Get Mystery Box with random crypto!

# ቃልህ ወዴት ነው ያለው ከሀሣቤ የራቀው ከልቤ ገስግሶ ጠልቆ የመሸገው ሄዶ በኖ የጠፋው ቃልህ | ግጥም እና ጥቅሶች

# ቃልህ

ወዴት ነው ያለው ከሀሣቤ የራቀው
ከልቤ ገስግሶ ጠልቆ የመሸገው
ሄዶ በኖ የጠፋው ቃልህ ላይመለስ
ተንዶ ፈሶብኝ ያለው አልታፈስ

ቆርቁሮኛል ህይወት በርትቷል ህመሙ
ያልተጓዘ ቃልኪዳን ፀንቶብኝ ሸክሙ
ማይተው ሆኖብኝ አጥቻለው መላ
እኔጋ ትርጉሙ ፅኑ ነው መኃላ

ጠፍቷል እኮ መኖር ቃልን ካኖርክበት
የማይድነው ልቤ አንተን ካመነበት
አልመለስ ብሏል ቀልቤ ከሄደበት
ለጐደለ አካሌ ልቤን መልስለት

ፂዮን ምትኩ

@gtem_na_tks
@gtem_na_tks