Get Mystery Box with random crypto!

እናንብብ

የቴሌግራም ቻናል አርማ maedot29 — እናንብብ
የቴሌግራም ቻናል አርማ maedot29 — እናንብብ
የሰርጥ አድራሻ: @maedot29
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 531
የሰርጥ መግለጫ

ስነልቡና ፣ ግብረገብ ፣ ሐይማኖታዊ እውነቶችን እና አስተማሪ ጽሑፎችን ከተለያዩ መጽሐፍት በመቀንጨብ ይቀርባሉ። መጽሐፍትን ይተዋወቃሉ።
እርሶም ያስተዋዉቁ! Join ያድርጉ ጓደኞቻችሁን Invite በማድረግ ወደ ገፁ ያስገቡ።
ዘመኑን ዋጅተን ለኛ ያወቅናትን ለጓደኞቻችን እናጋራ።
Our Group Chanel
https://t.me/maedot29
በማንበብ ባለብሩህ አእምሮ ይሁኑ!።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-08 06:53:28

16 views03:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 03:11:22
ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን . . .

ቢሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን ሌላ መንገድ አለ! ሌላ ሕይወት አለ! ሌላ አቅጣጫ አለ! ሌላ አማራጭ አለ!

• እውነት ነው፣ ተምሬ ቢሆን ኖሮ ጥሩ ነበር . . . የመማሩን እድል ካላገኘሁ ግን ሕይወትን ውብ የሚያደርጉ ሌሎች ብዙ አማራጮች አሉ፡፡
• እውነት ነው፣ ፍቅረኛ ቢኖረኝ ኖሮ ጥሩ ነበር . . . ትክክለኛ ፍቅረኛ ካላገኘሁ ግን ትክክለኛ ሕይወት የምመራበት ብዙ እድሎች አሉኝ፡፡
• እውነት ነው፣ ትዳሬ በሰላም ቀጥሎ ቢሆንና ባይፈርስ ጥሩ ነበር . . . አንዴ ከሆነና ሁኔታውን በፍጹም ማደስ ካልቻልኩ ግን የተዝረከረከውን ሕይወቴን አፋፍሼ፣ ሰብስቤና እንደገና አደራጅቼ በአዲስ መልኩ ሕይወት ይቀጥላል፡፡
• እውነት ነው፣ የምወደው ስራ ቢኖረኝ ኖሮ ጥሩ ነበር . . . ሁኔታው ያንን ለማግኘት ካልፈቀደልኝ ግን ባለኝና ካለሁበት በመነሳት የማድግበትን መንገድ የመፈለግ መነሳሳቱ አለኝ፡፡

በአጭሩ፣ ሕይወት እኔ እንደምፈልጋት ብትሆን ጥሩ ነበር፣ ካልሆነ ግን ለምን አልሆነም ብዬ ደብቶኝ አልውልም፡፡ ቀና እላለሁ! ብርቱ ሰው ለመሆን እወስናለሁ! ስብር አልልም! አልደካክምም!

ከዶ/ር ኢዮብ ማሞ ገጽ የተወሰደ
https://t.me/maedot29
77 viewsedited  00:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 02:58:37 ክረምትና ጠፍጣፋ ቲቪዎቻችን

ፍላት ስክሪን ቲቪዎችን የሚያበላሹ ነገሮች

. ቮልቴጅ

ሁሉም እቃዎችን የሚያበላሸው የተለመደው የቮልቴጅ መጨመር እና መቀነስ ነው አብዛኛው ቲቪዎች የራሳቸው መቆጣጠሪያ ስለሌቻው ቦርዳቸው ቶሎ ለመቃጠል ይዳረጋል ስለዚህ 500 V Stabilizer ገዝተው ይጠቀሙ።

. የቲቪ የጀርባ መብራቶች (Backlight) መቃጠል

ላይቶቹ ሚቃጠሉበት ወቅት ቲቪዎቹ ምስል ማሣየት አቁመው ድምፅ ብቻ ማሠማት ይሆናል ይህ ነገር እሚከሠተው የባክ ላይቶቹ እድሜ (life span) ሲያልቅ እና ከፍተኛ ሀይል ሲመታቸው ይቃጠላሉ በቶሎ ማስቀየር ያስፈልጋል።

