Get Mystery Box with random crypto!

ከአላህ ሱብሀነሁ ወተአላ ዉጭ በሆነ ነገር የተሞላ ልብ ሁሉ ባዶ ነው !!! { وَأَصْبَح | ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

ከአላህ ሱብሀነሁ ወተአላ ዉጭ በሆነ ነገር የተሞላ ልብ ሁሉ ባዶ ነው !!!

{ وَأَصْبَحَ فُؤَادُ أُمِّ مُوسَىٰ فَٰرِغًا }


«የሙሳም እናት ልብ ባዶ ሆነ »

【አል ቀሰስ 10】

የሙሳ እናት ሙሳን ከማስታወስና ስለእሱ ከማሰብ ውጭ ሌላ ልቧን የሞላው ነገር አልነበረም ።

{إِن كَادَتْ لَتُبْدِى بِهِۦ لَوْلَآ أَن رَّبَطْنَا عَلَىٰ قَلْبِهَا لِتَكُونَ مِنَ ٱلْمُؤْمِنِينَ}

« ከምእምናን ትሆን ዘንድ በልቧ ላይ ባላጠነከርን ኖሮ ልትገልጸው ቀርባ ነበር፡፡»

አላህ በልቧ ላይ ያለውን ኢማን ባያፀናላት ኖሮና ባትጠናከር … ሙሳ ልጇ እንደሆነ በተናገረች ነበር … ይህም የማንኛውም ባዶ ልብ ሁኔታ ነው ። ባጋጠመመው ችግርና መከራ በፍርሀት ሊበር ይደርሳል ።

በአላህ እንደማመንና እንደመተማመን ሊያፀናውና ሊያጠነክረው የሚችል ነገር የለም።

ለእነዚያ ለተጨነቁና ግራ ለተጋቡ ልቦች ከዚህ በአንደበት ውስጥ ከሚሰርፀው ኢማን በስተቀር መረጋጋትና ስክነትን የሚያሰፍን ነገር የለም ።


ይ ላ ሉን share
┏━ ━━━━ ━┓
@Halal_Fonqaa
┗━ ━━━━ ━┛