Get Mystery Box with random crypto!

የሰማይ ቤት ግሮሰሪ (አሱ እንደፃፈዉ) . . 'ጨረቃ' ምንላት ግሮሰሪ ቤት ናት!!! 'ሰማይ' ለም | ግጥም እና ጥቅሶች

የሰማይ ቤት ግሮሰሪ
(አሱ እንደፃፈዉ)
.
.
"ጨረቃ" ምንላት
ግሮሰሪ ቤት ናት!!!
"ሰማይ" ለምንለው ፣ ቀውጢ ከተማ
ሥራ ምትጀምረው ፣ሲሆን ነው ጨለማ!!!
..................................................
በር እንደከፈተች ፣ አብረው የሚወጡ
ከዋክብት ደሞ...
ሰካራሞች ናቸው ፣ እሷ ጋ ሚጠጡ!!!
*
በጣም የሰከረው...
ከሰማይ ፈጥፍጦ ፣ ራሱን ሲገድል
"ተወርዋሪ ኮከብ" ..
ማለት ነው የኛ እድል!!!
****
ተወርዋሪ ጠርሙስ ሊሆንም ይችላል!
ማን ያውቃል?

(( በላይ በቀለ ወያ ))

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks