባቸው እሳት ውስጥ ከመግባታቸው በፊት።
ሃቅን ፈላጊ ለሆናችሁ እህቶቻችን ማስታወሻው ይጠቅማችኋል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ። እያወቁ ለሚያጠፉትም አላህ ሰበብ ያድርግላቸው።

የሃራም መንገዱን /መፍትሄውን /እና ምክር


ክፍል ሶስት

የሚገርመው ይሄን መንገድ ኒቃቢስቶች ሳይቀሩ እየተሸወዱበትና መጨረሻው ወደ ሃራም እየወሰዳቸው ነው ሚገኘው።

አንዳንድ ወንዶች አንዲትን ሴት አይተው ቁጥብ መሆኗን በተለያየ መንገድ ያውቃሉ በአላባበሷ ሊሆን ይችላል ወይም መስጅድ ስትመላለስ ሊሆን ይችላል እናም ወንዱ ቁጥብ መሆኗን ሲያውቅ በሃራም ለማግኜት መንገዱን ይጀምራል ከዛም ስልኳን ፈልጎ ወይም ከሷም በሆነ መንገድ ተቀብሎ እሷን የሚያሳምንበት የውሸት ሰበቦችን ይደረድራል። በዲኔ ደካማ ነኝ እንዳንቺ አይነት ጠንካራ እህት ያስፈልገኛል ፣ቤተሰብም የለኝም ፣ ሰዎችም አይወዱኝም እያለ በቃ የተለያየ ምክንያት በማቅረብ እንደማንም አሳዝኖ ከልጅቷጋ በፁሁፍ ማውራት ይጀምራል ከዛም በቃ እንደ እህትና ወንድም እንሁን ሌላ ምንም አልፈልግም ይላታል እሷም እውነት መስሏት እሽ ትለዋለች ከዛም መጀመሪያ ላይ ስለዲን ያወራታል ከዛ እየቆየ ወሬው ሁሉ ይቀየራል እሷም መቅረብ ካለባት በላይ ድምበር አልፋ ትቀርበዋለች አጅ ነብይ መሆኑንም ትረሳዋለች በዛ መሃል ልጅቱ በልጁ ትሳባለች ማለትም በፊት ሲያወራት በነሩት የውሸት የእዝነት ቃላቶች ተፅእኖ ይፈጥርባታል ከዛም ልጁ የሚፈልገውን ሃራም ነገር ካልሰጠችው እንደሚርቃት ይነግራታል ከዛም ልጁን ከማጣው ብላ ወደ ሃራም ግኑኝት ተገባለች። ከዛ መጨረሻው ዚና ይሆንና ህይወቷን አበላሽቶ ይርቃታል።
በተለይ ወንዶች አንዴ ዚና ካደረጉ ወዲያው ነው ከልጅቱ ላይ ያለው ፍቅራቸው የሚወጣባቸው ከዛም ልጅቱን እንደ ወሲብ እቃ በማየት ለስሜቱ ማራገፊያ ነው ሚጠቀማት ልጅቱም የሚወዳት እየመሰላት ህይወቷን መከራ ውስጥ ትከተዋለች መጨረሻውም መለያየት ነው ሚሆነው ምክያቱም አላህን አስከፍተን መቸም ጥሩ ነገር አናገኝም። በዚህ ምንገድ አልፈው ብንጋባ እንኳ ትዳራችን በፈተና የተሞላና የሚያስጠላ ነው ሚሆንው ምክንያትም ቤት ውስጥ በፊት የነበረውን ነገር ነው ሚያደርጉት ከዛም መሰለቻቸት ይመጣል ትዳር ማለት ደግሞ አብሮ መተኛት ብቻ አይደለም።

አያችሁ ሸይጧን ትንሽ ክፍትት ብቻ ነው ሚፈልገው!
ስህተቶችን ቶሎ ማረም ካልቻክን ወደ መጥፎ መዘዝ ነው የሚያስገባን።

ውድ እህቴ ወንድሜ ብለሽ ስለቀረብሽው የስጋ ወንድምሽኮ አይሆንም ወይም አጅ ነብይነቱ ሊጠፋ አይችክም ይሄ ትልቅ የሆነ ስህተት ነው ቁርዓን የሚያቀራሽ ቢሆን እንኳ ልቅ ሁነሽ ልትቀርቢው አይገባም አጅ ነብይሽ ነው እናም አላህን እንፍራ በዚህ ምንገድ በጣም በርካታ ሰዎች አሉ እና ድምበር አንለፍ ሃቁን እያወቅነው ስሜታችንን አንከተል። መጨረሻው ፀፀት ነው።

አንደኛ ልጁ በዲኔ ደካማ ነኝ ካለሽ መስጅድ ሂደህ ቅራ በይውም ከዛ ውጭ ደግሞ ከቻልሽ አንዳንድ የሱና ቻናል ላኪለትና ልጁን ብሎክ አድርጊው ከዛ ውጭ እንደ ቀላል አይተሻቸው አንዳንድ ነገር ምታወሩ ከሆነ አንደኛ ይሄ የሃራም ምንገድ ነው ሁለተኛ ወደ መጥፎ መንገድ እየሄድሽ መሆኑ ልትረሽው አይገባም በሃራም ምንገድ በሃራስ መተማመን ሚባል ነገር የለም።

እና ውድ እህቴ እንደዚህ ልቅ ሁነሽ ቀርበሽው እንዴት ከወንድምና ከእህትነት ውጭ የሆነ ነገር አይፈጠርም ብለሽ ታስቢያለሽ? ይሄ ራስን ማታለል ነው አንዳንዶች ራሳቸውን ለመሸወድ ሲፈልጉ እኔ ከወንድምነት ወይም ከእህትነት ውጭ አልፈልግም ይሉና አቀራረባቸው ግን ልክ እንደ ባልና ሚስት ነው እናም ራሳችሁን አትሸውዱ ግንኙነታችሁ ወደ መጥፎ ነገር ከመቀየሩ በፊት ሁኔታችሁን አስተካክሉ።
በዛ ምንገድ ተቀራርባችሁ ወደ ትዳር መቀየር ፈልጋችሁም ከሆነ ቶሎ ወደ ትዳር ቀይሩት ከዛ ውጭ በዛ ስሜት ላይ ሁናችሁ ከቀጠላችሁ መጨረሻው እራስን እሳት ውስጥ መጣል እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም አላህን እንፍራ ወደ አላህ እንመለስ

አንዳንዶች ደግሞ እንደ እህት እንቀራረብ ይሉና ልጅቱን ወጥመድ ውስጥ ማስገባት ፈልገው ከግዜ በኋላ ወድጄሻለሁ ፍቅረኛ እንሁን ይላታል እሷም በማውራት ብዛት ልጁን ትወደውና እንዳይለያት በማሰብ አላህን አስከፍታ ግኑኝነታቸው ወደ ሃራም ይቀየራል ይሄ አንዱ የወንዶች ማጥመጃ ዘዴያቸው ነው። እንንቃባቸው

ሌላው እንደዚሁ እንደ እህት እንቀራረብ ብለው ከግዜ በኋላ አፈቅርሻለው ፍቅረኛ እንሁን ይላታል እሷም እንደ ወንድም ስለቀረበችው እኔ ከወንድምነት ውጭ አስቤህ ስለማታውቅ እንደዛ መሆን አንችልም ስትለው እሱም እሽ በቃ ትቸዋለሁ እንደ እህት እንቀጥል ይላታል እሷም እሽ ብላ እንደበፊቱ ትቀጥላለች። ውድ እህቴ እንዴት ብሎ ነው ፍቅር ይዞት ከነበረ ወደ እህትነት ሊቀየር የሚችለው? ይሄ ውሸት ነው እንደ በፊቱ እንቀጥል የሚልሽ አንቺን ወጥመድ ውስጥ ለመጣል ወይም ፍቅር አስይዛለሁ ብሎ ያልሆነ ነገር አደርጋለሁ ብሎ ስለሚያስብ ነው እናም ከዚህ የሸይጧን መንገድ ቶሎ እንራቅ


