Get Mystery Box with random crypto!

ድምጻዊ አብርሐም በላይነህ (ሻላዬ) ከእስር ተፈታ! ከ3ኛ ፎቅ ላይ ወድቃ ህይወቷ ካለፈው ዶ/ር | ሐበሻ ጣዕም/Habesha Taem

ድምጻዊ አብርሐም በላይነህ (ሻላዬ) ከእስር ተፈታ!

ከ3ኛ ፎቅ ላይ ወድቃ ህይወቷ ካለፈው ዶ/ር ቤዛ ተዋበ ጋር ተያይዞ ከአንድ ወር በላይ ምርመራ ሲደረግበት የቆየው ድምጻዊ አብርሐም በላይነህ (ሻላዬ) በዛሬው ዕለት ከእስር ተፈቷል።

የፖሊስ የምርመራ መዝገብን ሲመለከት የቆየው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ባሳለፍነው ሀሙስ በነበረ ቀጠሮ የፖሊስ የምርመራ መዝገብ በመጠናቀቁ የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡ እንዲዘጋ ትዕዛዝ መስጠቱ ይታወሳል።

በዕለቱ ከሰዓት በኋላ ጠበቃው ገመቹ መረራ ለፍርድ ቤቱ 1ኛ የፍትሐብሄር ልዩ ልዩ ችሎት አካልን ነጻ የማውጣት መብት ጥያቄ አቅርበዋል። ነገር ግን 10:00 ላይ የችሎቱ ዳኛው ባለመኖራቸው ምክንያት ጥያቄው ሳይታይ አድሯል።

በይደር አርብ ዕለት ለችሎቱ ማመልከቻው ቀርቦ የታየ ቢሆንም፤ ፍርድ ቤቱ መርምሮ ብይን ለመስጠት ለዛሬ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር። በዚህ መሰረት ዛሬ በነበረ ቀጠሮ ችሎቱ የድምጻዊ አብርሐም በላይነህን አካልን ነጻ የማውጣት አቤቱታ ተመልክቶ ድምጻዊ አብርሐም በላይነህ በነጻ ከእስር እንዲፈታ ትዕዛዝ መስጠቱን ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ ዘግባለች። አብርሐም በላይነህ ከእስር ተፈቶ ከቤተሰቡ ጋር መቀላቀሉን ጠበቃው ገልጸዋል።

bbc