Get Mystery Box with random crypto!

HALAALE TUBE -ሀላሌ ቲዩብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ halaaletube — HALAALE TUBE -ሀላሌ ቲዩብ H
የቴሌግራም ቻናል አርማ halaaletube — HALAALE TUBE -ሀላሌ ቲዩብ
የሰርጥ አድራሻ: @halaaletube
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 613
የሰርጥ መግለጫ

📡JOURNALIST AT .W...
ምን ማግኘት ይፈልጋሉ ስኮላርሽፕ
👉ክፍት የስራ ቦታ ማስታወቅያ
ወቅታዊ መረጃ
👉ሃገራዊና ዓለም አቀፍ ዜናዎችን
👉ስፖርት
👉ከታሪክ ገፅ እና ለየት ያሉ መረጃዎችን በፍጥነት ከታዓማን ምጮች ።
በቻናላችን ወደ እናንተ እናደርሳለን Join And Share አትርሱት ።
👇
@Jozerfu
ለመሬጃ
0934074262
አዲሎዓዊነት አይኑር። ፍቅር ያብዛልን።

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-21 15:51:32
36 viewszerfu samuel, 12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 15:09:35
67 viewszerfu samuel, 12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 15:09:08
በአይቮሪ ኮስት ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት የሚፈቅድ ረቂቅ ህግ መቅረቡ በመብት ተሟጋቾች ዘንድ ቁጣ ቀሰቀሰ

በአይቮሪ ኮስት የሚገኙ የሴቶች መብት ተሟጋቾች ለወንዶች ከአንድ በላይ ሚስትን ማግባትን ህጋዊ ለማድረግ የቀረበው ረቂቅ ህግ በመቃወም ለእኩልነት የሚደረገው ትግል ወደ ኋላ የሚመልስ እርምጃ ሲሉ ቁጣቸዉን ገልጸዋል፡፡

እ.ኤ.አ 1964 አይቮሪ ኮስት ከአንድ በላይ ማግባት በህግ ከልክላ የነበረ ሲሆን በበርካታ የዓለም ሀገራት የተከለከለ ነው ፡፡ነገር ግን በምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ውስጥ በመስፋፋት ላይ ይገኛል፡፡

የመብት ተሟጋች ቡድኖች የአይቮሪኮስት ሴቶች የስርዓት እኩልነት እና መድልዎ ይደርስባቸዋል ሲሉ ይናገራሉ፡፡የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ድርጊቱ በሴቶች ላይ አድሎአዊ ነዉ ጠይቋል።ሕጉ በፓርላማ ድምጽ ከመሰጠቱ በፊት በሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት መከለስ ይኖርበታል።

በናትናኤል ሀብታሙ
#ዳጉ_ጆርናል
43 viewszerfu samuel, 12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 15:08:27 በደብረማርቆስ ከተማ ጥይትም ሆነ ርችት መተኮስ የሚከለክል ደምብ ፀደቀ

የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ደብረማርቆስ ከተማ ተግባራዊ የሚሆን በከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት የሰላምና ደህንነት ደምብን መርምሮ በማሻሻል ማፅደቁን የደብረ ማርቆስ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል ።

ማንኛውንም ሰው ስምሪት ከተሰጠው የህግ አስከባሪ ውጭ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳይሰጠው ማንኛውንም የጦር መሳሪያ ወደ ከተማ ይዞ መግባት ፣ በከተማ ውሰጥ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑንና ክልከላውን ተላልፎ የተገኘ ሰው 1000 ብር እንደሚቀጣ አፅድቋል ።

በተጨማሪም ማንኛውንም ሰው አስገዳጅ ሁኔታ ካላጋጠመው በስተቀር ጥይት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን እንዲሁም በየትኛውም ሁኔታ ርችት መተኮስ የተከለከለ ሲሆን ይህንን የተላለፈ በአንድ ጥይት 2000 ብር ሲቀጣ በርችት 500 ብር እንደሚቀጣ መመሪያው መፅደቁን የደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የኮሚኒኬሽን እና ሚዲያ ዋና ክፍል ሀላፊ የሆኑት ምክትል ኮማንደር ዮሐንስ በየነ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

