Get Mystery Box with random crypto!

የኖህ መርከብ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ hamreel — የኖህ መርከብ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ hamreel — የኖህ መርከብ ዘኦርቶዶክስ ተዋህዶ
የሰርጥ አድራሻ: @hamreel
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.69K
የሰርጥ መግለጫ

የ ኢ/ኦ/ተዋህዶ/ቤተክርስቲያን አስተምህሮ የጠበቁ የ አባቶች ምክር;ግጥም;ተከታታይ አምዶች;ልሳነ ግእዝ;ጥያቄናመልሶች የምናገኝበ ስለሆነ ቻናሉን ይቀላቀሉ። for any opinion @Abeln ይላኩ
"ይህች ቤተክርስቲያን
ክርስቶስን ከቶ አታውቀውም" በሉ
ግድ የለም ለቃሉ !
ግን ድምጽ ቀንሱ !
የጌታን መከራ ሕማሙን አስባ
ስግድት ላይ ናትና ልጆቿን ሰብስባ
ግድ የለም አንቋሿት
ግን አትረብሿት !!

Ratings & Reviews

5.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-21 18:21:41 #ሥርዓተ_ማኅሌት_ዘነሐሴ_ኪዳነ_ምሕረት

፩/ ነግሥ ( ለኲልያቲክሙ )

ሰላም ለኵልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወፀ ለሣህል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኀኒት መስቀል፡፡

ዚቅ፦

ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ ፨ እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፨ ከመ ትኵኒ ተንከተመ ለዉሉደ ሰብእ፨ ለሕይወት ዘለዓለም ፨ ለኪ ይደሉ ከመ ትኵኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ ፨ ኦ መድኀኒተ ኵሉ ዓለም ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

፪/ ነግሥ ( እምጌቴሴማኒ ፈለሰት )

እምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ መካን፤
ውስተ ቤተ መቅደስ ረባቢ ዘመሳክዊሁ ብርሃን፤
አንቀጸ አድኅኖ ማርያም ጽላተ ኪዳን፤
ኵሉ ይብልዋ በአኅብሮ ዘበዕብራይስጢ ልሳን፤
ዕፀ ጳጦስ ይእቲ እንተ በአማን ቅድስተ ቅዱሳን፤
እመቅድሀ ከርሣ ተቀድሐ አስራባተ ወይን፤
ወበውስቴታ ተሠርዓ ቊርባን፡፡

ዚቅ፦

ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን መዝገቡ ለቃል ፨ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን አንቀጸ ብርሃን፨ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን ጽጌ ደንጐላት ፨ ሐረገ ወይን ዘእምነገደ ይሁዳ፨ እንተ ሠረፀት ለሕይወት፡፡

፫/ ለፍልሰተ ሥጋኪ ( መልክአ ኪዳነ ምሕረት )

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ኀበ ሕንጻ ሕይወት ተሐደሰ፤
እምቅድመ ዝኒ ኀቤሁ ሥጋ ወልድኪ ፈለሰ፤
ቤዛዊተ ዓለም ማርያም አስተበቊዓኪ አንሰ፤
ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚአየ ነፍሰ፤
እስመ በሥራይኪ ለቊስልየ ቀባዕክኒ ፈውሰ፡፡

ዚቅ፦

ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ፨ ወማኅደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሃሊ፨
ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ ፨ በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ፨ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ።

ወረብ፦

ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤
በመሰንቆሁ እንዘ የሐሊ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ
ወዓሊ።

፬/ ለዝክረ ስምኪ ( መልክአ ማርያም )

ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤
እምነ ከልበኒ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ
ማርያም ድንግል ለባሲተ ዐቢይ ትእዛዝ፤
ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤
ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ፡፡

ዚቅ፦

ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ፨ ወልድኪ ይጼውዓኪ፨
ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር፡፡

ወረብ፦

ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ ማኅደረ መለኮት፤

ወልድኪ ወልድኪ ይጼውዓኪ ውስተ ሕይወት ወምንግሥተ ክብር።

፭/ ለእስትንፋስኪ ( መልክአ ማርያም )

ሰላም እስትንፋስኪ ዘመዐዛሁ ሕይወት፤
ከመ መዐዛ ዕፅ ኅሩይ ዘውስተ ገነት፤
ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት፥
ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት፤
በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት፡፡

ዚቅ፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ፨ መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፨ ወኵሉ ነገራ በሰላም፡፡

