Get Mystery Box with random crypto!

#የኃጢአት #ይቅርታ መቼም በደል በሌለበት ስለ ይቅርታ ማሰብ አይቻልም። ስለ እርቅ በትክክል ለ | Grace Commission (የጸጋ ተልዕኮ)

#የኃጢአት #ይቅርታ

መቼም በደል በሌለበት ስለ ይቅርታ ማሰብ አይቻልም። ስለ እርቅ በትክክል ለማወቅ ከፈለግን ስለ በደል እና ኃጢአት እንዲሁም ስለ መዘዛቸው ከመረዳት መጀመር የግድ ነው። መፅሐፍ ቅዱሳችን የኋላ ታሪካችንን ሲያወሳን "በበደላችሁና በኃጢአታችሁ ሙታን ነበራችሁ።" በማለት ነው (ኤፌ 2:1-2)። ኃጢአታችን ከእግዚአብሔር ለይቶን እንደነበርም በዚሁ ክፍል ተነግሮናል። (ኤፌ 2:12)። ሮሜ 6:20 ላይም መፅሐፍ ቅዱሳችን "የኃጢአት ባሪያዎች ሳላችሁ ከፅድቅ ነፃ ነበራችሁ" እንዳለን እኛ ሰዎችን ኃጢአት ከእግዚአብሔር ለይቶ የራሱ አድርጎን ቆይቶአል።

ሆኖም እግዚአብሔር ኃጢአታችንን ይቅር ብሎ የራሱ ሊያደርገን ወደደ። ኃጢአት ከእግዚአብሔር ለይቶ የራሱ እንዳደረገን እግዚአብሔርም ከኃጢአት ለይቶ የራሱ ሊያደርገን ወሰነ። በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ሥራም ሀሳቡን አሳካ።
የኢየሱስ የመስቀል ሞት እኛን ከበደል አርቆ ወደ አምላክ ለማቅረብ ተብሎ የፈሰሰ ደም ነው፤ ከኃጢአት ለይቶ የእግዚአብሔር ለማድረግ የተከፈለ ዋጋ ነው፤ ከአመፃ ጋር አጣልቶ ከፈጣሪ ጋር ለማስታረቅ የተሰጠ መስዋዕትነት ነው። (ኤፌ 2:12-13፣ ቆላ 1:14፣ ሮሜ 6:6፣11)።

በክርስቶስ ኢየሱስ የመስቀል ሥራ ላመናችሁ ለሁላችሁም የምስራች! ከኃጢአት ተለይታችሁ የእግዚአብሔር ሆናችኋል። ከአመፃ ጋር ተጣልታችሁ ከአምላክ ጋር ታርቃችኋል፤ ከበደል ርቃችሁ ወደ ፈጣሪ ቀርባችኋል።

ቢኒያም በርሄ
የ"ከበፊት እስከ ወደፊት" መጽሐፍ ፀሐፊ

#መጽሐፉን #ማንበብ #የምትፈልጉ፦ ኢማና መ/ቤት (ቦሌ)፣ ቤሪያ መ/ቤት (4ኪሎ) እና መሰረተ ክርስቶስ መ/ቤት ስታዲየም ዙሪያ

ለሌሎች አካፍሉ፦
ይህን ሊንክ ለ10 ሰዎች በመላክ አገልግሉ፦

#Grace #Commission
https://t.me/gracecom