Get Mystery Box with random crypto!

#45 አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች ሊሸለሙ ነው! የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ክብር ለ | ሐበሻ ጣዕም/Habesha Taem

#45 አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎች ሊሸለሙ ነው!

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ክብር ለጥበብ! በሚል ርእስ ዘንድሮ ለሁለተኛ ጊዜ በሚያደረገው የእውቅና እና የሽልማት ፕሮግራም በስነ-ጽሁፍ፣ሙዚቃ፣ውዝዋዜ፣ሰርከስ፣ቴአትር፣ሲኒማና በሌሎች አራት ዘርፎች የሚሰጥ መሆኑን ገልጽዋል፡፡ ለሽልማቱ መስፈርቶቹን ያሟሉ 45 አንጋፋ እና ወጣት የኪነጥበብ ባለሞያዎችም እንደተመረጡም ተነግርዋል፡፡

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባለሞያዎችን በህይወት ሳሉ ማመስገንና የእውቅና ሽልማት መስጠት ተተኪ ወጣቶችን የሚያበረታታ ነው ብሎታል፡፡

ሽልማቱ የፊታችን ረቡዕ ሰኔ 29/2014 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን የዘንድሮው ለየት የሚያደርገው የክልሎችን የኪነጥበብ ባለሞያዎች የሚያካትት መሆኑን ነው የባህልና ስፖርት ሚኒስትር በሰተው መግለጫው ያስታወቀው።