Get Mystery Box with random crypto!

‍ ​ ዳግማዊት ራህመት ደራሲ ኢሳቅ ሀብታሙ ክፍል ሶስት ኤሊያስ ፈገግ ያለሁ ለካ ከራህመ | ʜᴀʟᴀʟ ꜰᴏɴǫᴀᴀ || ሀላል ፎንቃ

‍ ​ ዳግማዊት ራህመት
ደራሲ ኢሳቅ ሀብታሙ
ክፍል ሶስት


ኤሊያስ ፈገግ ያለሁ ለካ ከራህመቴ ደብዳቤ ተቀብሎ ነበር ለሪድዋን ስትልኝ ብላ ሰጠችው
ከፍቼ ማንበብ ጀመርኩ
ሪዱ ሆይ ያመመኝ ነው ህመሜ ምን እንደሆነ ታውቃለ? ናፍቆት ይሰኛል ሐኪሞቹ መዳኒቴ የአንተ አይን እንደሆነ ነገሩኝ ሪፈር ፅፈው ሰተውኛል ሪዱ ሳልሞትብህ አግኘኝ ከሰላምታ ጋር ያንተዋ ራህመት
ራሴን መቆጣጠር አቃተኝ በደስታ ብዛት ስካር ውስጥ ወደኩ ሳይጠጡ መስከር በጣም ደስ ይላል ትምህርት ባይኖረኝም እሷ ጋ ሄድኩ በጣም አምሮባታል ተገናኘን ጥሩ ጊዜ አብረን ካሳለፍን ቡኃላ ስልክ ቁጥሬን ሰጥቻት ተለያየን ለኔ ሲል ኢሊያስ ትምህርት ጀመረ ብዙም ሳይቆይ እኔም ሚኒስትሪ ተፈተንኩ እነ ኤሊያስ ከሁለት ሳምንት ቡኃላ ትምህርት ጨረሱ ክረምቱ ገባ ከእለታት አንድ ቀን የኤሊያስ እናት በጣም ስለታመሙ ለመጠየቅ ሄድን እዛ ስንደርስ እናቱ ወደ አኪራ ሂደዋል ኢሊያስ ከሀዘን መውጣት ተሳነው በጣም ይከብድ ነበር

ከአራት ወራት ቡኃላ ዛሬ በጣም ደስተኛ ሁኛለሁ አይስኩል ገባሁ ኤሊያስም ከነበረበት ስሜት የወጣ ነው ራህመቴ በጣም ኮርታብኛለች ሚኒስትሪ ጥሩ ውጤት በማምጣቴ ምክንያት ኤሊያስ አስጠንቅቆ ነው የላከኝ ፍቅሬን እንድገልፅላት እኔም እሱ ያለኝን ላደርግ ወደ ክፍላቸው ሳቀና ከጓደኞቿ ጋር ሀይለኛ ወሬ ይዛ ነበር አረብሻትም ብዬ ትቼ ወጣሁ ከክፍላቸው ስለ አይስኩሉ ትንሽ ልበላቹ የተሰራው 2006 costa foundation በተባለ የግል ተቋም ነው ጊቢው በጣም ውብ ነው አንድ ነገር ይጎላቸዋል እንጂ ምን መሰላቹ ራህመትን የመሰለች ቆንጆ ሴት እሷን ከፍለዉ ነበር ማስገባት የነበረባቸው ግን ነገ የመጣው ይምጣ ፍቅሬን ከመግለፅ ወደኋላ አልልም ብዬ ለራሴ ቃል የማይደርስ ነገር የለምና ቀኑ ከብዙ ደቂቃዎች እና ረዢም ከሚመስሉ ሰዓታት ቡኃላ ወደነ ራህመት ክፍል ሊሄድ ስል የትምህርት ቤቱ ጊቢ ዝግ ነበር ያለኝ አማራጭ በአጥር መሽሎክ ነበረ አደረኩት ግን ምን ያደርጋል ተያዝኩ መጨረሻ ለይ ወላጅ እንዳመጣ ተወሰነብኝ ምንም እንኳን ብባረርም ራህመቴ ጋር መሄዴ ስለነበረብኝ ቀጥታ ሄድኩ ያየውትን ማመን ተሳነኝ

