Get Mystery Box with random crypto!

  ለውድ እህቴ ውድ ስጦታ   የ ሀ ራ ም ፍ ቅ ር     ( ቦይ-ፍ | ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

 
ለውድ እህቴ ውድ ስጦታ
 
የ ሀ ራ ም ፍ ቅ ር
    ( ቦይ-ፍሬንድ  ገርል-ፍሬንድ )
 
ወላሂ መነበብ ያለበት በጣም አስተማሪ ፁሁፍ ነው። አልሃምዱሊላህ ለብዙዎች የመመለስ ሰበብ ሆኗል። ብዙዎችም ፁሁፍን አምበብው ጥንቃቄ እያደረጉ ነው።

ውድ እህቴ ለአላህ ብለሽ ሶስቱንም ክፍል አምብቢው።

→ ክፍል አንድ

بــســم الــلــه الــرحــمــن الــرحــيمــ
الحمد الله رب العالمين

 ውድ እህቴ የሃራም ፍቅር ግኑኝነትን በጣም በሩቁ ልትጠነቀቂው ይገባል ምክንያቱም በዚህ ሰዓት ብዙ እህቶችሽ እየተፈተኑበት የሚገኙው ከባድና አስቸጋሪ ፊትና ነው አሁን ባለንበት ዘመን የተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ተበራክተዋል ለምሳሌ ዋሳፕ ፌስቡክ ኢሞ ቴሌግራም እና መሰል ሚዲያ አፖች አሉ በነዚህ ቴክኖሎጂዎች ከሚመጡ ፊትና እራስሽን ማራቅ ይኖርብሻል። ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ብዙ እህቶች በነዚህ ሶሻል ሚዲያዎችና ስልክ በማውራት ከተለያዩ ወጣቶች ጋር የሃራም ፍቅር ግኑኝነት ፈጥረዋል ለምን እህቶች ተብለው ሲጠየቁ ምን ችግር አለው ለቀልድ ለመዝናናት እና ጊዜ ለማሳለፍ ብቻ ነው ብለው ይመልሳሉ።
ውድ እህቴ ይሄንንስ የሃራም የቀልድ ግኑኝነት እንድትቀርቢው ማን ነው የፈቀደልሽ  ውድ እህቴ ይሄ ሃራም ነው። አላህን ፍሪ! እንዲህ አይነቱ የሃራም ፍቅር ግኑኝነት በኢስላም በጥብቅ የተከለከለ ነው እስከዛሬም ወደፊትም በሸሪዓው አልተፈቀደም። እንደውም ከከባባድ ወንጀሎች ሊመደብ ይችላል ምክኛቱም እህቴ ያን ሚስኪን ወጣት በለስላሳው ድምፅሽና አንደበትሽ ተስፋን ሰጠሽ ፍተና ላይ ትጥይዋለሽ  በአላህ ይሁንብኝ ስንትና ስንት ወጣቶች ናቸው በሃራም ቆሻሻ ተግባራቶች ላይ የወደቁት ምክንያቱን ሲናገሩ እንደምንሰማው በእከሌ ምክንያት ተፈትኜ እከሌ ፊት ባትሰጠኝ እከሌ ባታማልለኝ ኖሮ እንዲህ አልሆንን ነበር ይላል። እና መሰል የፊትና ሰበቦች እያመጣሽባቸው ስለሆነ ነው። እና በማንኛውም ምንገድ ለወንድሞችሽ ፈተና ከመሆን ልትጠነቀቂ ይገባል።
 
ወድ እህቴ ከየትኛውም አይነት ወጣት ጋር የሶሻል ሚዲያ የሃራም ፍቅር ግኑኝነት ሚባለውን በጣም በሩቁ ልትጠነቀቂው ይገባል በጣም ተጠንቀቂ  ፍቅር አይደለም ብለሽ ልታወሪም አይገባም በፁሁፍ የምታወሪውን በስልክም ምታወሪውን ልታቆሚ ይገባል። ትዳር ፈልገሽም ከሆነ በዚህ በሃራም ምንገድ መሆን የለበትም ብዙዎች ትግስት እያጡ ወደ ሃራም ፍቅር ይገባሉ ግን መፍትሄው ይሄ አይደልም ማወቅ ያለብሽ ነገር በሃራም ፍቅር የጀመርሽው ግኑኝነት መጨረሻ ላይ ልታገቢው ብትችይ እንኳ ለትዳርሽ ጥፍጥናን አታገኝም ምክንያቱም በሁለት ጥንዶች መሃል መዋደድንና መተዛዘንን የሚያደርገው አንድ አላህ ብቻ ነው። እና አላህን አስከፍትሽ በሃራም ባመጣሽው ትዳር እንዴት ደስተኛ ህይወት ልትኖሪ ትችያለሽ።ይሄ በጭራሽ አይሆንም ካገባሽው በኋላ ባጭር ግዜ ውስጥ በትናንሽ ነገር ትዳራችሁን ይበጠብጠዋል እና ቆም ብለን አርቀን በማሰብ ከዚህ የሃራም ግኑኝነት እንራቅ አላህን በማስቆጣታችን ጉዳቱ ለኛ እንጂ ለአላህ አይደለም።
 