ምክር ቤቱ ካፀደቃቸው ተጨማሪ ደምቦች መከካል ሺ በቡድንም ሆነ በተናጠል ማስጨስም ሆነ ማጨስ እና ጫትን ህጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው ከሁለትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ማስቃም ከመከልከሉ ባለፈ የገንዘብ ቅጣት እንዳለው ገልፀዋል ። በምክር ቤቱ ሌሎች ደምቦች ቀርበው መፅደቃቸውን ምክትል ኮማንደር ዩሐንስ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል ።

በአበረ ስሜነህ
#ዳጉ_ጆርናል
41 viewszerfu samuel, 12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 15:08:01
ቻይና አሜሪካ በህዋ ላይ የምታደርገዉን ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንድታቆም አሳሰበች::

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ዣኦ ሊጂያን ዋሽንግተን በህዋ ላይ የምታደርገዉን ወታደራዊ እንቅሰቃሴ እንድታቆም አሳስበዋል፡፡
አሜሪካ በህዋ ላይ ትጥቅ በመታጠቅ ላይ ነች ያሉት ቃል አቀባዩ፣ከድርጊቷ በመቆጠብ የህዋ ደህንነትን ማስጠበቅ አለባት ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም አሜሪካ በህዋ ላይ የበላይነትን የማስፈን ስትራቴጅንና እንደ ዳይሬክት ኢነርጅ፤የተቆጣጣሪ ኮሙኒኬሽን ሲስተም በመዘርጋት ላይ እንደምትገኝም ተነግሯል፡፡
አገሪቱ አደገኛ የውጭ ጠፈር መሳሪያዎችን በከፍተኛ ሁኔታ በማዘጋጀትና በማሰማራት ላይ ትገኛለች ስትልም ቻይና ከሳለች፡፡
በተጨማሪም ዋሽንግተን በአለም አቀፍ ስትራቴጂካዊ መረጋጋት ላይ ከፍተኛ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል በተባለዉ ጠፈር ላይ ስለላ ስለመጀመሯም ቤጂንግ ማስታወቋን ሲ ጂ ቲኤን ዘግቧል፡፡

በቤዛዊት አራጌ
ሐምሌ 13 ቀን 2014 ዓ.ም
54 viewszerfu samuel, 12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 20:58:36
67 viewszerfu samuel, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-19 20:56:51
95 viewszerfu samuel, 17:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:49:00
በካሚላት መህዲ ላይ አሲድ የደፋው ግለሰብ ከ30 በላይ ሴቶችን በማጭበርበር ተጠርጥሮ በቁጥጥር ስር ዋለ!

ከ13 ዓመታት በፊት በካሚላት መህዲ ላይ አሲድ ደፍቶ የግድያ ሙከራ ወንጀል በመፈፀም የሞት ፍርድ ተፈርዶበት በማረሚያ ለ12 ዓመታት ቆይቶ በምህረት የተፈታው ደምሰው ዘሪሁን የማነ፤ አሁን ደግሞ ከ30 በላይ ሴቶችን ገንዘብ በማጭበርበር ወንጀል ተከሶ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ከ13 ዓመታት በፊት በፍቅረኛው ካሚላት መህዲ ላይ አሲድ በመድፋቱ በጥር 21 ቀን 2000 ዓ.ም በተከሰሰበት የግድያ ሙከራ ወንጀል በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የሞት ቅጣት የተላለፈበት ደምሰው ዘሪሁን የማነ የተባለው ወይም ራሱን ሳምሶን እያለ የሚጠራው ተጠርጣሪ በወቅቱ ቅጣቱ ወደ የዕድሜልክ እስራት ተሻሽሎለት ማረሚያ ቤት ቢወርድም 12 ዓመት ከ7 ወራት እንደታሰረ እስራቱን ሳይጨርስ በይቅርታ ተለቋል።