ወረብ፦

ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ፤
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል መዓዛ አፉሃ ታንሶሱ፡፡

፮/ ለፍልሰተ ሥጋኪ ( መልክአ ፍልሰታ )

ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ዘኢይቀብል ሞገሱ፤
ወዘኢይነጽፍ ባሕርየ ተውዳሱ፤
ማርያም ታዕካ ለእግዚአብሔር ጽርሐ መቅደሱ፤
ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ፤
ማርያምሰ እንተ በምድር ታንሶሱ ፡፡

ዚቅ፦

ማርያም ጽርሕ ንጽሕት ማኅደረ መለኮት ፨እኅቶሙ ለመላእክት ሰመያ ሰማያዊት ፨ እንተ በምድር ታንሶሱ፡፡

ወረብ፦

ማርያም ጽርሕ ንጽሕት ፤
ማኅደረ መለኮት ጽርሕ ንጽሕት።

+++++ አንገርጋሪ +++++

ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ፤
ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ፥
ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ ፡፡

ወረብ ዘአመላለስ፦

ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ፤

ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ወይቤላ ሠዓለም፡፡

+++++ ዘሰንበት +++++

በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኁብርት፤ እኅትየ መርዓት አዳም አጥባትኪ እምወይን፤ መዓዛ ዕፍረትኪ እምኩሉ አፈው፤ እትፌሳህ ወእትኃሰይ ብኪ ነፍቅር አጥባተኪ እምወይን፤ ርቱዕ አፍቅሮትኪ ኩለንታኪ ሰናይት አንተ እምንሴየ፤ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ ፃዒ እምሊባኖስ እኅትየ መርዓት፡፡

መልካም በዓል
143 viewsአቤል ታደሰ, 15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-21 13:53:31 "መንፈሳዊ ጥበብን የምትወድ ነፍስ ዘወትር እግዚአብሔርን ታመሰግናለች፡፡ ሰው ሆይ! ሰዎች ክፉ ነገር ሲያደርሱብህ እግዚአብሔርን አመስግን፤ ያን ጊዜም ክፉው መልካም ይኾንልሃል፡፡

"እንዴት?" ብለህ የጠየቅኸኝ እንደኾነም፦ "በደል የሚፈፅመው ክፉ ነገር የሚቀበለው ሳይኾን ክፉ ነገር የሚያደርሰው ሰው ነውና" ብዬ በእውነት ያለ ሐሰት እመልስልሃለሁ፡፡

ስለዚህ ዘወትር እግዚአብሔርን አመስግን፡፡ ብትታመምም እግዚአብሔርን አመስግን፤ ሀብት ንብረት ብታጣም አመስግን፤ በሐሰት ቢከሱህም አመስግን፡፡ እንደ ነገርኩህ ተጎጂዎቹ ክፉ ተቀባዮች ሳይኾኑ ክፉ አድራሾች ናቸውና፡፡"
152 viewsአቤል ታደሰ, 10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 07:58:44 ‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስምህ ደስ ይላቸዋል›› (መዝ. ፹፰፥፲፪)

በትንቢት ‹‹ታቦርና አርሞንኤም በስም ደስ ይላቸዋል›› ብሎ ነቢዩ ዳዊት እንደተናገረው ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡ (መዝ. ፹፰፥፲፪)

በዚህችም ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ፤ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ፡፡

ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደእርሱ መጡ፡፡ ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው፤ ‹‹አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን? ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ላንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ።››

በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት። ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና ራሱን የሚሠውርበትን ቤት ይሠራለት ዘንድ የተናገረው ነው። ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሳበ ነው። ራሱንና ባልንጀሮቹ ሐዋርያትን እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና።

እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ እነሆ ደመና ጋረዳቸው።

የጌታችን ጌትነቱን የሚገለጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው፤ እርሱንም ስሙት። ሙሴና ኤልያስም ከእርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ተሰሙ። ስለ እርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነብያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።
ምንጭ:መጽሐፈ ስንክሳር
እንኳን አደረሳችሁ!
221 viewsአቤል ታደሰ, 04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 21:20:20 ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት ጭራፍ ለምን ይጮሃል ?

ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል

ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል

ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና

ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና

ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው

ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበርካታ ዓመታት ሲወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል ፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው
270 viewsአቤል ታደሰ, 18:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 14:35:41 ማርያም ማለት ሥጦታና ሀብት (ጸጋ ወሀብት) ማለት ነው። ይህ እንዴት ነው ቢሉ፦

#መጀመሪያ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ለእናት አባትዋ ነው። "ልጆች የአግዚአብሔር ሥጦታዎች ናቸው" ተብሎ ተጽፎአልና።

#ሁለተኛ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ደግሞ ለሰው ልጆች ሁሉ ምልክት ሆና ነው። "ጌታ ራሱ ምልክትን ይሠጣችኋል፣ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል" ተብሎ ተጽፎአልና። (ኢሳ 7፥14)

#ሦስተኛ ወላጆችዋ ለእግዚአብሔር ስእለት አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ መሥጠታቸው ደግሞ ለእግዚአብሔር የተሠጠች ሥጦታ ያደርጋታል።

#አራተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ ከመሥጠቱ በፊት እመቤታችን ራስዋን "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ለእግዚአብሔር ሥጦታ አሳልፋ መሥጠትዋ ነው።

#አምስተኛው ደግሞ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን በመስቀል ላይ ለወዳጁ ለዮሐንስ "እናትህ እነኋት" ብሎ የሠጠ መሆኑ ነው። "በጎ ሥጦታና ፍጹም በረከት ከብርሃናት አባት" ከላይ የሚወርዱ ናቸው። ከእነዚህ የፈጣሪ ሥጦታዎች አንድዋ እመቤታችን ናት።

እመቤታችን ሱባኤያችንን የሐዋርያት ሱባኤ ታድርግልን፣ ካህናትና ምዕመናን እንደ ዕጣን ከእሳት ተጨምረው በሰማዕትነት መዓዛ ያስጀመሩትን ሱባኤ የሰላምና ከበረከታቸው የምንሣተፍበት ያድርግልን። የሀገራችንን ፍጹም ኀዘንዋን፣ የቤተ ክርስቲያንንም ልቅሶዋን በምልጃዋ ትስማልን።

#ዲያቆን_ሄኖክ_ኃይሌ
305 viewsአቤል ታደሰ, 11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 14:09:07 በዚህች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤልን ወደ ከበረና ከፍ ከፍ ወዳለ ጻድቅ ኢያቄም ላከው አምላክን የወለደች የእመቤታችን የደንግል ማርያምን ፅንሰቷንና ልደቷን በእርሷም ለዓለሙ ሁሉ ድኅነትና ተደላ እንደሚሆን ነገረው፡፡

ይህ ጻድቅ ሰው ኢያቄምና የከበረች ሚስቱ ሐና ልጅ ሳይወልዱ ሸመገሉ፤ የከበረች ሐና መካን ሁናለችና ስለዚህም እጅግ ያዝኑ ነበረ፤ የእስኤል ልጆች ልጅ ያልወለደውን ከእግዚአብሔር በረከትን ያጣ ነው እያሉ ያቃልሉት ነበርና፡፡

እነርሱም ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ዘወትር ፈጽሞ ይለምኑ ነበር፡፡ ወንድ ልጅን ወይም ሴት ልጅን ቢወልዱ ለእግዚአብሄር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ስለትን ተሳሉ፡፡

የከበረ ኢያቄምም በተራራ ላይ ሲጸልይና ሲማድ እነሆ በላዩ እንቅልፍ እንቅልፍ ብሎት አሸለበ፡፡ያን ጊዜ ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክ አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ተገለጸለት እንዲህም አለው ሚስትህ ሐና ትፀንሳለች ዓለሙ ሁሉ ደስ የሚሰኝባትን የብዙዎችም ዐይነ ልቡ ናቸው በእርሷም ድኅነት የሚሆንባን ሴት ልጅ ትወልድልሃለች፡፡

በነቃ ጊዜም ወደ ቤቱ ሒዶ ለሚስቱ ለቅድስት ሐና ነገራት ራእይዋን እውነት እንደሆነች አመኑዋት ከዚህም በኋላ ነሐሴ ሰባት በዚህች ቀን የከበረች ቅድስት ሐና ለዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነች በሁለት ድንግል የሆነች የአምላክ እናት እመቤታችንን ማርያምን ፀነሰች።
ምንጭ፦ መጽሐፈ ስንክሳር
290 viewsአቤል ታደሰ, 11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 14:09:03 "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተፀነስኪ አላ በሩካቤ ዘበሕግ እምሐና ወኢያቄም ተወለድኪ!"

