Get Mystery Box with random crypto!

ለእህቶች መልዕክት ⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼ الحمدلله وحده، والصلاة والسلام ع | 🌹Islamic_deawa 🌹

ለእህቶች መልዕክት
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
الحمدلله وحده، والصلاة والسلام على من لا نبي بعده؛ أمابعد:


ምክር ለ ኒቃብ እና ጂልባብ
ለባሾች እንዲሁም ኒቃብ
ልበሱ ስትባሉ ኢማን በልብ
ነው ለምትሉ እህቶች

➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩

➜ ኒቃብ እና ጅልባብ በሚለብሱ እህቶች ልጀምር
➼ በመጀመርያ ይህንን የተከበረ ልብስ እንድትለብሱ ልባቹሁን ክፍት ያደረገላችሁን አላህ ልታመሰግኑት ይገባል። ይህን የተከበረ ልብስ ስትለብሱ ፅናት ሊኖራቹህ ይገባል። ይህን ልብስ በመልበሳቹህ ብቻ የተለያዩ ሰዎች ከእውነታው የራቀ ትችት ሊሰነዝሩባችሁ ይችላሉ ምናልባት 'ፋራ' ሊሏቹህ ይችላሉ ራሳቸውን 'አራዳ' አድርገው በማሰብ ' ገጠሬ ' ይሏችኋል 'ከተሜ ' የሆኑ መስሏቸው የመሳሰሉ የተለያዩ ትችቶችን ይሰነዝራሉ ይሄኔ ግን እናንተ እውነታው ባገልባጩ መሆኑን ተረድታችሁ በፅናት ወደፊት ልትጓዙ ይገባል። ፋራዎች ተባልን ብላቹህ የለበሳችሁትን ኒቃብ አሊያም ጂልባብ እንዳታወልቁ። አይደለም ፋራ ሌላም ሊሏቹህ ይችላሉና!!!

➭ ሁሌም ሐቅ ላይ ያለ ሰው መተቸቱ የማይቀር ነው ነገር ግን ሐቅ ላይ እስከሆነ ድረስ ትችቱ አይጎዳውም።

➪ ሰለፎች ሐቅ ላይ የነበራቸውን ፅናት ተመልከቱ አይደለም ስድብ ስንት ድብደባ እና ግርፋት ደርሶባቸው ከአቋማቸው ዘንበል አላሉም ። ስለዚህ አርአያዎቻችሁን አላህ ያወደሳቸውን ትውልዶች በማድረግ ከአቋማችሁ በትንሽ ድግሪ እንኳን እንዳትዘነበሉ።

➺ ሶስተኛው እና ይበልጥ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ነጥብ ደሞ የኢኽላስ ጉዳይ ነው። ማንኛውንም ኢኽላስ የሌለውን ስራ አላህ እንደማይቀበለው ተናግሯል። ስለዚህ ይህንን በመረዳት ኒቃቡን አሊያም ጂልባቡን የለበሳችሁት የአላህን ፊት ፈልጋችሁበት እንጂ የሰውን ፊት ፈልጋችሁበት ሊሆን አይገባም።

ኒቃብ የለበስሽው እገሊት ኒቃብ ለባሽ ናት እንዲሉሽ ከሆነ ትልቅ አደጋ ላይ ነሽ። ይህን ርእስ ብዙ ኒቃብ እና ጂልባብ ለባሾች የተዘናጉበት ጉዳይ ነው።

➻ ከላይ ስታያቸው ማሻአላህ ኢማነኛ ናቸው ነገር ግን ከሰው ተደብቀው የሚሰሩት ስራ ግን በጣም የሚያሳዝን ሆኖ ታገኘዋለህ። አላሁል ሙስተዓን! ለዚህም ይመስለኛል አንዳንድ ጂልባብ ለባሾች በሚሰሩት ስራ ብዙ እህቶች ለምን ጂልባብ ወይም ኒቃብ አትለብሱም ሲባሉ ኢማን በልብ ነው የሚሉት እናም እህቶቼ ሆይ! ኒያችሁንም አስተካክሉ ለልብሱም ክብር ስጡት።

ኒቃብ ልበሱ ስትባሉ ኢማን በልብ ነው ወደምትሉ እህቶች ልምጣ ይህ ንግግር በመሰረቱ ችግር ያለበት ንግግር ነው። ምክንያቱም የአህለሱናዎችን ዓቂዳ ይቃረናልና። እንዴት ከተባለ አህሉ ሱናዎች ኢማን በልብ ብቻ ሳይሆን ከስራ ጋርም የተቆራኘ በመሆኑ ነው የሚያምኑት።

➽ ኢማን እና ስራ የተለያዩ ናቸው ኢማን በልብ ብቻ እንጂ ከስራ ጋር ቁርኝት የለውም ብለው የሚያምኑ 'ሙርጂአ' የሚባሉ ጠማማ አንጃዎች አሉ። ስለዚህ ባለማወቅ የነሱን እምነት እያንፀባረቅን ነውና ከዚህ ንግግራችን ልንቆጠብ ይገባናል። እናም እህቶቼ ሆይ! አላህ ያዘዘበት ነገር እስከሆነ ድረስ የአላህን ትእዛዝ ለመፈፀም ስትሉ ኒቃባችሁን ልበሱ። የሚል መልእክት አስተላልፍላችኋለው።

ወላሁ አዕለም!!!