በዚህ ምንገድ በጣም ብዙ እህቶች ስህተት ይሰራሉ እየተሸወዱም ነው ከነሱ ትምህርት እንውሰድ!
እንደወንድም ተቀራርባችሁም ይሁን ድምበር ያለፋችሁ ካላችሁ ከዚህ ምንገድ ራሳችንን እናውጣ ገና እየገባንበትም ከሆነ ከዚህ ምንገድ እንራቅ። ካልገባንበትም ራሳችንን እንጠብቅ።
ቁጥብ መሆን ለራስ ነው ሚጠቅው።!

(አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)


ክ ፍ ል አራት ይ ቀ ጥ ላ ል


በዚህ መንገድ ሌላ ጥያቄ ካላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ እንዲሁም ይሄንንም መንገድ አስተላልፈው ትምህርት ይሆናል የምትሉት ካላችሁ በውስጥ ፃፉልኝ። ከሃራም መንገድ ለመውጣት ከአላህ በታች እገዛ ካስፈለጋችሁ ማማከር ትችላላችሁ።


@Jezakellah
@Jezakellah


ሟር ሟር ሟር ሟር ሟር ሟር

ለሴት ጓደኞቻችሁ በምትችሉት ሼር አድርጉት።
አንዲት ሴት ከ15 ላላነሱ እህቶች ሼር ታድርግ እንዲሁም በግሩፖች ሼር አድርጉት። ጀዛከላሁ ኸይረን


ያለፉትንና የቀሩትን አስተማሪ ፁሁፎች ቻናሉን ተቀላቅላችሁ ተከታተሉን
በዝሙት አንዘምን ๓
Join us on
telegram channel

https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
222 views🅂🅈🄷, 04:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 18:25:13 ለእህቶች መልዕክት
                
الحمدلله وحده، والصلاة والسلام على من لا نبي بعده؛ أمابعد:


ምክር ለ ኒቃብ እና ጂልባብ
ለባሾች እንዲሁም ኒቃብ
ልበሱ ስትባሉ ኢማን በልብ
ነው ለምትሉ እህቶች

➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊➊

➜ ኒቃብ እና ጅልባብ በሚለብሱ እህቶች ልጀምር
➼ በመጀመርያ ይህንን የተከበረ ልብስ እንድትለብሱ ልባቹሁን ክፍት ያደረገላችሁን አላህ ልታመሰግኑት ይገባል። ይህን የተከበረ ልብስ ስትለብሱ ፅናት ሊኖራቹህ ይገባል። ይህን ልብስ በመልበሳቹህ ብቻ የተለያዩ ሰዎች ከእውነታው የራቀ ትችት ሊሰነዝሩባችሁ ይችላሉ ምናልባት 'ፋራ' ሊሏቹህ ይችላሉ ራሳቸውን 'አራዳ' አድርገው በማሰብ ' ገጠሬ ' ይሏችኋል 'ከተሜ ' የሆኑ መስሏቸው የመሳሰሉ የተለያዩ ትችቶችን ይሰነዝራሉ ይሄኔ ግን እናንተ እውነታው ባገልባጩ መሆኑን ተረድታችሁ በፅናት ወደፊት ልትጓዙ ይገባል። ፋራዎች ተባልን ብላቹህ የለበሳችሁትን ኒቃብ አሊያም ጂልባብ እንዳታወልቁ። አይደለም ፋራ ሌላም ሊሏቹህ ይችላሉና!!!

