Get Mystery Box with random crypto!

እውቁ አሜሪካዊ ድምጻዊ አር ኬሊ በጾታዊ ጥቃት ወንጀል የ30 ዓመት እስር ተፈረደበት ታዋቂው የ | ሐበሻ ጣዕም/Habesha Taem

እውቁ አሜሪካዊ ድምጻዊ አር ኬሊ በጾታዊ ጥቃት ወንጀል የ30 ዓመት እስር ተፈረደበት

ታዋቂው የአሜረካዊ የአር ኤንድ ቢ አቀንቃኝ አር ኬሊ በአሜሪካ ፍርድ ቤት የ30 ዓመት እስር እንደተፈረደበት ተነግሯል።

የ55 ዓመቱ ሙዚቀኛ ባሳለፍነው መስከረም ወር ላይ ነበር በወሲብ ንግድ፣ በህፃናት ላይ ጾታዊ ጥቃት፣ በአፈና እና ሌሎች ከወሲብ ጋር በተያያዙ ወንጀሎች ተከሶ ፍርድ ቤት የቀረበው።

በዚህም ፍርድ ቤቱ ትክክለኛ ስሙ ሮበርት ሲልቪስተር ኬሊ በተባለው ድምጻ ላይ የ30 ዓመት እስር የፈረ ሲሆን፤ ይግባኝ ማለት መብት እንዳለውም አስታውቋል።