Get Mystery Box with random crypto!

ሞዴልና ተዋናይ ሀናን ታሪክ ይታሽ ሞቢሊያ የተሰኘ የቱርክ ኩባንያ ወኪል ከሆነው ቡሩል ትሬዲንግ ኃ | ሐበሻ ጣዕም/Habesha Taem

ሞዴልና ተዋናይ ሀናን ታሪክ ይታሽ ሞቢሊያ የተሰኘ የቱርክ ኩባንያ ወኪል ከሆነው ቡሩል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ኩባንያ የብራንድ አምባሳደር በመሆን በዛሬው ዕለት ፊርማዋን አኖረች።

ቡሩል ትሬዲንግ እ.ኤ.አ በ2016 የተመሰረተ አስመጪና ላኪ ኩባንያ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ለሶስት የቱርክ ኩባንያዎች የምስራቅ አፍሪካ ገበያ ወኪል በመሆን በመስራት ላይ ይገኛል።

ኩባንያው "ኢንጂ ፈርኒቸር" የሚል የብራንድ ስም በመያዝ ከተለመደው ወጣ ያሉ ፣ ቅንጡ፣ ውብና ማራኪ ፈርኒቸሮችን በልዩ ትዕዛዝ እንደሚያስመጣ ወ/ሮ እንቁጣጣሽ ሀይሌ በዛሬው ዕለት በሀያት ሬጀንሲ ሆቴል በተሰጠው መግለጫ ጠቅሰዋል።

ኩባንያው በደንበኞቹ ጥያቄ መሰረት የሆቴልና አፓርትመንት ቅንጡ ፈርኒቸሮችን በማስመጣት በኬንያ፣ በደቡብ ሱዳን፣ በናይጄሪያ፣ በታንዛኒያ ለሚገኙ ደንበኞቹ ሲያቀርብ መቆየቱን ጠቅሰው በመስከረም 2022 በናይሮቢ የመጀመሪያውን ሾው ሩም እንደሚከፍት ወ/ሮ እንቁጣጣሽ ጠቅሰዋል።

አርቲስት ሀናን ኩባንያው በሀገር ውስጥና በሌሎች ሀገራት ለሚያደርጋቸው እንቅስቃሴዎች በብራንድ አምባሳድነት ለመስራት የፈረመች ሲሆን ክፍያውን በተመለከተ ከፍተኛ ነው በሚል ቁጥሩን ከመጥቀስ ተቆጥበዋል።
አርቲስት ሀናን በብራንድ አምባሳደርነት በመመረጥዋ መደስቷን ገልፃለች።