"ድንግል ሆይ በኃጢአት ፍትወት የተፀነስሽ አይደለም በሕግ በሆነ ሩካቤ ከሐና ከኢያቄም ተወለድሽ እንጂ!"
ቅዳሴ ማርያም
241 viewsአቤል ታደሰ, 11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-10 07:48:57 የረቡዕ ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ

“እንተ በአማን ንጹሕ ዝናም” የተባለ፣ የነፍሳትን ጥም ያበረደ የሕይወት ዝናም፣ የሕይወት ጠል፣ የሕይወት ውሃ ክርስቶስን ቋጥረሽ (በድንግልና ፀንሰሽ፣ በድንግልና ወልደሽ) የታየሽልን እውነተኛ ደመና አንቺ ነሽ፡፡ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊሥ ዘጋሥጫም፡- “ንዑ እንከ ከመ ናልዕላ ለዛቲ ደመና ብርሃን እንተ ጾረቶ ለማየ ዝናም ንጹሕ" "ንጹሑን የዝናም ውሃ የተሸከመችውን የብርሃን ደመና ኑ ከፍ ከፍ እናድርጋት” ብሎ ጋብዞናል /አርጋኖን ዘሠሉስ ፮፡፪7። ስትወልጂው ማኅተመ ድንግልናሽ አለመለወጡ፤ አካላዊ ቃል ሰው ሲኾን አምላክነቱ ላለመለወጡ፣ ድንግል ወእም (ድንግልም እናትም) ስትባዪ መኖርሽም ልጅሽ አምላክ ወሰብእ (ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው) ሲባል ለመኖሩ ምሳሌ ነውና አብ የልጁ ምልክት አደረገሽ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ቢያድርብሽ፣ ኀይለ ልዑል ወልድም ሥጋሽን ቢለብስ፤ አንድም መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ ግብራት (ማለትም ከሩካቤ፣ ከዘር፣ ድንግልናን ከመለወጥ) ቢከለክልሽ፣ ኀይለ ልዑል ወልድም ከሦስቱ ግብራት ቢከልልሽ ለዘላለሙ የሚኖር አካላዊ ቃልን ወለድሽልን /ሃይ.አበ.፻፲፡፳፱/። እርሱም ሰው ኾኖ ከኃጢአት አንድም ከኃጢአታችን ፍዳ አዳነን።

ደስ ያለህ ባለ ምሥራች ገብርኤል ሆይ! ወደኛ የመጣ የጌታን ልደት ነግረኸናልና ላንተ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ አንድም “ወነዋ ተወልደ ፍስሐ ዘይከውን ለክሙ ወለኩሉ ዓለም" "እነሆ ለሕዝቡ ኹሉ የሚኾን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁ” ብለህ /ሉቃ.፪፡፲/የጌታን ልደት ለኖሎት (ለእረኞች) ነገርኻቸዋልና ለአንተ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ “እግዚአብሔር ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ካንቺ ጋራ አንድ ይሆናልና ደስ ይበልሽ” ብለህ /ሉቃ.፩፡፴/ ለእመቤታችን ነግረኻታልና ለአንተ የተሰጠ ክብር ፍጹም ነው፡፡ እንዲህ ካለ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳነሣን ለምኚልን፡፡
353 viewsአቤል ታደሰ, 04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 06:35:03 #ሐምሌ_5
#ቅዱስ_ጳውሎስና_ቅዱስ_ጴጥሮስ

ሐምሌ አምስት በዚች ቀን የክቡራንና የዐበይት አባቶቻችን ሐዋርያት #የቅዱስ_ጴጥሮስ እና #የቅዱስ_ጳውሎስ የሰማዕትነታቸው መታሰቢያ ነው።