በዚህ የሃራም ፍቅር ውስጥ የተደበቀውን እውነታ እነግርሻለሁ በደምብ አድምጪኝ
 
→ የመጀመሪያው እውነታ፦  አንችን ሊወድሽ ይችላል ግን ካንችም ውጭ ሌሎችን ብዙ ሴቶችንም ይወዳል ያወራል ይህ ማለት አንችም ላይ ይጫወታል ካንችም ውጭ ብዙ ሴቶች ጋር ግኑኝነትን ይፈጥራል። ይህ የመጀመሪያው እውነታ ነው። ሲጀመር ለአላህ ያልታመነ እንዴት ላንቺ ሊታመን ይችላል።? ይሄ የመጀመሪያው የተረጋገጠ እውነታ ነው ንቂ እህቴ! ይሄን በተለያየ መንገድ ማረጋገጥ ትችያለሽ
 
 → ሁለተኛው እውነታ ደግሞ ምንም ጋብቻ ሚባለውን ነገር አያስበውም አላማውም ግቡም የለውም ይህ ማለት ወደ ጋብቻ አይገፋፋሽም ሀሳቡም ግቡም የለውም እንደውም ካንች ጀርባ ሁኖ ስላንች ብዙ ያወራል ከኔ ውጭ ሌላ ውንድ ጋር እያወራች ከሃዲ ናትኮ እያለ ስምሽን ያጠፈዋል ግን በተዘዋዋሪ እሱም አንችን ይከዳሻል።
 
→ ሦስተኛው እውነታ አንችን የሱ ባሪያ ወይም ምርኮኛ የሚያደርግብሽ በሁለት ከባባድ ምክንያቶች ነው።
 
 ↠ አንድኛው ያንች የተገላለጡ የራቁት ፎቶዎች ካሉት ነው። ይህ ወንድ ልጅ ይሄ ፎቶሽ ካለው አንቺን የሚያስፈራራብሽ የመጀመሪያው ከባድ ሰበብ ይሄ ነው። እሱ ያሰበው ሃራም ነገር የማትሰሪ ከሆነ ያን ፎቶ ለሌሎች አሰራጨዋለሁ ብሎ ያስፈራራሻል ይሄኔ አንች አቋምሽን እያለወጥሽ ትመጫለሽ ምክኛቱም ሌላ ነገር ለማድረግ አትደፍሪም እሱ የያዘብሽ ሚስጥራዊ ፎቶ ስላለ ትፈሪያለሽ ያኔ ያዘዘሽን ቆሻሻ ነገር ሁሉ ትሰሪያለሽ። እና እባካችሁ ተጠንቀቁ እህቶች ፎቶ መላላክ ይቅርባችሁ እባካችሁ ለማንም ፎቶ አትላኩ ሌላው ይቅርና የምትቀርቢያትና የምታምኛት ጓደኛሽ እንኳ ብትሆን ፎቶሽችን እንዳትልኪላት እስካሁን ከነበረም አስጠፊ ምክንያቱም በገዛ ፎቶሽ አሳልፋ ልትሰጥሽ ትችላለች። በያዘችብሽ በገዛ ፎቶሽ ልታስፈራራሽ  ትችላለች ወይም እሷ ሳታውቀው ከሷ ሌላ ሰው ሊወስደው ይችላል ስለዚህ ፎቶ መላላክ ጭራሽ አስፈላጊ አይደለም።
  ኖርማል ፎቶ እንኳ ቢሆን ከራቁት ፎቶ ጋር አቀናብረው ሊያስፈራሩሽ ስለሚችል ራስሽን ከማንኛውም ፎቶ አፅጂ በሚዲያ የለቀቅሻቸውም ፎቶዎች ካሉም አጥፊያቸው።
    ራስን ቁጥብ ማድረግ ለራስ ነው ሚጠቅመው!


ይ ቀ ጥ ላ ል ክፍል ሁለት

ውድ እህቴ ይሄን ፁሁፍ በውስጥ መስመር ለምታውቂያቸው ሁሉ ሼር የማድረግ ሃላፊነት አለብሽ
ምን አልባት የአንድ ሰው የመመለስ ወይም ጥንቃቄ የማድረግ ሰበብ ልትሆኚ ትችያለሽ እና ለአላህ ብልሽ ሼር አድርጊው።

Share ሼር share

ቀጣዩን ሌሎችን ለመከታተል ቻናሉን ይቀላቀሉ
Coment
@jezakellah

በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል
Join us on t/g channel


https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
የዝሙት ሌላኛው ስሙ የሃራም ፍቅር ነው!