➭ ሁሌም ሐቅ ላይ ያለ ሰው መተቸቱ የማይቀር ነው ነገር ግን ሐቅ ላይ እስከሆነ ድረስ ትችቱ አይጎዳውም።

➪ ሰለፎች ሐቅ ላይ የነበራቸውን ፅናት ተመልከቱ አይደለም ስድብ ስንት ድብደባ እና ግርፋት ደርሶባቸው ከአቋማቸው ዘንበል አላሉም ። ስለዚህ አርአያዎቻችሁን አላህ ያወደሳቸውን ትውልዶች በማድረግ ከአቋማችሁ በትንሽ ድግሪ እንኳን እንዳትዘነበሉ።

➺ ሶስተኛው እና ይበልጥ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነጥብ ደሞ የኢኽላስ ጉዳይ ነው። ማንኛውንም ኢኽላስ የሌለውን ስራ አላህ እንደማይቀበለው ተናግሯል። ስለዚህ ይህንን በመረዳት ኒቃቡን አሊያም ጂልባቡን የለበሳችሁት የአላህን ፊት ፈልጋችሁበት እንጂ የሰውን ፊት ፈልጋችሁበት ሊሆን አይገባም።

➲ ኒቃብ የለበስሽው እገሊት ኒቃብ ለባሽ ናት እንዲሉሽ ከሆነ ትልቅ አደጋ ላይ ነሽ። ይህን ርእስ ብዙ ኒቃብ እና ጂልባብ ለባሾች የተዘናጉበት ጉዳይ ነው።

➻ ከላይ ስታያቸው ማሻአላህ ኢማነኛ ናቸው ነገር ግን ከሰው ተደብቀው የሚሰሩት ስራ ግን በጣም የሚያሳዝን ሆኖ ታገኘዋለህ። አላሁል ሙስተዓን! ለዚህም ይመስለኛል አንዳንድ ጂልባብ ለባሾች በሚሰሩት ስራ ብዙ እህቶች ለምን ጂልባብ ወይም ኒቃብ አትለብሱም ሲባሉ ኢማን በልብ ነው የሚሉት እናም እህቶቼ ሆይ! ኒያችሁንም አስተካክሉ ለልብሱም ክብር ስጡት።

➨ ኒቃብ ልበሱ ስትባሉ ኢማን በልብ ነው ወደምትሉ እህቶች ልምጣ ይህ ንግግር በመሰረቱ ችግር ያለበት ንግግር ነው። ምክንያቱም የአህለሱናዎችን ዓቂዳ ይቃረናልና። እንዴት ከተባለ አህሉ ሱናዎች ኢማን በልብ ብቻ ሳይሆን ከስራ ጋርም የተቆራኘ በመሆኑ ነው የሚያምኑት።

➽ ኢማን እና ስራ የተለያዩ ናቸው ኢማን በልብ ብቻ እንጂ ከስራ ጋር ቁርኝት የለውም ብለው የሚያምኑ 'ሙርጂአ' የሚባሉ ጠማማ አንጃዎች አሉ። ስለዚህ ባለማወቅ የነሱን እምነት እያንፀባረቅን ነውና ከዚህ ንግግራችን ልንቆጠብ ይገባናል። እናም እህቶቼ ሆይ! አላህ ያዘዘበት ነገር እስከሆነ ድረስ የአላህን ትእዛዝ ለመፈፀም ስትሉ ኒቃባችሁን ልበሱ። የሚል መልእክት አስተላልፍላችኋለው።

ወላሁ አዕለም!!!
252 viewsAlhamdulillah, 15:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-21 16:04:11 ክፍል አንድ



በጣም ወሳኝ ማስታወሻ ሁሉም እህቶቻችን ማወቅ ያለባቸው እሳት ውስጥ ከመግባታቸው በፊት።
ሃቅን ፈላጊ ለሆናችሁ እህቶቻችን ማስታወሻው ይጠቅማችኋል ብየ ተስፋ አደርጋለሁ። እያወቁ ለሚያጠፉትም አላህ ሰበብ ያድርግላቸው።