. ፅዳት

ስክሪኑ ላይ Spray ረጭቶ ማፅዳት በፍፁም ሊደረግ እማይገባ ነው። ስክሪኑ በጣም Sensitive ስለሆነ ውስጥ ውሀ ገብቶ በቀላሉ ይበላሻል። ለማፅዳት ሲፈልጉ በንፁ ለስላሣ ጨርቅ ላይ ስፕሬውን በትንሹ በመርጨት ማፅዳት ይችላሉ።

. ኬብል

በክረምት ወቅት HDMI ኬብል አይጠቀሙ መብረቅ በዲሹ ኬብል አልፎ በHDMI አማካኝነት ቲቪዎን ቀጥታ ያገኘዋል

በዚ ጊዜ Av ጃክ መጠቀም የተሻለ ነው።

. የስክሪን መሰበር ነው።

በተለያዩ አጋጣሚዎች ስክሪን ይሰበራል ይሰነጠቃሉ ማሰቀየር በጣም_ውድ ነው፤ ስለዚህ ልንጠነቀቅላቸው ይገባል።

ቲቪዎን ከፍ አርጎ ግድግዳ ላይ መስቀል ያስፈልጋል።

▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።

ለተሻለ ለውጥ እንተጋለን!!
━━━━━━━━━━━━━━━
━━━━━━━━━━━━━━━
▬▬▬▬▬ Share ▬▬▬▬▬



https://t.me/maedot29
51 views23:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 16:43:52

57 views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:56:10

68 views18:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 21:39:11 የተለየ ጥረት ያስፈልግሀል!

ታሪክ መስራት ከፈለክ አብዛኛው ሰው የማያደርገውን ማድረግ አለብህ፤ ሌላው ሲተኛ አንተ ትነሳለህ፣ ሌላው ጊዜውን በከንቱ ነገር ሲያጠፋ አንተ ራስህ ላይ እና ስራህ ላይ ታጠፋለህ፣ ሌላው ገንዘብ ሲያጠፋ አንተ ታስቀምጣለህ፣ ሌላው ወደ ፈጣሪው ለመቅረብና ፀሎት ለማድረስ ጊዜ ሲያጣ አንተ ይበልጥ በመንፈሳዊነትህ ትጠነክራለህ!

ወዳጄ የተለየ ነገር ከፈለክ የተለየ ጥረት ያስፈልግሀል።

መልካም ቆይታ!
66 views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-04 16:47:49

75 views13:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-01 22:51:45

98 views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-29 19:42:36 በሆነ ባልሆነው አትጸጸቱ!
“የሕይወት ጸጸቶች” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ

አንዳንድ የምንጸጸትባቸው ስህተቶች እጅግ ጎጂ ስለሆኑ ሊያሳስበን ይገባል፡፡ ከዚያ ባላነሰ ሁኔታ ሊያሳስበን የሚገባ ጉዳይ ቢኖር ግን በሆነ-ባልሆነውና የመጸጸት ዝንባሌያችን ጉዳይ ነው፡፡ አብዛኛው የሕብረተሰቡ ክፍል በሆነ-ባልሆነው ነገር ሲጸጸት እንቅልፈ አጥቶ ያድራል፡፡ እነዚህ ከጥቃቅንና ከአይቀሬ የየእለት ስህተቶች የሚመጡ ጸጸቶች “ጉዳት የለሽ” ጸጸት ከምንላቸው የጸጸት አይነቶች ይመደባሉ፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት የምንጸጸትባቸው ነገሮች ምንም እንኳን ከተሳሳተ ምርጫ የመነጩ ቢሆኑም የሚያስከትሉት ሰበብ ግን እጅግ አናሳና በሕይወት ላይ ምንም አይነት ጫና የማያስከትሉ በመሆናቸው ነው፡፡

ሆኖም፣ ይህን መሰል ጸጸቶችን የሚያስከትሉ ጥቃቅን ውሳኔዎች ውጤታቸው አናሳ ቢሆንም፣ በሕይወታችን ያለብንን የምርጫ ችግር ሊጠቁሙን ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም በሆነ ባልሆነው የመጨናነቅ ባህሪ ካለብን ትኩረትን የመሳብና ከዋናው ስራችን የማስተጓጎል ተጽእኖ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ራስህን በእንደዚህ አይነት የጸጸት ሁኔታ ስታገኘው ልትወስዳቸው የምትችላቸው እርምጃዎች በርካታ ሲሆኑ ለመንደርደሪያ ያህል የሚከተሉትን መጠቀም ትችላለህ፡፡