በዚህች ዕለት ስለክርስቶስ የተገፋ፣ ስለክርስቶስ የተወገረ፣ ስለክርስቶስ የተሰደደ፣ ስለክርስቶስ የታሰረ፣ ስለክርስቶስ ከአለም ሃሳብና መሻቷ የተለየ፣ ስለክርስቶስ ራሱን የለየ፣ ስለክርስቶስ ምእመናን ያነፀ፣ ስለክርስቶስ መልካምን መልእክት የፃፈ #ቅዱስ_ጳውሎስ ሰማዕት ሆነ። ነገር ግን በስጋ ሞተ በመንፈስ ግን ህያው ነው፤ የፅድቅን አክሊል ተቀበለ ከክርስቶስ ጋር መኖርን እንደናፈቀ አገኛት፤ ከእልፍ አእላፋት ቅዱሳን ማህበር ተቀላቀለ ከመላእክት ምስጋና ተጋራ በስጋ ህይወቱ ከእውቀት ከፍሎ እንዳወቀ በሰማያዊው ኑሮ በእጅጉ የበለጠ እውቀትን ተቸረ። በማይጠወልግ፣ በማይደርቅ፣ በማይዝል፣ ፍሬያማም በሆነ ክርስቶስ ግንድነት ላይ ቅርንጫፍ ሆኖ ተሰርቷልና በስጋ ኑሮው በድካም ዝለት ጠውልጎ እንደነበረ የሚጠወልግ አይደለም፤ በማስተማር ብዛት ጉሮሮው እንደደረቀ አሁን የሚደርቅ አይደለም፤ በብርቱ ክንድ ላይ በምቾት አለና የሚዝልም አይደለም፤ ክፉወች ሮማውያን ግን ቅዱስ ጳውሎስን ገደልን አሉ። አይሁድም እፎይ ጳውሎስ ሞተ አሉ። ቅዱስ ጳውሎስ ግን የናፈቀው ክርስቶስ ጋር ሊኖር ወደ ዘለዓለማዊው ህይወት ሄደ፤ ራሱን ህያው መስዋእት አድርጎ በክርስቶስ ፊት እንደ ንፁህ መገበሪያ ስንዴ ተፈጨ፤ አይሁድ በጳውሎስ መሞት ድል ያደረጉ ይመስላቸዋል ነገር ግን የፅድቅን አክሊል በራሱ ላይ አድርጎ ከፀሃይ ይልቅ እያበራ በሰማይ ሆኖ ቅዱስ ጳውሎስ አለ በማይደርቅ ግንድ ላይ የተተከለ ቅዱስ ጳውሎስ ፍሬ በሙላት የያዘ የለመለመ ቅርንጫፍ ሆኖ አለ በቅድስና በተዋበ የክርስቶስ አካል መካከል መልካም ብልት ሆኖ አለ፡፡

አይሁድ ግን ቅዱስ ጳውሎስን ገደልን አሉ በሰይፍ አንገቱን ቆርጠው በስጋ ገድለውታልና አላዋቂ አይሁድ ከሮማውያን ጋር አብረው ጳውሎስን ገደልን አሉ፤ እርሱ ግን ከአፈር በተበጀ ስጋ ሞት ቢሞት በእግዚአብሔር እስትንፋስ ስለተሰጠች ነፍስ ህያው ነው፡፡

ዳግመኛም በብርሃኑ ብርሃንን በጨውነቱ መጣፈጥን በመድሃኒቱ መፈወስን የሰጣቸው ተወዳጅ የሐዋርያት አለቃ #ቅዱስ_ጴጥሮስን አይሁድ ቁልቁል ሊሰቅሉት ወደ ሮም አደባባይ ከወዳጁ ከጳውሎስ ጋር አጣደፉት፤ ጴጥሮስ ግን በትምህርቱ ብርሃን ጨለማቸውን ገፍፎላቸው፣ በእምነት መድሃኒት ሙታናቸውን አንስቶላቸው፣ ጎባጣቸውን አንቅቶላቸው አንካሳወቻቸውን አፅንቶላቸው ክፉ ጠላት ዲያብሎስንም አባርሮላቸው ነበር አይሁድ ግን ከወዳጃቸው ጴጥሮስ ይልቅ ጠላቶቻቸውን ሮማውያን ጋር አብረው አንድም ከወዳጃቸው ከክርስቶስ ይልቅ ከጠላታቸው ዲያቢሎስ ጋር አብረው ቅዱስ ጴጥሮስን እንደጌታውና መምህሩ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሊሰቅሉት ወደሮም አደባባይ አፋጠኑት። የማይጠፋውን ፋና ሊያጠፉ የማይደበዝዘውን ብርሃን ሊያደበዝዙ የማይሞት የክርስቶስን ልጅ ሊገድሉ በገሃነም ደጆች የማትናወጥ ክርስትናን ሊያናውጡ አይሁዳውያን የክርስቲያኖች ዋና ያሉትን ቅዱስ ጴጥሮስን በብዙ ስቃይ አንገላቱት፤ ተወዳጅ ሐዋርያ ቅዱስ ጴጥሮስ ግን የስጋ ሞቱ ዕረፍቱ እንደሆነ እጅግ አስቀድሞ አውቆ ነበር የአይሁድ ማሰቃየት ወደ ክርስቶስ የፀጋ ግምጃ ቤት እንደሚያደርሰው አውቆ ነበር የአይሁድ መጨከን ወደ ክርስቶስ አማናዊ ፍቅር እንደሚመራው አውቆ ነበር፤ “ገደልንህ” አሉት። እርሱ ግን “ወደ ዘለዓለማዊ ህይወት ክርስቶስ ገፋችሁኝ” አላቸው። “ክርስቲያኖችን ጨረስን” አሉት እርሱ ግን “የእኛ ሞት የክርስቲያኖች ዘር ነው” አላቸው፤ “አንተ ርጉም” አሉት እርሱ ግን “የክርስቶስ ምህረት በእናንተ ላይ ይሁን” ሲል በፍቅር ፀለየላቸው፡፡

