Get Mystery Box with random crypto!

የራስ አለም ከንቱ በራስ አለም ውስጥ ጠልቆ መዋኘት : ወዘ ቢሱን ህይወት ለመምራት ደፋ ቀና | ግጥም እና ጥቅሶች

የራስ አለም ከንቱ

በራስ አለም ውስጥ ጠልቆ መዋኘት : ወዘ ቢሱን ህይወት ለመምራት ደፋ ቀና ያለች ህሊና ማሰብ ሲሰለቻት የምትወስነው ብቸኛ አማራጭ ነው!! አጠገብ ያለ ቁም ነገር ድምፅ ሲያሰማ በራስ አለም : ዙሪያ ገባውን ቀን ሳይል ለሊት ለመስረቅ የሚጣደፈው ኮቴ ሲያሰማ አሁንም በራስ አለም : ማስተዋል በራስ አለም ተቆጣጥራ ቸልታ ሲበዛ በራስ አለም

ይሄ የብቻ አለም ገላግሌ እየመሰለን በብዙ ተታለንበታል! ይሄ የራስ አለም ስታጠፋ አይቀጣህም ወይም አይመክርህም : ደስታህን ተደስተህ ባለምክንያቱን አታመሰግንበትም : አሁንም በራስህ አለም ሰምጠሀላ:: ከዚህ አለም እንድቶጣ ሀይለኛ ማዕበል አትጠብቅ ደስታህን ተደሰተው : መከራህን ተጋፈጠው : ከራስ አለም ውስጥ ያስቀመጥከውን የህሊናህን ጓዝ ጠቅልለህ ውጣ ተቀላቀለው ሁነታውን : ማዕበሉ ከሚያነቃህ በጊዜ ንቃበት : ያንተ አለም ከንቱ ለህይወትህ ማይቀርለት አለም ግን ዘላቂ:: የፈጠረህን ታመሰንግ ዘንድ ከንቱን ንቀህ ንቃ!!

@Tziom
@gtem_na_tks
@gtem_na_tks