1. ለምርጫና ለውሳኔ አትቸኩል
የየእለት ጥቃቅን የኑሮ ዘይቤአችን፣ ውሳኔዎቻችንና ምርጫዎቻችን የአጠቃላይ የሕይወት አመለካከታችንን ጠቋሚ እንደሆነ ቀንደኛ የሆኑ የስነ-ልቦና አዋቂዎች ይነግሩናል፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ በጥቃቅንና ከፍተኛ ችግር በማያስከትሉ የየእለት የሕይወት ሂደቶች ውስጥ ያለን አመለካከት አጠቃላይ በሕይወት ላይ ያለንን ንጽረተ-ዓለም ጠቋሚ ስለሆነ ነው፡፡ በጥቃቅንና ለክፉ በማይሰጡ ሁኔታዎች ላይ የምርጫና የውሳኔ ችግር ካለብን በግዙፉና ትልቅ ተጽእኖ በሚያስከትሉ ሁኔታዎች ላይም የሚኖረን ሁኔታ ከዚያ ተለይቶ አይታይም፡፡ ይህ የሆነበት ምክንያት፣ በአንድ ጎኑ ትልልቅ ውሳኔዎች የጥቃቅኖቹ ጥርቅም በመሆኑ፣ በሌላ ጎኑ ደግሞ በትንንሽ ነገሮች ላይ የሚንጸባረቅ አመለካከታችን በሌላውም ላይ የሚገለጥ በመሆኑ ነው፡፡

2. ከራስህ ጋር “ተጫወት”
ሁሉን ነገር አክርሮ መያዝ በሕይወት ላይ ይህ ነው የማይባል ሰበብ ያስከትላል፡፡ ለትልቁም ለትንሹም ማዘን፣ መነጫነጭና መጸጸት ከዋናው የሕይወት የሃዲድ መስመር ያወጣናል፡፡ በተለይም ጉዳት-የለሽ ሁኔታዎች ውስጥ ራሳችንን ስናገኘው ከራሳችን ጋር አንዳንድ ጨዋታዎችን መጫወት እንችላለን፡፡ ልክ ጓደኛችን አስቂኝና ለጉዳት የማያደርስ ስህተት ሲሰራ እንደምንስቅበትና ተጨዋውተነው እንደምናልፍ ከራሳችንም ጋር በዚህ መልክ “ወዳጅነትን” መፍጠር እንችላለን፡፡ ይህንን አይነቱን ብዙ ሰዎች የሚጠቀሙበትን ልምምድ ተግባራዊ ለማድረግ ግን ትንሽ ፈታ ማለትን ይጠይቃል፡፡ ምናልባት ሕይወትህን በሙሉ ውስጥህ ተቋጥሮና ግንባርህ ተኮሳትሮ ያሳለፍክ አይነት ሰው ከሆንክ ነገሮችን አቅልሎ በማየት ትንሽ ፈታ እንድትል ላደፋፍርህ፡፡

3. ትንንሾቹን ተለማመድባቸው
በቀን ውሎህ ባደረግሃቸው ተግባሮች፣ ወይም በተናገርካቸው ነገሮች ምክንያት ማታ በመኝታህ ላይ ሆነህ የጸጸትን ሃሳቦች በማውጣትና በማውረድ ስትገላበጥ ራስህን አግኝተኸው ካወቅህ የጸጸት ርእስ እንደሚመለከትህ ጥርጥር የለውም፡፡ ከዚህ በፊት በወሰንካቸው ውሳኔዎችና ባደረግሃቸው አንዳንድ ምንም ችግር በማያስከትሉ ምርጫዎች ምክንያት “ምነው ይህንን ባላደረግሁ” በማለት ውስጥህ የሚታመም ከሆነ ከዚያ የተለየ ምርጫ ልስጥህ፡፡ ጥቃቅን እንቅፋቶች ነገ ለሚገጥሙህ አደገኛ እንቅፋቶች መለማመጃ ናቸው፡፡ ትንንሽና ለክፉ የማይሰጡ ችግሮች ነገ ከሚመጡ ከፍተኛ ችግሮች እንዴት መጠበቅ እንዳለብህ የምትማርባቸው ሁኔታዎች ናቸው፡፡ ይህንን ሁኔታ በሚገባ ተገንዝበህ ጉዳታቸው አናሳ የሆኑትን ሁኔታዎች በማሰብ ከመጸጸት ይልቅ ትምህርትን በማግኘት ለነገህ ተዘጋጅባቸው፡፡
***
ሰኔ 23-2014
121 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 06:19:32 ጥላቻ ይወገድ

