Get Mystery Box with random crypto!

#እህቴ ልንገርሽ አድምጪኝ ሀጂ ነብይ ወንድ በተቀላቀለበት ግሩፕ ተጨምረሽ መናገር ያለብሽን ተናገ | 🌹Islamic_deawa 🌹

#እህቴ ልንገርሽ አድምጪኝ

ሀጂ ነብይ ወንድ በተቀላቀለበት ግሩፕ ተጨምረሽ መናገር ያለብሽን ተናገሪ በስተቀር
#ክክክክክክ
@kkkkkkkk
@hahaha አትበይ::

እስቲ ልጠይቅሽ ምላሽ እፈልጋለዉ ካንቺ በአካል ቢሆን ኢሄ የግሩፕ ስብስብ !? በዚህ መልኩ ተጨምሮ እንኳን ለመንካካት መደባለቅም አይቻል አደል እንዴ!?

ማሸአላህ አላህ ይጨምርልሽ ተሳትፎሽ ዒልምሽ ነገር ግን አንዳንድ እህቶች አሉ እንደ ወፍጮ
#ክክክክክክክክከክ የሚሉ::

አድቢ እህቴ አላህ ይመለከትሻል ከቀኝና ከግራ ያሉ መላይካዎች ንግግርሽን ይመዘግባሉ::

በል አንዳንዴ ዝም ብሎ የወሬ ግሩፕ ይከፈትና ስገቡ ሀሜት አሉባልታ ወሬ ሴቷ ከወንዱ ጋ ዉዴ ምኔ እያለች ስትለፈልፍ ትመለከታላቹ:: ፈታ በሉ ይላሉ የግሩፑ አሚሮች ስሙ
#መሀመድ #አህመድ ስሟ #ሀናን #ኸድጃ #ጀሚላ የሆነ ሁላ #ኢናሊላሂ_ወኢና_ኢለይሂ_ራጁኡን

በሀራም ነገር ነዉ ፈታ!? ወንድን ከሴት አደባልቀህ ከኢስላማዊ ንግግር ማይጠበቅ ነገር እንዲያወሩ እየፈቀድክ ነዉ ፈታ!?

,እዛ ግሩፕ ለሊት 4:00 6:00 ብገቡ ወሬ ነዉ ሴቷ ሀያዕዋን ትታ ወንዱም እንደዛዉ::
#እህቴ_አላህ_እኮ_ይመለከትሻል_ያይሻል::
በዚ ሰአት አንድ አማኝ ወደ ጌታዉ ሚቃረብበት ሰአት ነዉ::

#እህቴ ሆይ አድቢ ለወንድሞችሽ የፊትና በር አትክፈቺ:: አላህ ሱብሀነ ወተአላህ #ዚናን አትስሩ ሳይሆን #አትቅረቡ ነዉ ያለዉ::

ወደ
#ዚና መዳረሻ መንገዶችን አትቅረቡ:: ቤትሽ ቁጭ ብለሽ በጅሽ በምፅፊያቸዉ ፅሁፎች ወንድሞችሽን ለፊትና እየዳረግሽ ነዉ::

ነገ አላህ ፊት ስቀርቢ የገዛ እጅሽ ጠላት ሆኖ ይመሰክርብሻል የገዛ አይንሽ ይመሰክርብሻል::

ነገ አላህ ፊት ስቀርቢ በጊዜሽ በገንዘብሽ (ዳታ ሚበላብሽ) በያንዳንዱ ነገርሽ ይጠይቅሻል::

ታድያ
#እህቴ ምንድን ነዉ አላማሽ ዛሬ ለጋ ታዳጊ ወጣት ወደ አኸራ ሄደ ኤኬሌ ሞተ ሲባል አልሰማሽም!? አንቺ መሞቻሽን ታዉቂዋለሽ!? ዛሬ!? ነገ!? መች!? አላህ ብቻ ነዉ ሚያቀዉ ድንገት ሞት ይመጣል ሳያስፈቅድሽ ሊወስድሽ ላትመለሺ ወደዚች የዱንያ ሂወት::

ተዉበት አድርጊ ለወንድሞችሽ መበላሸት ወንጀል ሰበብ አትሁኚ::

በየ ግሩፑ
@kkkkkkkkkkkk @Hahahaha አትበይ:: ሰዉ ባያይሽ ረቡና ከላይ እያየሽ ነዉ አንሶላ ብትለብሽሚ ከረቡና አይን አታመልጪም::

#ቁጥብ_ሁኚ_ዉድ_ትሆኛለሽ::

ሀያእ አይናፋርነት መልካም ነገርን እንጂ ሌላን አያመጣም::

bint nesro

https://t.me/+KoYMWLdIV7AzNjk0