የሃራም መንገዱን /መፍትሄውን /እና ምክር

ክፍል አንድ ተከታታይ ፕሮግራም

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።


ወንዶች በሃራም መቆየት ሲፈልጉ ወይም ለዚና ማመቻቸት ሲፈልጉ ወይም ልጅቱን ወደ መጥፎ ነገር ውስጥ ማስገባት ሲፈልጉ በዚህ ያክል ግዜ አገባሻለሁ ጓደኛ እንሁን ይላታል ልጅቱም እውነት መስሏት ወይም እርድና መስሏት እሽ ብላ በሃራም ግኑኝነት በርካታ ግዜን ከሱ ጋር በመገናኘትም ይሁን ስልክ በማውራት በሚዲያ በማውራት ታሳልፋለች። በመጀመሪያ ይሄ በጣም ክልክል የሆነ መንገድ ነው።

    እህቴ በመጀመሪያ እንደዚህ አይነት ነገር በቤተሰብ ነው ማለቅ ያለበት ምክንያቱም እንዳለው ልጁ ከሁለት አመት በኋላ ወይም ከአንድ አመት በኋላ አገባሻለሁ ብሎሽ ሊሆን ይችላል ነገር ግን ይሄ የልጁ ብቻ ሃሳብ ነው ይሄን የሚልሽ ቤተሰቡ ጋር ተማክሮ አይደልም አንቺን ለማታለል እንጂ እናም የልጁ ቤተሰብ ምንም ሚያውቁት ነገር አይኖርም ከዛ በኋላ እሱ በፈለገበት ሰአት ቤተሰብ ሲጠየቁ ላይመቻቸው ይችላል ወይም እነሱ ላይፈልጉ ይችላሉ  ያንቺም ቤተሰብ እንደዛው ላይመቻቸው ይችላል  እናም ቤተሰቦችሽን እንደ ጓደኛ ቀርበሽ ያለውን ነገር አማክረሽ ስሜታቸውን ማወቅ ይኖርብሻል ይሄ የሚፈራበት ወይም የሚያሳፍር ነገር አይደለም እናም ልጁ ምርጫሽ ከሆነ ማድረግ ያለብሽ ልጁ ሽማግሌ ልኮ ቀን አስቆርጡ ከዛ በኋላ እስከምትጋቡ ድረስ ምንም አይነት ግኑኝነት መኖር የለበትም! ወይም አብራችሁ መኖር ካልቻላችሁ ኒካህ አስራችሁ እንደፈለጋችሁ መሆን ትችላላችሁ። ነገር ግን ከኒካህ በፊት በስልክም ሆነ በአካልም በፅሁፍም በማንኛውም መንገድ መገናኘት የለባችሁም።

ሌላው አንዳንድ ሰዎች ቀኑ ስለተቆረጠ ብቻ ማውራት መገናኘት የሚችሉ ይመስላቸዋል ይሄ በጭራሽ አይቻልም! ሁሉም ነገር ከኒካህ በኋላ ብቻ ነው። ብዙዎች በዚህ ፈተና ወድቀዋል አላህን እንፍራ ስሜታችንን አንከተል።
ይሄን ውድ ትዳር በሃራም መንገድ አናነካካው በዚህ በሀራም መንገድ ሂደን ብንጋባም አላህ ለትዳራችን ጥፍጥናን አይሰጠንም። በዚህ ሰአት ለብዙዎች የትዳር ፍች ምክንያት የሆነው ይሄው ከትዳር በፊት በሚደረገው የሆነ ግኑኝነት ነው። ራሳችንን አምጉዳ። ለአላህ ብለን ከዚህ የሸይጧን መንገድ እንራቅ።