ተጠርጣሪው ውሎ ሳያድር በተለያዩ ወንጀሎች ተከሶ ድጋሚ ታስሮ ስለመለቀቁም የፌደራል ፖሊስ ምርመራ ያመለክታል።

ከዚያ በኋላም ተጠርጣሪው ከ30 በላይ ሴቶችን ገንዘብ በማጭበርበር ወንጀል ተከሶ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፤ ለአብነትም ነዋሪነቷን በሀገረ ጀርመን አድርጋ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በኮንስትራክሽን ዘርፍ በኢንቨስትመንት በተሰማራችው መሐሪት ክፍሌ ላይ ከባድ የማታለል ወንጀል ስለመፈፀሙ ነው ፖሊስ ያስረዳው።

Via EBC
https://t.me/Halaaletube
145 viewszerfu samuel, edited  12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 15:47:42
የቀድሞ የጋምቢያ የስለላ ተቋም ኃላፊ የሞት ፍርድ ተበየነባቸዉ

የጋምቢያ ፍርድ ቤት በቀድሞው ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ የጭካኔ አገዛዝ የመጨረሻ ቀናት በ2016 በአንድ የፖለቲካ መብት ተሟጋቹ ላይ ግድያ የፈጸሙ የሀገሪቱን የቀድሞ የስለላ ሀላፊ ያንኩባ ባድጂ እና ሌሎች አራት የደህንነት አባላት ላይ የሞት ፍርድ ተበይኖባቸዋል፡፡

የፖለቲካ መብት ተሟጋቹ ኤብሪማ ሶሎ ሳንዴንግ የተቃዋሚው የተባበሩት ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ግንባር ከፍተኛ አመራር የነበረ ሲሆን በጸረ መንግስት ተቃውሞ በያህያ ጃሜህ አገዛዝ ዘመን ታስሯል።ከሁለት ቀናት የእስር ቤት ቆይታ በኃላ በድብደባ ህይወቱ አልፏል።

የፖለቲካ መብት ተሟጋቹ ኤብሪማ ሶሎ ሳንዴንግ ግድያ ህዝባዊ ቁጣዉን በማባባስ ለ22 አመታት ስልጣን የጨበጡት ፕሬዝዳንት ጃሜህ ከስልጣን እንዲወገዱ ምክንያት ሆኗል።ጃሜህ እ.ኤ.አ በ2017 ወደ ኢኳቶሪያል ጊኒ ሸሽተው በስደት ላይ ይገኛሉ፡፡

https://t.me/Halaaletube
112 viewszerfu samuel, edited  12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 09:29:26 የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ወደ ስራ መግባቱን አስታወቀ

ሐምሌ 06 ቀን 2014(ኢዜአ) የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ወደ ስራ መግባቱን አስታውቋል።

የሰላም አማራጭ አብይ ኮሚቴው የመጀመሪያ ስብሰባውን ማካሄዱን የኮሚቴው አባል አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል።

አምባሳደር ሬድዋን እንዳሉት ኮሚቴው በአፍሪካ ሕብረት መሪነት ለሚካሄደው ንግግር የራሱን የአሰራርና ሥነምግባር አካሄድ ተወያይቶ ወስኗል።

በንዑሳን ኮሚቴዎች በመደራጀትም ኃላፊነት ተከፋፍሎ ስራውን ጀምሯል ሲሉ አስታውቀዋል።

በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ያለውን ችግር ለመፍታት መንግስት ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ.ም ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን በሰብሳቢነት የሚመሩት በአጠቃላይ ሰባት አባላት ያሉት የሰላም አማራጭ ዐቢይ ኮሚቴ መሰየሙ ይታወሳል።

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

https://t.me/Halaaletube
125 viewszerfu samuel, 06:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