የኔዋ ራህመቴ ከሆነ ልጅ ጋር ስትሳሳም አየሁ ምን አለ በህልሜ ቢሆን እያለቀስኩ ወደ ቤት ገባሁ ካሁን ቡኃላ ማድረግ ያለብኝ ትምህርቴ ለይ ማተኮር ብቻ ነው ሀሰኔ ተጫውቶብኛል እስኪ ምን አድርጌው ነው እንዲህ የሚጫወትብኝ? ደግሞ የኔስ ነገር አይገርምም አምኜው ጊዜዬን መፍጀቴ እሷ ጋር ለማሳለፍ ስል ስንት ክፍለ ጊዜ ፎረፍኩ ይበለኝ የራሴ ጥፋት ነው የሚገርመው እኮ የኤሊያስ ነገር ነው ተሳስተህ ነው እንጂ እሷ እንዲህ አታደርግም ማለቱ ከአይኔ በላይ ማንንም አላምንም እርግጠኛ ነኝ ራሷ ናት ዱዓ ማድረግ ጀመርኩ ከጥቂት ጊዜያት ቡኃላ ራህመት አይኗን በጨው አጥባ መነጋገር አለብን አለችኝ
የጨረስን መስሎኝ
እባክህ ምን ተፈጥሮ ነው አታስጨንቀኝ
እኔ ልጠይቅሽ እንጂ ካልሰገድክ ካልቀራህ እንዳታናግረኝ ያልሽበት ኢማን ነው አጅ ነቢ ወንድ ጋር ያሳሳመሽ? እኔን አጅ ነቢ ወንድ አልጨብጥም ብለሽ መሳሳሙን እንዴት ደፈርሽ ባክሽ?
ስለምንድ ነው የምታወራው
ከልቤ አፍቅሬሽ ነበር እንኳን ደስ አለሽ ተጎድቻለሁ
እኔም እኮ አፈቅርሃለሁ
እረ ባክሽ ታዲያ ሌላ ወንድ ጋር ምን አሳሳመሽ የኔ ፍቅር ነው?
ብዬ ሳልጨርስ በጥፊ ብላኝ ሄደች ከትንሽ ቆይታወች ቡኃላ ራህመቴ ሁለት ሰዎችን ይዛ መጣች የሆነ ቦታ የማቃቸው መሰለኝ አንዷ ራህመቴን ቁርጥ ይበልጥ ግራ ተጋባሁ ለምን ይዛቸው መጣች እነማን ናቸው? ራህመቴ እያለቀሰች ነው ለምንድ ነው የምታለቅሰው? እንባዋን እና ጎሮሮዋን እየጠረገች
አሚና ትባላለች እሱ ደግሞ ጣሂር ፍቅረኛዋ ነው በስንት ልመና ነው ወደ ዚህ ያመጣዋቸው
አሀ ትዝ አለኝ ገና አንቺ ጋር ተመሳስላብኝ ነው እሱን ነበር ያየሁት
መንታ ነን እኔም ጠርጥሬ ነበር የተፈጠረውን ስነግራት እንዳየችህ እና ያለቀስክ እንደሄድክ ነገረችኝ አሁንስ እውነታው ገባህ
በጣም ይቅርታ ልረዳሽ ስላልሞከርኩ ሽልማቱ ይገባኝ ነበር
የቱ ሽልማት
ጥፊዋ ናታ
በጣም ይቅርታ ማድረግ አልነበረብኝም ግን አትዘንብኝ የማደርገውን ሳጣ ነው
ኧረ ችግር የለውም
እኔ ምልህ ስሄድ ለምን አላስቆምከኝም
ልብሽ እኔ ጋር ስለሆነ ትመለሻለሽ ብዬ ነው

በቃ እንዴት ልንገራቹ በጣም ደስ ብሎኛል አሁን ራሱ ቤት ውስጥ ብቻዬን ስስቅ ያበድኩ መስሎት ኤሎ የተገረመ ነው ሁሉም ነገር ለከይር ነው በራህመት ማዘኔ መጣላቴ መጨረሻ ለይ የዘወትር ምኞቴ የነበረው ቃል ከአንደበቷ ሰማው ሰሞኑን ጥሩ ጊዜ አብረን ያሳለፍን ነው ዛሬ የሆነ የምነግርህ ነገር አለ ብላኝ ወደ ሷ የሄድኩ ነው

ክፍል አራት ይቀጥላል

ይ ላ ሉን share
┏━ ━━━━ ━┓
@Halal_Fonqaa
┗━ ━━━━ ━┛