→  እንዴት ልጁን ካላወራሁት አውቀዋለሁ የማላውቀውን ወንድ ለምን አገባሁ ልትይኝ ትችያለሽ  አንደኛ ልጁን በስልክ ስላወራሽው ወይም በፁሁፍም ስላወራሽው እሱን በጭራሽ ልታውቂው አትችይም በጭራሽ! በስልክ የምታገኝውና በአካልም አግንተሽ የምታይው ከማንነቱ ፍፁም የራቀ ነው! ምክንያቱም አንችን ለማሳመንና እሽ እንድትይውና በሱ እንድትሳቢ ለማድረግ ብዙ ያልሆነውን ነገር ያደርጋል ብዙ እህቶች በዚህ መንገድ እየተሸወዱ ነው በሚዲያ የሚያገኙትን ወንድ በማውራት በፁሁፍ ፍቅር በሚል ሰበብ በመግባት ምንም ሳታጣራ ታገባዋለች ካገባችውም በኋላ ከጠበቀችው ውጭ ሆኖ ታገኘዋለች ቶሎ ወደ  ፍችም ያመራሉ። ንቂ እህቴ!
በሚዲያ መገናኘት ያለው እውነታ ይሄ ነው! አንዷ 6ወር በሃራም አሳልፋ አግብታው የሆነችውን ብነግራችሁ በጣም ታዝናላችሁ ዚና ላይ እንኳ አልወደቁም ነበር ነገር ግን ካገባችው በኋላ ከፊቷ ላይ ነው ሚጀናጀነው ከሴት ጋር ነው ሚውለው ብዙ ነገር ነግራኛለች እናም ይሄ ነው እውነታው! አላህን አስከፍቶ መቼም ጥሩ ነገር አይታሰብም እናም ሚዲያን ለዲንናችን እንጂ ትዳር መፈለጊያ አንጠቀመው! እንደ ቀልድም እንደ መዝናኛም ብለን ከማውራት እንቆጠብ መጨረሻው ፀፀት ነውና።

ስለዚህ ውድ እህቴ ማድረግ ያለብሽ ስለ ልጁ ቤተሰብ እንዲያጣራ አድርጊ አንቺም በምትችይው በሩቅ ለማጣራት ሞክሪ ስታጣሪ ጓኞቹን አይደለም መጠየቅ ያለብሽ የአካባቢውን ሰው በልጁ አቅራቢያ ያሉትን ነው ምክንያቱም ጓደኞቹን ከጠየቅሽ ስለ ልጁ መጥፎ ነገር ላይነግሩሽ ይችላሉ።

→ ሌላው ጥንቃቄ ማድረግ ያለብን ነገር አገባሻለው ስላለሽ አንቺ ሂደሽ ሊያይሽ አይፈቀድልሽም እውነተኛ ሊያገባሽና ሊያይሽ ከፈለገ ቤተሰቦችሽ ጋር ሂዶ በቤተሰቦችሽ ፊት ይይሽ ወየም በመንገድ ስታልፊ አንቺ ሳታስቢበት ቢያይሽ ችግር የለውም። እንጂ ሆቴል ወይም ካፌ ተቀጣጥሮ መገናኘት አይፈቀድልሽም ፎቶም መላክ አይፈቀድልሽም አላህን ፍሪ እህቴ ትዳርሽን ፈተና ላይ አትጣይው ጌታሽ ረሺ አይደለም የመጥፎ የሰራችንንም የጥሩ ስታችንንም ምንዳ ጠብቆ ይሰጠናል።


(አላህ የላቀና ይበልጥ አዋቂ ነው)


ክ ፍ ል ሁ ለ ት ይ ቀ ጥ ላ ል


በዚህ መንገድ ሌላ ጥያቄ ካላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ እንዲሁም ይሄንንም መንገድ አስተላልፈው ትምህር ይሆናል የምትሉት ካላችሁ በውስጥ ፃፉልኝ። ከሃራም መንገድ ለመውጣት ከአላህ በታች እገዛ ካስፈለጋችሁ ማማከር ትችላላችሁ።


@Jezakellah
@Jezakellah


ሟር ሟር ሟር ሟር ሟር ሟር

ለሴት ጓደኞቻችሁ በምትችሉት ሼር አድርጉት።
አንዲት ሴት ከ15 ላላነሱ እህቶች ሼር ታድርግ እንዲሁም በግሩፖች ሼር አድርጉት። ጀዛከላሁ ኸይረን


ያለፉትንና የቀሩትን አስተማሪ ፁሁፎች ቻናሉን ተቀላቅላችሁ ተከታተሉን
በዝሙት አንዘምን ๓

Join us on
telegram channel
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
350 views🅂🅈🄷, 13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 17:49:03 ዘመንኩኝ አትበይ .....
ዘመንኩኝ አትበይ ------???

