Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅራችን ቅኔ በፍቅር ሰሌዳ በመዋደድ ቅኔ፣ የኔ ልብ ባንተ ያንተም ልብ በኔ። የነፍስያችን ወግ | ግጥም እና ጥቅሶች

የፍቅራችን ቅኔ

በፍቅር ሰሌዳ በመዋደድ ቅኔ፣
የኔ ልብ ባንተ ያንተም ልብ በኔ።
የነፍስያችን ወግ ካሳባችን ሰርፆ፣
በልባችን ሀዉልት ፍቅራችን ተቀርፆ።
ደምህና ደሜ ፍፁም ተዋህዶ፣
ባንደበት ሊገለፅ በቃላት ተጋምዶ።
ቀና ብለህ እያት ዉቢቷን ጨረቃ፣
የብርሃን ዝናር በወገቧ ታጥቃ።
ተስፋ ልታድል ጽልመት ለጋረደዉ፣
በትዝታ ጋሪ ሞሽራ ልትሸኘዉ።
ያቺ ዉብ ጨረቃ ምስክር ትሁንህ፣
በሷ ብርሃን የኔ መልክ ይታይህ።
ከዋክብትን ስታይ ከደጃፉ ቆመህ፣
በአንተ ብርሃን ድምቀቴ ይታወስህ።
የኔና አንተ ፍቅር በወርቅ ይመሰላል፣
ካፈር ተደባልቆ ከሳት ይፈተናል።
ከጭቃዉ ይጠራል ነበልባሉን አልፎ፣
ከነፍስ ተራቆ ከህሊና ገዝፎ።

ዔደን(@ediwub)
@gtem_na_tks
@gtem_na_tks