Get Mystery Box with random crypto!

አሐዱ ባንክ 'አንድ ቅርንጫፍ ለአንድ ልጅ' የበጎ ድጋፍ ፕሮግራም ይዞ መጥቷል አሐዱ ባንክ | ሐበሻ ጣዕም/Habesha Taem

አሐዱ ባንክ

'አንድ ቅርንጫፍ ለአንድ ልጅ' የበጎ ድጋፍ ፕሮግራም ይዞ መጥቷል

አሐዱ ባንክ ሐምሌ 9 ቀን 2014 ዓ.ም በይፋ ስራ የሚጀምር መሆኑን ገለፀ

አሐዱ ባንክ በ7 አደራጅ ኮሚቴ አባላት ታህሳስ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. የተጠነሰሰውንና 10 ሺህ
የሚደርሱ ባለአክሲዮኖችን ያሰባሰበውን በ564 ሚሊዮን የተከፈለ ካፒታል እና በ702 ሚሊዮን የተፈረመ
ካፒታል በታላቅ ዉጥን የተዋቀረዉን የአሐዱ ባንክ ስራ መጀመሩን አስመልክቶ ዛሬ በማሪዮት ኤክስኪዩቲቭ
አፖርትመንት ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጠ

***
የመግለጫው ሙሉ ቃል

አሐዱ ባንክ ክፍተቶች በማስተዋል በዘመኑ
ቴክኖሎጂ የተደራጀና በተደራሽነት በኩል በአገልግሎት
አሰጣጥ፥ በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፥ የተሻለ የፋይናንስ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ሐምሌ 9
2014 ዓ.ም. በይፋ ስራ የሚጀምር መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።

አሐዱ ባንክ እንደ ስሙ፤ ባለዉ የስራ መርሕ መሰረት “ምስጢሩ አንድ ብሎ መጀመሩ' የሚለዉን ለማሳየት
በዋናዉ መስሪያ ቤት ባደራጀዉ ዘመናዊ ቅርንጫፍ ስራዉን በይፋ የሚጀምር ሲሆን ከምርቃቱ እለት አንስቶ
በተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ እና ክልል ከተሞች ዝግጁ የሚያደርጋቸዉን ቅርንጫፎች በመክፈት አጠቃላይ
የቅርንጫፍ ብዛቱን እስከ መስከረም 30 2015 ድረስ 50 የሚያደርስ ይሆናል።

በተጨማሪም ብዛት ያላቸዉ
የባንክ አገልግሎት ወኪሎችንም ይዞ ወደ ገበያ የሚገባ ይሆናል።

ባንካችንን ልዩ ከሚያደርጉት መገለጫዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፤

● በየዓመቱ ከሚያቀርበዉ ብድር እስከ 15% ያህሉን የፋይናንስ አቅርቦት ለሥራ ፈጣሪዎችና ለአነስተኛ
ኢንተርፕራይዞች የሚያመቻች ሲሆን ለተመረጡ ሥራ ፈጣሪዎች በየቅርንጫፎቻችን የምርት ማሳያ
ቦታ ለማጋራት የሚያስችል ሁኔታም እናዘጋጃለን፤

● አጠቃላይ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግ በስፋት በአገሪቱ ዉስጥ ህዝባችን የወኪል ባንh
አገልግሎትን በተለያዩ የዲጂታል አማራጮች ተደራሽ ማድረግ የሚያስችል አጋርነትና ኢደረጃጀትፈጥረናል፤

● ከተለመደዉ በሠራተኛ ከታገዘ የቅርንጫፍ አገልግሎት በተጓዳኝ ደንበኞች በራሳቸዉ የዲጂታል
አገልግሎት የሚያገኙበት የቅርንጫፍ ዉስጥ አገልግሎት አደረጃጀት (experience area)
አመቻችተናል፤

● የገጠር የባንክ አገልግሎትን ለአርሶና አርብቶ አደሮች፣ የገበሬ ማህበራት እንዲሁም በግብርና እሴት
ሰነሰለት ለሚሳተፉ ተዋናዮች በስፋት ለማዳረስ ተዘጋጅተናል፤

● የብድር፥ የአለም አቀፍ ባንክ አገልግሎት፥ እና ማንኛዉም የአገር ዉስጥና የዉጭ ሀዋላ እና ክፍያዎች
ወረቀት አልባ (ዲጂታል) በሆነ መልኩ እንዲከናወን አስቻይ የሆነ መተግበርያ (ፕላትፎረም)
ተዘጋጅቷል፤