ዘመንኩኝ አትበይ ወደ ኃላ ቀርተሽ፤
የተፈጠርሽበት አላማን እረስተሽ ፤

ዘመንኩኝ አትበይ የጨስኩኝ አራዳ፤
ድርጊትሽ መስካሪ ከሁሉ የሚያስረዳ፤
ዘመንኩኝ ባትይስ ከቶ ማን ይሰማሽ፤
በአደባባይ ሲታይ ደስ የማይለው ስራሽ፤

ማንኛው' ማንነው ማንነው አትበይኝ እህቴ፤
ለማንም አይደለም ለአንች ነው ስስቴ፤

እስኪ ተመልከችው ያረግሽውን ሂጃብ፤
ኧረ !ሂጃብ አልኩት እንዴ? የደረብሽው እስከርብ፤

እጅጉን ይገርማል የእህታችን ጉዳይ ፤
ፀጉሯ ተገላልጦ ሲታይ በአደባባይ፤
ሂጃብ ያልኳት ብጣሽ ተንጠልጥላ ከላይ፤

ደግሞ የሚገርመው በጣም የሚደንቀው፤
በአርቲፊሻል ዊግ ፀጉር አስመስላው፤
እፍረት የላት ጭራሽ እንደው ጉድ እኮ ነው፤

ሀቂቃው ይገርማል ምን ነክቶሽ ነው እህት፤
አለቃው ጅብራኤል መልዕክቱ ሲያወርዱት፤

ይህማ አይደለም መዘመን መሠልጠን፤
የነዛ መንገድ ነው የምዕራቦች ፋሽን፤

ኢስላም የሚያዝሽን የጥዋቱ የጥንቱ፤
እሡን በደንብ ያዥው ይጠቅምሻል እቱ፤
አንችኛዋ ደግሞ ጥግ ላይ ያለሽው፤
ለጅልባብሽ ጌጥም ሂጃብ የደረብሽው፤

ኧረ ለምን ሲባል ጅልባቡ ይደምቃል፤
ምን ነካሽ እህቴ በደመቀ ከለር ይሸበራረቃል፤

አንች የለበሽው የአኢሻ ጅልባብ፤
እንኳን ሊሽሞነሞን ከላዪ ሊደረብ፤
ቁርአን እንዳለሽ እንደታዘሽው፤
ሌላውን ተይና በላይሽ ልቀቂው፤

ጅልባብ ምን እንደሆነ ጠንቅቀሽ ተረጅ፤
ወንፊት ልብስ ለብሰሽ የትም አትሂጅ፤

የጌታሽ ፍራቻ በውስጥሽ ላይ ኖሮ፤
በሰይጣን ሽወዳ እንዳትይ እሮሮ፤

ከመጥፎ ተግባሮች ከሁሉም እርቀሽ፤
በቁርአን በሀዲስ ልብሽን አንፀሽ፤

ውስጠ ኻቲማሽን እንዲያምር ከፈለግሽ፤
ዘመን ያመጣውን ወደ ኃላ ትተሽ፤
መኖር ያዋጣሻል ትዕዛዙን ተግብረሽ፤
በኹሹዕ በኢማን ፈጣሪሽን ታዘሽ፤

ከቁርዓን ከሀዲስ ቀደም ቀደም አትበይ፤
ቁጭ ብለሽ ተማሪ ዘመንኩኝ አትበይ፤

ኡሙ አብደላህ

t.me/umumahi1
263 views🅂🅈🄷, 14:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