እነሆ አባቶቻችን እነሆ ዋኖቻችን በክፋት በአንዳች እንኳን የሚከሰሱበት ምክንያት አልተገኘም በቀማኝነትም ማንም እነሱን ሊከስ የሚችል የለም ነገር ግን የሚሰድቧቸውን መረቁ ለሚያሳድዷቸው ፀለዩ ለተራቡት ምግብን ለተጠሙት መጠጥን አቀበሉ ድሆችን ተንከባከቡ ድውዮችን ፈወሱ የጨለማን ክፋት በፍቅር ብርሃን አረከሱ የዲያብሎስን ጭካኔ በክርስቶስ ርህራሄ ሰበሩ፡፡ እነሆ አባቶቻችን አስቀድመው ክርስቶስን አይተው ነበርና ክርስቶስን በትምህርቱ በተአምራቱ በሞቱም መሰሉት፡፡

እንኳን ለቅዱስ ጴጥሮስና ለቅዱስ ጳውሎስ አመታዊ መታሰቢያ እለት አደረሰን፡፡ በረከታቸው ይደርብን። አሜን!!
689 viewsአቤል ታደሰ, 03:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 12:43:00 ፀሐይ ብርሃን ካልሰጠች ፀሐይ አትባልም፤ ብርሃን አለመስጠት ተፈጥሮዋ አይደለምና፡፡ እንስሳት ካልተነፈሱ እንስሳት አይባሉም፤ መተንፈስ ተፈጥሮአቸው ነውና፡፡ ዓሣ ከውኃ ከወጣ ሕይወት ያለው ዓሣ መኾኑ ይቀርና ይሞታል፡፡ አንድ ክርስቲያንም እውነተኛ ክርስቲያን የሚባለው፡-

1. #ሲጸልይ ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በወልድ ውሉድ በክርስቶስ ክርስቲያን በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳዊ መባል ነውና፡፡ ልጅ ከኾኑ ደግሞ አባትን ማናገር ክርስቲያናዊ ተፈጥሮ ነውና፡፡

2. #ሲያመሰግን ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት እግዚአብሔር ፈጣሬ ዓለማት ነው ብሎ ማመን ነውና፡፡ ስለዚህ ለአንድ ክርስቲያን የሰማይና የምድር ውበት እየተመለከተ እግዚአብሔርን ማመስገኑ ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነው፡፡

3.#ሲመጸውት ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት ሀብት ኹሉ ከእግዚአብሔር እንደ ኾነ መመስከር ነውና፡፡ ስለዚህ ራስን እንደ መልእክተኛ አድርጎ በመቁጠር ያለውን ለሌላው ማካፈል ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

4. #ቅዱሳት #መጻሕፍትን #ሲያነብ ነው፡፡ ክርስቲያን ማለት በመንፈስ ቅዱስ ሀብት ደስ የሚሰኝ ነውና፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ መንፈስ ቅዱስ በቅዱሳት መጻሕፍት በኩል ሲናገር መስማት ለአንድ ክርስቲያን ክርስቲያናዊ ተፈጥሮው ነውና፡፡

እግዚአብሔር የተግባር ሰዎች ያድርገን!!
523 viewsአቤል ታደሰ, 09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