● የባንኩ ደንበኞች ካሉበትና ባሉበት ቦታዎች ሆነዉ ራሳቸዉን የባንኩ ደንበኛ ማድረግ የሚችሉበትን
አሰራር ይዘን መጥተናል፤

● የዉስጥ አሰራሩን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባና ዘመናዊ አድርገናል፤
እንዲሁም
ሁሉም የባንኩን አሰራሮች በቴክኖሎጂ ላይ የተመሠረቱ እና የተሳለጡ እንዲሆኑ ማድረጋችን
ተጠቃሾች ናቸዉ።

ማህበራዊ ግዴታችንን ከመወጣት አንፃር፤
ባንካችን ከተቋቋመት ተልዕኮ ጋር የተጣጣሙ ዕሴቶችን ከመኖር አኳያ ከምስረታው ጀምሮ በተለያዩ ማኅበራዊ
ግዴታን ለመወጣት የሚጋብዙ ዝግጅቶች ላይ ተሳትፎ እያደረገ መምጣቱ ይታወሳል።

በቀጣይም ባንኩ
በቋሚነት ወላጅ አልባ የሆኑ ህጻናትን በማደጎ በመረከብ ለማሳደግ፥ አልባሽ አጉራሽ ለሌላቸዉን
ቤተሰቦች የስራ እድል ለመፍጠር፥ እንዲሁም በአገር ታሪክ፥ ባህል እና ቅርስ ጥበቃ ላይ የሚሰሩ አካላት
ጋር በትብብር የሚሰራ ይሆናል።

ሙሉ ዝግጅቱን አጠናቆ አገልግሎት ወደ መስጠት ለመግባት በተዘጋጀበት ዋዜማም ይህንኑ አጠናክሮ
በመቀጠልና ከወዲሁ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ

1ኛ. ሐምሌ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. የአሐዱ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፥ የማኔጅመንት አባላት እና መላው
ሠራተኞቹ የሰዉ ልጅን ክቡር ህይወት ለማስቀጠል ይረዳ ዘንድ ዉድ ከሆነዉን ስጦታ ለመጀመር
በማሰብ የደም ልገሳ መርሐ ግብር ያካሂዳሉ።

2ኛ. ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. በተስፋ አዲስ የካንሰር ሕሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት ከተለያዩ የሀገሪቱ
ክፍሎች በመምጣትና ዉድ የሆነች ህይወታቸዉን ለማትረፍ የህክምና ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ላሉ
የካንሰር ህሙማን የገንዘብ ስጦታ ይበረከታል።

3ኛ በመቀጠልም ሐምሌ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. በጌርጌሴኖን የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል እና በአሥመሮም
ጎዳና ሻወር በመገኘት የምሣ ማብላት መርሐ ግብር ያካሄዳል።

4ኛ. ባንካችን የአገር ቅርስ እና እሴቶችን ተንከባክቦና ጠብቆ ማስቀጠል የሁሉም የሕብረተሰብ ክፍል ኃላፊነት
ነዉ ብሎ ያምናል።

ይህንንም ታሳቢ በማድረግ ሐምሌ 6 ቀን 2014 ዓ.ም. የአገራችን ትልቅ ሃብት
የሆነውን የቅዱስ ላሊበላ ገዳም የእድሳት ስራ ለመደገፍ የብር 500,000.00 ድጋፍ የሚከናወን ይሆናል።

5ኛ. በመጨረሻም ሐምሌ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በስለእናት የበጎ አድራጎት ድርጅት በመገኘት በማዕከሉ ላሉና
እገዛ እየተደረገላቸዉ የሚገኙ ሕጻናትን የመጎብኘትና የገንዘብ ስጦታ የማበርከት መርሐ ግብር
የሚከናወን ይሆናል።

ባንካችን በዚህ ድጋፍ ሳይገደብም 'አንድ ቅርንጫፍ ለአንድ ልጅ' በሚል እሳቤ
ባንኩ በሚከፍታቸዉ ቅርንጫፎች ቁጥር ልክ ድጋፍ እና እገዛ ለሚያስፈልጋቸዉ ልጆች ዓመታዊ
ወጪያቸዉን ለመሸፈን መወሰኑን ስንገልጽ ከታላቅ ደስታ ጋር ነዉ ።

በዚህም የማኅበረሰብ አጋርነቱንና "ከብዙዎች ለብዙዎች" ብሎ የተነሳበትን ዓላማ በተግባር ለማሳየት
እንቅስቃሴውን መጀመሩን ያበስራል።

ሐበሻ ጣዕም