Get Mystery Box with random crypto!

'አንባቢዎች መሪዎች ናቸው!!!!!' ሰኔ 30 የንባብ ቀን እየተከበረ ነው። የኢትዮጵያ ደራስያን | ሐበሻ ጣዕም/Habesha Taem

"አንባቢዎች መሪዎች ናቸው!!!!!"

ሰኔ 30 የንባብ ቀን እየተከበረ ነው።

የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር በየአመቱ ሰኔ 30 ቀን በኢትዮጵያ የንባብ ቀን እንዲሆን በማቀድ የጀመረው እንቅስቃሴ አመታዊ መርሀ ግብር እየተካሄደ ነው።

በአብርሆት ቤተ መጻህፍት እየተካሄደ ባለው በዚህ መርሀ ግብር ላይ ከአራት አመቱ ታዳጊ አንባቢ ናኦል ጀምሮ የተለያዩ ደራስያን እና ጠንካራ የንባብ ልማድ ያላቸው እንግዶች ስለ ንባብ ጥቅም ልምዳቸውን እያካፈሉ ይገኛሉ።

"አንባቢዎች መሪዎች ናቸው!!!" በሚል ሀይለ መልእክት ስር እየተከበረ በሚገኘው በዚህ ዝግጅት ላይ እንደተነገረው የኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር ሀገር አቀፍ ንባብ ተገቢው ትኩረት እንዲያገኝ በዚህ ክረምት ሰፊ ስራዎች ይሰራሉ ተብሏል።