ጥላቻ ሰፍኗል በዓለማችን:: መፍትሔውስ ምን ይሆን? የሚናገር ይጠላል:: ዝምም የሚል ይጠላል:: የሚሠራ ይጠላል:: የማይሠራም ይጠላል:: በምሥራቅ ጥላቻ አለ:: በምዕራብም ጥላቻ አለ:: በሰሜን ጥላቻ አለ:: በደቡብም ጥላቻ አለ:: በቤተ መንግሥት ጥላቻ አለ:: በቤተ ክህነትም ጥላቻ አለ:: በክርስትና ጥላቻ አለ:: በእስልምናም ጥላቻ አለ:: የቤተ ክህነት አገልጋዮች ጥላቻን ይሰብካሉ:: የመንግሥትም ሠራተኞች ጥላቻን ይሰብካሉ:: ፍቅርና ይቅርታም ከምድረ ገፅ ተወግደዋል:: በገዳም ጥላቻ አለ:: በዓለምም ጥላቻ አለ:: የሰው ዘር እንደ ገና በጥላቻ ተበከለ::
በጥላቻ የተፀነሱ ሕፃናት የጥላቻ ልብወለድ ሲነበብ በማሕፀን የሰሙ ጩቤ ጨብጠው ተወለዱ:: በመጀመሪያ አባቶችን ሰለቡ, እናቶችንም ደፈሩ, ጌታቸውንም ሸጡ:: በጥላቻ ጥበባቸው እስከ ሰማይ ከፍ ከፍ አሉ እስከ ሲኦልም ወረዱ::
ለሁለት ሺ ከዚያም በላይ ዓመታት የተሰበከው ፍቅር ወዴት ሄደ እስኪ በአንድነት እንፈልገው ምናልባት ጥላቻን ከዙፋኑ አውርዶ ቢያንኮታኩተው:: ጭፍን ጥላቻን ከሰው ሕሊና አውጥቶ የሚጥለው ሰው ራሱን ከራሱ በላይ መውደድ ሲችል ነው:: ራሱን የሚወድ ሌላውንም ይወዳልና:: ራሱን የማይወድ ሌላውንም አይወድምና::

ስለዚህ የዘር ጥላቻን የሚዘሩ, የሚኮተኩቱና የሚያዋጉ, የንፁሐንን ደም በከንቱ የሚያፈሱ/የሚያስፈስሱ የድሆችን ቤትና ንብረት የሚዘርፉ, ነፍሰ ጡሮችን, አጥቢዎችን እናቶችን የሚያሰቃዩ የሚገርፉ #ወዮላቸው! #ወዮላቸው! #ወዮላቸው!

በሁሉም ሃይማኖቶች ያሉ #ሰባኪዎች በሙሉ
ወደ ውስጣቸው ይመልከቱ:
በመጀመሪያ ራሳቸውን ይስበኩ:: በውስጣቸው ያለውን የጥላቻ ጉቶ ነቅለው ይጣሉት:: በዚያ ፈንታ ፍቅርንና ይቅርታን ይትከሉበት:: ፍቅርንና ይቅርታን ኮትኩተው ያሳደጉ ሰባኪዎች ጥላቻን ለማስወገድ አቅምና ጉልበት ያገኛሉ:: ከቁጣውም ያመልጣሉ::

በዓለም ሁሉ በከንቱን የፈሰሰው/የሚፈስሰው የንጹሐን ደም እንደ አቤል ደም ወደ እግዚአብሔር ደርሶ ክስ አቅርቧል:: የእግዚአብሔር የቁጣ ሰይፍም ተመዝዟ!
የቁጣው መላእክትም ትእዛዝ ለመቀበል በተጠንቀቅ ቆመዋል:: ጥላቻን የሚሰብኩ ንፁሐንን የሚገድሉ/የሚያስገድሉ ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!

የሚሰማ ጆሮ ያለው ይስማ!!!

ስብሐት ወክብር ለስሉስ ቅዱስ ይደሉ!

ሰአሊ ለነ ቅድስት
ቅድስት ሆይ! ለምኝልን!

የመ/ፀሐይ መኮንን
19-10-2014
(26/06/2022)
126 views03:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